This Content Is Only For Subscribers
ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የጀመረቸው ጥረት አስተማማኝ ደርጃ ላይ መድረሱን የኢፌዴሪ ፕሬዜዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ አስታወቁ፡፡ ስለወደብ ማንሳት የሚያስቀጣና የሚያሸማቅቅ ተገባር ተደርጎ በቆየባት ኢትዮጵያ ይህን መስማት ፤ዩ የታሪክ እጥፋት እንደሆነ ተመልክቷል።
በመሪነት ሞገስ፣ ለማድመጥ በሚያነሳሳ ቅላጼ የ6ኛውን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት የከፈቱት ፕሬዚዳንቱ፣ “የኢትዮጵያ መንግሥት ከሶስት አሥርት ዓመታት በኋላ የባሕር በር ጉዳይን ዓለም አቀፍ መነጋገሪያ ማድረግ ችሏል” ሲሉ በዲፕሎማሲው አግባብ የተኬደበትን ርቀት አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የባህር በር በጦርነት ለማስመስለስ እየተዘጋጀ ነርው ለሚሉት ቡድኖች ምላሽ ሰጥተዋል።
“የባሕር በር ፍትሕዊ ተጠቃሚነታችንን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያገኘንበት ነው”
ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ኢትዮጵያ እጣ ፋንታዋ እና መጻኢ ዕድሏ ከዓባይ እና ከቀይ ባሕር ውሃዎች ጋር በእጅጉ መቆራኘታቸውን አስታውሰዋል።
ኢትዮጵያ ፍትህን ባልተከተለ መንገድ ህዝብን ባላሰተፈ መንገድ ከቀይ ባህር ተገልላ መቆያቷን በማንሳት ይህንኑ ለማስተካከል መንግሥት ፍትሃዊ ተጠቀሚነቷን ለማረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝ ይፋ አድርገዋል። ቀደም ሲል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በተደጋጋሚ ቀይ ባህር ላይ የመመለስ ጉድሳይ የማይቀር መሆኑን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
የኤርትራ መንግስት ለአሜሪካ መንግስት ድርድር ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አማካይነት ካስታወቀ በሁውላ፣ አዲስ አበባ ባለው ኤመባሲው በኩል በድጋሚ “ድርድር እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ አይታሰብም” ማለቱ አይዘነጋም።
ከሶስት አሥርት ዓመታት በኋላ የባሕር በር ጉዳይን ዓለም አቀፍ መነጋገሪያ ማድረግ መቻሉን ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ፣ በቀጣይነትም በአፍሪቃ ቀንድ በጋራ የመልማት ፍላጎትና ትስሰር ለማጠናከር ዲፕሎማሲያዊና ሰላማዊ ጥረቶች እንደሚጠናከሩ ጠቁመዋል። እሳቸው ባይዘረዝሩትም የሶማሌያ መሪ ሃሰብ ሼክ ኢትዮጵያ ፤ላይ ያሳዩት ለውጥና ወደብ ለማግኘት እየሄድችበት ያለውን ሰላማዊ አካሄድ አጋባብ መሆኑን መናገራቸው፣ ከኬንያና ኡጋንዳና ደቡብ ሱዳን ጋር የተደረሰው ሰፊ ትብብርና ታሪካዊ ስምምነቶች አፍሪቃ ቀንድ ላይ ኢትዮጵያ የያዘቸውን አቅጣጫ ትክክለኛነት የሚያመላክት መሆኑን ቀደም ሲል ባለሙያዎች መናገራቸው አይዘነጋም።
” በአባይ ወንዝ ያገባናል፣ በቀይ ባህር አያገባችሁም ማለት አይቻለም። ፍትሃዊም አይደለም። ተቀባይነትም የለውም”
መንግሥት ፍትሃዊ እና አስተማማኝ የባሕር በር ለማግኘት ከቀጣናው ሀገራት ጋር በትብብር እንደሚሰራም አበክረው ሲያስታውቁ፣ ” የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ አስተማማኝ ደርጃ ላይ ደርሷል” በማለት ነው። አክለውም “የባሕር በር ፍትሕዊ ተጠቃሚነታችንን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያገኘንበት ነው” ብለዋል።
ጉዳዩን ከአባይ ጋር በማያያዝ ኢትዮጵያ ሀገራችን በድንበር ተሻጋሪ ሀብት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ስተቀበል፤ አስተማማኝ የባሕር በር የማግኘት መብቷን ማረጋገጥ እንደሚገባት ጠቁመዋል፡፡ ቀደም ሲል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” በአባይ ወንዝ ያገባናል፣ በቀይ ባህር አያገባችሁም ማለት አይቻለም። ፍትሃዊም አይደለም። ተቀባይነትም የለውም” ማለታቸው አይዘነጋም።
በሌላም በኩል በዓባይ ወንዝ ላይም የጋራ መተባበርና መተማመን እንዲዳብር የተፋሰሱን ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርጉተግባራትን እንደሚያከናውን እና በንቃት እንደሚሳተፍ ፕሬዚዳንቱ አክለው ገልጸዋል።
በትቅሉ በሁለቱ ታላላቅ የውሃ ሀብቶች ዙሪያ መንግሥት ያልተቆራረጠ ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን እያደረገ መሆኑን ያስታወቁት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ
የታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አጋጥመውት የነበሩ ፈተናዎች በጥበብ በማለፍ ማጠናቀቅና በደመቀ ሥነ- ሥርዓ ማስመረቅ መቻሉን የያዝነው ዘመን ታላቅ ብስራትና ድል መሆኑ አንስተው፣ ፍትሀዊ የባህር በር ጥያቄያም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ቅቡልነት እንዲያገኝ መደረጉን አብራርተዋል።