የናይል ትዕዛዝ Order of the Nile – ግብጽ ለትራምፕ ያበረከተችው ሽልማት ከህዳሴው ግድብ ጋር ተቆራኝቷል

Date:

የግብፅ መንግሥት የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትሯ፡ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የተሰጠው የክብር ሽልማት ከህዳሴው ግድብ ጋር ያለውን አንድምታ ገለጹ

ዋሽንግተን ዲ.ሲ.— የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሀማስና እስራኤል እርቀ ሰላም ላበረከቱት አስተዋጽኦ የግብፅ መንግሥት ያበረከተላቸው የናይል ትዕዛዝ (Order of the Nile) የክብር ሽልማት፣ በይፋ ከታሰበው ዓላማ ባሻገር፣ ከኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) ጋር የተያያዘ ልዩ ትርጉም እንዳለው ተገለጸ።

ይህን የገለጹት የግብፅ መንግሥት የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ራኒያ አል-መሻት ናቸው። ሚንስቴሯ መግለጫውን የሰጡት በዋሽንግተን ዲ.ሲ. የአለም የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ሳለ ለ”ጂዜሮ ወርልድ ሚዲያ (GZERO World Media)” በሰጡት ቃለ ምልልስ ነው።

ሚኒስትር አል-መሻት እንዳብራሩት፣ ሽልማቱ በትራምፕ ሰላም የማስፈን ሚና የተሰጠ ቢሆንም፣ የሽልማቱ ስም የሆነው ‘ናይል’ ለግብፅ ካለው ከፍተኛና ልዩ ቦታ አንጻር “ሌላ ተጨማሪ ትርጉም”እንዳለው አስረድተዋል።

ይህ ተጨማሪ ትርጉም የመጣው፣ ግብፅ በአሁኑ ወቅት “ከህዳሴው ግድብ በሚመጣው ተጽዕኖ ” እና በግብርና ጉዳዮች ላይ “ስምምነት ለመድረስ ከፍተኛ ጥረት” እያደረገች ባለችበት ወሳኝ ወቅት በመሆኑ እንደሆነ ተጠቁሟል።

በማጠቃለያም፣ ሽልማቱ የአባይ ወንዝ ለግብፅ ያለውን “ህልውናዊ ክብደት” እና በግድቡ ዙሪያ ፍትሐዊና ዘላቂ መፍትሔ የማፈላለግ ጥረቷን የሚያንጸባርቅ “ዲፕሎማሲያዊ ምልክት” መሆኑን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የሽግግር መንግስት ቀመኞች ከአሜሪካ ወደ አምስተርዳም ፤ በባንዳነትና ማሕጸን ውስጥ ድሮ የተወለደው “አዲሱ ፍኖተ ካርታ”

በአለባቸው ጉብሳ ባልንጀራየ ሰሞኑን አምስተርዳም ውስጥ በተካሄደ የዲያስፓራ የኢትዮጵያ...

ሃገራዊ የወርቅ ገበያ ዋጋ መናሩ የተለያየ ትንተና እየቀርበበት ነው

አዲስ ሪፓርተር ጥቅምት 12 ቀን 2018 አዲስ አበባ -...

ኦርቶዶክስ በኢትዮጵያ የተለያየ የፓለቲካ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 2 ቀን 2018 በኢትዮጵያ እየተወሳሰበ የመጣውን...