በትግራይ መምህራን ውዝፍ ደመወዛቸውን እንዳይጠይቁ መከልከላቸውን አስታወቁ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለመንግሥት ሰራተኞች መክፈል የነበረበትን ውዝፍ የደሞዝ ክፍያ ለመክፈል ፍቃደኛ አልሆነም። በክልሉ የሚገኙ ከሃምሳ ሺህ በላይ መምህራን ውዝፍ ደሞዛቸው ይከፈለን የሚል ጥያቄ እንዳያነሱ መከልከላቸውን አስታውቀዋል፤

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞችን ውዝፍ ክፍያ ለመክፈል 20 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው የተገለፀ ሲኾን ለመንግሥት ሰራተኞች የሚውለው ይኸው ክፍያ በተያዘው በጀት ዓመት እንደሚከፍል ቃል ትገብቶላቸው ነበር። ይሁን እንጂ በተባለው መሰረት ተፈፃሚ እንዳልሆነ የትግራይ ክልል መምህራን ማሕበር ለአዲስ ሪፖርተር አመልክቷል።

ማህበሩ ከዚህ ቀደም ከጊዜያዊ መስተዳድሩ ጋር ባደረገው ውይይት ለመንግስት ሰራተኞች መክፈል የሚጠበቅበትን ውዝፍ ደመወዝን በአንድ ጊዜ መክፈል እንደማይችልና በአዲሱ በጀት ዓመት ከሚኖረው በጀት(አሁን በተጀመረው ዓመት ለማለት ነው) ቢያንስ አምስት በመቶውን ለውዝፍ ደሞዝ መክፈያ ለማዋል መወሰኑን ተገልፆላቸዋል እንደነበር አስታውሰዋል።

አዲሱ በጀት ዓመት ከተጀመረ ወዲህ ክፍያው እንዲፈፀምላቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም የክልሉ ጊዜያዊ መስተዳደር ፍቃደኛ አለመሆኑ፣ ፈቃደኛ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን “የደመወዝና ጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ጉዳይ እንዳታነሱ” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ለጊዜው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የማህበሩ አመራር አስታወቀዋል።

ትግራይ ክልል የሚገኙ የመንግስት ስራተኞች በጦርነቱ ወቅት ያልተከፈላቸው የአስራ ሰባት ወራት ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ እንደነበር ገልፀው ሆኖም እስካሁን መፍትሔ ማግኘት አለመቻላቸውን ለማወቅ ተችሏል። ከልሉ ከበጀቱ በተጨማሪ ከፌደራል መንግስት ከፍተኛ ገንዘብ መውሰዱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከትግራይ ተወካዮች ጋር በተወያየበት ወቅት መናገራቸው አይዘነጋም። በጦር ሰራዊት ኃይል ከስልጣናቸውና ከትግራይ እንዲወጡ መደረጋቸውን ያስታወቁት አቶ ጌታቸው ረዳ የክልሉን በጀት አብዛኛውን ለታጣቂዎች ደሞዝና ቀለብ ያውሉ እንደነበር መናገራቸው አይዘነጋም።

የትግራይ ክልል መምህራን ማሕበር ጉዳዩን ወደ ፍርድቤት ወስዶት የፌደራል መንግስት የ12 ወራት እንዲከፍል የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ደግሞ የ5 ወራት ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፍሉ ውሳኔ ቢሰጥበትም በክልሉ ያሉ መምህራን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አለመተገበሩን ተናግረዋል።

የመምህራን ማሕበሩ እንደገለፀው ከሆነ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፍርድ ቤት ውሳኔ ካሳለፈ በኃላ የደመወዝና ጥቅማጥቅም ጥያቄዎች በተመለከተ ጉዳዮ በፍርድ ቤት ዳግም አቤት እንዳይባልባቸው የሚከለክል ደንብ በማውጣት መምህራን ያቀረቧቸው የመብት ጥያቄዎች ምላሽ እንዳያገኙ እንደተደረገ መረጃውን ያካፈሉ አስታውቀዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመምህራን ጥያቄ ታፍኗል የሚል እምነት እንዳላቸውና ለውዝፍ ደመወዝና ተያያዥ ጥቅማ ጥቅም ጉዳዮች ጥያቄያቸው ቁርጥ ያለ ምላሽ መንግስት እንዲሰጥ ጠይቀዋል ተብሏል።

ቀደም ሲል የተወሰነውን ውሳኔ ተግባራዊ እንዳልተደረገ የሚገልፀው መምህራን ማሕበሩ በዚህም ምክንያት ደንቡ እንዲሻር እንዲሁም የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲደረግ የትግራይ መምህራን ማሕበር የፍርድ ቤት ክርክሩ ቀጥሏል ተብሏል።

ይሁንና፣ ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንዳለበት የሚገልፀው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፌዴራሉ መንግስት የሚያገኘውን የበጀት ድጎማ ሙሉ በሙሉ ለደመወዝ እና ሥራ ማስኬጃ እያዋለ መሆኑ ይገልፃል።

አጠቃላይ 50 ሺህ ገደማ የሚገመቱ በክልሉ የሚገኙ መምህራንን ጨምሮ ከ120 ሺህ በላይ ለሚሆኑ መንግስት ሠራተኞች ከአንድ አመት በላይ ያልተከፈለ ውዝፍ ደመወዝ እንዳልተከፈላቸውና የሚመለከተው አካል መፍትሔ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ላይ ናቸው ተብሏል።

ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳድር በቂ ምላሽ እየተሰጣቸው ባለመሆኑ ሳቢያም ለፌደራል መንግስት ጥያቄዎቻቸውን ለማቅረብ እንደሚገደዱ ገልፀዋል። አጠቃላይ ለመንግሥት ሰራተኞች ያልተከፈለው ውዝፍ እዳ ለመክፈልም ቢያንስ 20 ቢልዮን ብር እንደሚያስፈልገው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ሃገራዊ የወርቅ ገበያ ዋጋ መናሩ የተለያየ ትንተና እየቀርበበት ነው

አዲስ ሪፓርተር ጥቅምት 12 ቀን 2018 አዲስ አበባ -...

ኦርቶዶክስ በኢትዮጵያ የተለያየ የፓለቲካ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 2 ቀን 2018 በኢትዮጵያ እየተወሳሰበ የመጣውን...

“ኤርትራ እንደ አገር ትክሰማለች”

የአየር ንብረት ለውጥ አደጋና ስጋትን መቋቋም ከማይችሉት አገራት መካከል...