የመረጃ ጦርነት ወጥመድ፡ ሃገርንና መንግሥትን ለጥቃት ያጋለጠው የጌታቸው ረዳ የአልጀዚራ “ፊት ለፊት” ፕሮግራም ሲፈተሽ

Date:

ዓላማው ግልጽ ነው። አስታጥቀው፣ አደራጅተው፣ ሴራ አዋቅረው ያሰማሩትን ኃይል መርዳት ነው፤ ለቅጥረኞቻቸው ሽፋን በመስጠት ሲያፈራርሷቸው እንዳየናቸው አገራት ሊያፈርሱን ነው። ቀደም ሲል ከነጀሌዋቻቸው በአልጃዚራ በኩል ኢትዮጵያ ላይ ሲተፉ የነበሩ በመክሸፋቸው በሌሎች ተወክለው ስለማየታችን የጋዜጠኛነት ካባ ለብሳ ስለ ሞራል ያነሳችው የአማራ፣ የአፋር፣ የኦሮሞ እና ሌሎች ዜጎች ላይ የተፈጸመውና እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ ደንታ የማይሰጣት “ሞራለ ሙሉዋ” የአዲስ ስታንዳርዷ ጸዳለና “ነጩ ትህነግ” የሚባለው ሼትል ከፊት ሲታዩ ድግሱ ፍንትው ብሎ የሚታይ ይሆናል። ከዚያም በላይ አክቲቪስት ሆኖ ተተርጉሞ የተሰጠውን የጌታቸውንና የጠቅላይ ሚኒስትርን አብይ ልጥፎች እያነበነበ ሲወራጭ የነበረው ዲቃላ እንግሊዛዊ ማህዲ መካከል የገባው ጌታቸው ረዳ ይህን ድግስ አያውቀውም ሊባል አይችልም። ለሁሉም ትምህርትና ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የዘወትር አምደናችን የሚከተለውን ልከውልናል።

በአለባቸው ጉብሳ ነጻ አሳብ

እንደ መግቢያ

አዲስ ሪፖርተር ዒላማቸውን ኢትዮጵያ ላይ ያደረጉ በውጭ ሃገር መንግስታት ባለቤትነት፣ ጥቅምና  መተዳደሪያ ህግ የሚተዳደሩ እንደ  (ቢቢሲ፣ ዶቼቬሌ፣ ቪኦኤ እና ሌሎች) የመሳሰሉ የመገናኛ አውታሮች ሚና አስመልክቶ ሰፊ ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል። 

እነዚሁ መገናኛዎች ቀለብ ሰፋሪዎቻቸው የሃገራቸውን ብሔራዊ ጂኦስትራቴጂክ ግብ ለማሳካት እንደ አንድ ብሔራዊ የተፅዕኖ መሳሪያ የሚጠቀሙባቸው መሆናቸውን በመግለፅ በቀረበው ጽሁፍ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ርዕዮተ ዓለምና እሴቶችን ለማስረፅ፣ እምነትና አመለካከት ላይ የሚፈልጉትን ዓይነት ተፅዕኖ ለመፍጠር እና የጠላት ሃገርን ሰላማዊ አስተዳደርን ለማወክ ጥቅም ላይ ሲውሉ እንደነበር ከዚህ በፊት በዝርዝር አቅርቦ እንደነበር አይዘነጋም።

እነዚህ መገናኛ ብዙሃን የሃገራቸውን በተለይ ሶቪየት ኅብረት፣ የአሜሪካና የእንግሊዝ ስትራቴጂክ ግባቸውን በኢትዮጵያ ውስጥ ለማስከበር ባደረጉት ፉክክር ርዕዮተ ዓለም በማስረፅ፣ በመንግሥትና በህዝብ መካከል መተማመን እንዳይኖር፣ የሕዝቦች እርስ በርስ ግንኙነት በጥርጣሬና በጥላቻ የተሞላ እንዲሆን እና የሃገር ምሶሶ የሆኑት የፀጥታና ደህንነት፣ የመከላከያ፣ የፍትህ አስተዳደርና ሌሎች የመንግሥት ተቋማት በሕዝብ ዘንድ እምነት እንዳይጣልባቸው በማድረግ ህዝባዊ አመፅ በመቀስቀስና ለሽምቅ ተዋጊዎች ወታደራዊ ፕሮፓጋንዳ ድጋፍ በመስጠት የቀዳማዊ ኃይለሥላሴና የደርግን መንግሥትን ለመጣል ያደረጉትን አስተዋጽዖ አይተናል።

ባለሁለት ስለቱ አሁናዊ የመረጃ ጦርነት

የቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት በአሜሪካ መራሹ የምዕራቡ ጎራ አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ ዓለም ወደ ተረጋጋ ስርአት ውስጥ በመግባቱ የመረጃ ጦርነት ከጥቃት ይልቅ ማስተማርና ተፅዕኖ መፍጠር ላይ ያተኮረ ነበር። ሆኖም ግን ይህ የዓለም ስርዓት ሌሎች ከላሾች (ቻይና እና ራሽያ) ሳላጋጠሙት ዓለም ወደ ቀድሞው የጂኦፖለቲካ ፉክክር ሊመለስ ችለዋል። የፉክክሩ ተዋንያን የሆኑት ኃያላን ሃገራት ፍላጎታቸውና የተፅዕኖ አቅማቸው የተለያየ በመሆኑ ስርዓቱ ባለብዙ ዋልታ ሃገራት ስርዓት Multipolar world order እየተባለ ይጠራል።

ይህ ፉክክር የሚፈፀመው የመረጃ፣ የኢኮኖሚ፣ የወታደራዊ፣ የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂ እና ሌሎች ብሔራዊ የተፅዕኖ አቅሞችን (National Instrument of powers) በመጠቀም ነው። በመጀመሪያው የዝቃዛው ጦርነት ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ የመረጃ ጦርነት ማስፈፀሚያ መሳሪያዎች እንዳሉ የቀጠሉ ሲሆን በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አማካኝነት ይበልጥ ፈጣን፣ በጥልቀትና በስፋት ተደራሽ በመሆን ተፅዕኖን በማባዛት (Multiply)፣ በማጉላት (Amplify) እና በማፍጠን (Accelerate) የሃገር ደህንነት ስጋቶችን ዓይነትና ብዛት በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከፍ አድርገውታል። 

በመሆኑም በዚህ ፈጣን ዓለም አቀፍ የመረጃ ከባቢ ውስጥ ሃገራት የጥቃት ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ፣ የአመራርና የዓላማ አንድነትን እንዲሁም ሃገራዊ የፖለቲካ አንድነትን (political cohesion) በመጠበቅ ነጻነታቸውን፣ ደህንነታቸውንና ብልፅግናቸው ለማረጋገጥ የታቀደ፣ የተደራጀና የተቀናጀ የተግባቦት ስትራቴጂ (Coordinated communication Strategy) በመቅረፅና በመተግበር ላይ ይገኛሉ። በአንፃሩ ደግሞ በባለቤትነት የሚያስተዳድሩትን ተጽዕኖ ፈጣሪ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ከሌሎች ዘመን ያፈራቸው የዲጂታል ቴክኖሎጂ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር በማቀናጀት ስትራቴጂከ ብሔራዊ ጥቅማቸው ለማስከበር በተፅዕኖ መፍጠሪያ መሳሪያነት እየተጠቀሙት ይገኛሉ።

ዘመኑን ያልዋጀው ጌታቸው

እንግዲህ በዚህ አሁናዊ የዓለም የመረጃ ጦርነት ከባቢ ውስጥ ነበር የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ልዩ አማካሪ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ “ፊት ለፊት” ከተሰኘው የመሃዲ ሀሰን የአልጃዚራ ፕሮግራም እንግዳ ሆኖ የቀረበው። የፕሮግራሙ ቅርፅ የተለመደው ዓይነት ቢሆንም ይዘቱና አቀራሩቡ ሆን ተብሎ የኢትዮጵያን መንግሥት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ለማጥቃት ኢላማ አድርጎ እንደተዘጋጀ ማንም ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው በቀላሉ የሚረዳው ነው።

አቶ ጌታቸው በዚህ ፕሮግራም እንግዳ ሆነው የቀረቡት፣ ሃገራት የመረጃ መሳሪያዎቻቸውን በመጠቀም የጂኦፖለቲካ ፉክክር የሚያደርጉበት ዘመን ላይ መሆናቸውን በቅጡ በመረዳት አይመስልም። የዘመን መንፈስ ለውጥ መኖሩን አልተረዱም። በመሆኑም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሆን ተብሎ በታቀደና በተቀናጀ መልኩ ለተዘጋጀ የመረጃ ጥቃት ሃገራቸውና በአማካሪነት የተሾሙበት መንግሥታቸውን አጋልጠው ሰጥተዋል። ይህ አሌ ሊባል የማይችል ሃቅ ነው። በመንግሥት ግልጽነትና ተጠያቂነት ሽፋን ልንሸነግለው ወይም ሽፋን ሰጥተን ልናስተባብለው አንችልም። የሚገርመው ጉዳይ እስካሁን አቶ ጌታቸው በዚህ ፕሮግራም ላይ የቀረቡት በየትኛው አቅማቸው ነው? በግል ነው ወይስ በአማካሪ ሚኒስትርነት የሚለው እስካሁን አልተጠየቀም፤ ተጠይቆም ከሆነ ምላሽ አልተሰጠም። ይህ ግልጽነት አለመኖር ለችግሩ ትክክለኛውን መፍትሄ ለመጠቆም እንድንቸገር አድርጓል።

የሆኖ ሆኖ፣ እኛም ቻይናዎች “ቀድሞ ማወቅ ያሸልማል” እንዲሉ በዚህ ፅሁፍ መሃዲ ሃሰን በፕሮግራሙ ጌታቸው ረዳን እንግዳ አድርጎ በማቅረብ በታቀደና በተቀናጀ መልኩ በኢትዮጵያ ላይ የፈፀመውን የመረጃ ጥቃት ዓይነትና ስልት ዋና ዋና የሆኑትን በማቅረብ ወደፊት ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈፀም ትምህርት ይሆነን ዘንድ እንደሚከተለው አቅርበናል።

የሼቴል እና የፀዳለ ፅምዶ

ጌታቸውን ለመሞገት ቀድሞ ታስቦና ታቅዶ ዝግጅት የተደረገው ፕሮፌሰር ሼተልና ፀዳለ ለማን አቀናጅቶ ፓናሊስት በማድረግ መሃዲ ሃሰን የሚያቀርውበን ክሶች እንዲያጠናክሩና እንዲያጎሉ ተደርገዋል። ፕሮፌሰር ሼትል ትሮንቮል “ነጩ ወያኔ” በሚል ስያሜ ይጠራሉ። የትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ያህል በትህነግ ጉዳይ ወሳኝ ሰው ነበሩ። ዛሬም አፍቃሪ ትህነግነታቸውን ራሱን ከትህነግ ያገለለውን ጌታቸው ረዳን በመሞገት አስመስክረዋል። በትግራይ የተካሄደውን ኢ-ሕገመንግሥታዊ ምርጫ መቀሌ ተገኝተው “ሕጋዊ ነው” በማለት ያጸደቁና የተሟገቱ ናቸው። በተለይም በኅልውናው ጦርነት ወቅት ለትግራይ ታጣቂ ኃይሎች TDF የሚል የወል ስም ማውጣታቸውን ራሳቸው በአንደበታቸው በኩራት መናገራቸው አይዘነጋም። እኚህ ሰው ናቸው እንግዲህ ገለልተኛ ሙህር ፓናሊስት ሆነው የቀረቡት።

ፀዳለ ለማ ለሕወሃት ስስ ልብ ያላት አብሬ መቃብር ካልገባሁ የምትል የጉዲፍቻ ተጋዳላይ ነች። ፀዳለ ለሕልውናው ጦርነት መነሻ የሆነውን ትህነግ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመውን የሃገር ክህደትና ወታደራዊ ወንጀል በጋዜጣና በድህረ-ገጿ አትዘግብም። ከሴኮቱሬ በላይ ወያኔ መሆኑዋን የምታሳየው ዓለም የሚያውቅውን ትህነግ በመከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመውን የግፍ ወንጀል በመካድ ነው። ትህነግ በማይካድራና በኮምቦልቻ የፈፀመውን የዘር ፍጅት ወንጀል አያሳስባትም። በዚህ ጉዳይ አንዳች ነገር ተንፍሳ አታውቅም፣ ዝምታዋ “እሰይ፣ ደግ አደረጉ” የሚል መልዕክት ይሰጣል።

እንግዲህ አነዚህን ሁለት አፍቃሬ ትህነግ “ጋዜጠኛ” እና “ምሑር” ነው እንደ ገለልተኛ ፓናሊስት አድርገው ጌታቸውን ለመሞገት አልጃዚራዎች ያቀረቧቸው።

ይህ ምስል ቦኮሃራ ያደረሰው ጉዳት ነው፤ በሻሸመኔና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ይህን መስለ ጉዳት ያስተባበሩ በወኪሎቻቸው አማካይነት ኢትዮጵያን ወደዚህ መሰሉ አስከፊ መልክ ለመቀየር በግልጽና በተዘዋዋሪ እየሰሩ ነው

የታፈነው የብስራት ለሜሳ ድምጽ

ዶ/ር ብስራት ለሜሳ በውይይቱ በፓናሊስትነት ከነበሩት መካከል ነበሩ። መሃዲ ሃሰን የብስራትን ሃሳብ ለመቀበል ዝግጁ እንዳልነበር የምንረዳው ሃሳቡን ለማስጨረስ ፋታ የማይሰጥ መሆኑ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት የሰላምና የምክከር ሂደት በሃገር አቀፍ ደረጃ እያደረገ ያለውን ጥረት ሲያስረዳ ያስቆመዋል። እንደውም ስለ ውይይቱ በቅርብ በሰጠው ቃለ መጠይቅ በጣም ጥቂት ደቂቃ ነው የተሰጠኝ፤ ከዚያችው ላይም የተናገርሁትን በትክክል አላቀረቡትም፤ ድምፄ ታፍኗል። በውይይቱ የሰጠኋቸውን አስተያያቶች ቆርጠው እነሱን የሚጠቅማቸውን ብቻ አስገብተዋል ብሏል። እንግዲህ ይህ አፋኝ ሚዲያ ነው መንግሥት ጋዜጠኞችን አሰረ ብሎ የሚከሰው። የዶክተር ብስራት ጥረት በሃገራችን ወጣቶች ተስፋ እንዳንቆርጥ ያደረገ ስለነበር፣ ከፉ አይንካህዘ፣ እደግ፣ ተመንደግ እንላለን።

የአመራርን ተዓማኒነት መሸርሸር

የመረጃ ጦርነት የሚጀምረው ዒላማ በተደረገው መሪ ላይ አሉታዊ አውድ በመፍጠር ነው። ፕሮግራሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን እንደ አከራካሪ እና ከፋፋይ የፖለቲካ ሰው አድርጎ ያቀርባል። አስተናጋጁ፣ የዐቢይ ተቺዎች እንደ “አምባገነን” (tyrant) እና “ኢትዮጵያን የሚበትን” (dismembering Ethiopia) አድርገው እንደሚፈርጁ ማጉላቱ፣ የፕሮግራሙን ዋና አንኳር መልዕክት ያስቀምጣል። ይህ ስልት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስብዕና በዓለም አቀፍ ደረጃ የማጥቃት እና የኢትዮጵያን መንግሥት አመራር እምነት የማይጣልበት አስተማማኝ አለመሆኑን የማሳየት ዓላማ አለው። በተጨማሪም፣ መንግሥት “የሰብዓዊ መብቶች መሸርሸር”፣ “የጋዜጠኞች እስር” እና “የኢኮኖሚ ውድቀት እያስተናገደ ነው” የሚሉ ትርክቶች ላይ ብቻ ትኩረት መስጠቱ፣ የዐቢይ አስተዳደር በሀገር ውስጥ ጉዳዮች ላይ የተሳካ እንዳልሆነ በማሳየት የሀገሪቱን ገጽታ ያበላሻል። የጥቃቱ ተባባሪና አጃቢ የሆነችው “ጋዜጠኛ” ፀዳለ ለማም ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሰላምን ለማስፈን ቃል ገብተው አገሪቱን እንደበታተኑ” አስመስላ በተደጋጋሚ አስተያየት መስጠቷ፣ ይህንን አሉታዊ ትረካ ያጠናክረዋል።

ያለፉ ግጭቶችን በመጠቀም ጥምረቱን ማክሰም

የመረጃ ጦርነት ሌላው ዘዴ የተቃራኒ ወገኖችን የቅርብ ጊዜ ጥምረት በመጠቀም ሁለቱም አካላት ታማኝ እንዳልሆኑ ማሳየት ነው። ጋዜጠኛ መሃዲ ሃሰን ጌታቸው ረዳ በጦርነቱ ወቅት ሲጠቅሳቸው የነበሩ ከባድ ክሶችን (ዐቢይን የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጻሚ፣ ጨካኝ ብሎ መጥራትን) ደጋግሞ በማንሳት፣ አሁን ከዐቢይ ጋር መስራታቸው “የሞራል ውድቀት” እና “ክህደት” መሆኑን አጉልቶ ይሞግታል። ጌታቸው ረዳ ኩራታቸውን ዋጥ አድርገው ለህዝብ ጥቅም እየሰሩ መሆናቸውን ቢያብራሩም፣ መሃዲ ግን “ዓለምን የሚመለከቱበትን አመለካከት ቀይረዋል” በማለት የትግራይን ህዝብ በመክዳት የፖለቲካ ታማኝነት የጎደላቸው መሆናቸውን ለማሳየት ይሞክራል። ይህ ስልት ሁለቱንም መሪዎች በማጋለጥ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት አመራር በመርህ ሳይሆን በግል ፍላጎት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ለዓለም አቀፉ ተመልካች ለማሳየት ይጠራል። ይህም በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የተፈጠረውን መተማመን በመሸርሸር ኢትዮጵያ በውጭ ኃይሎች በቀላሉ ተጽዕኖ የምትወድቅ ደካማ ሃገር እንደሆነች ለማሳየት ሞክሯል።

የፍትህ እና የተጠያቂነት እጦትን ማጉላት

የመንግሥትን ስም የማጥፋት ስልት በጦርነቱ ሰለባዎች ላይ ፍትህ አለመገኘቱን በማጉላት ይተገበራል። በውይይቱ እንደተገለጸው፣ የሽግግር ፍትህ ስምምነት ከተፈረመ ከሶስት ዓመታት በኋላ፣ ዋና ዋና ተዋናዮች ለጦር ወንጀሎች “ተጠያቂ አልተደረጉም”። ተጋባዥ ፓናሊስት የነበረው ሮርዌጂያኑ አፍቃሬ ትህነግ የሆነው ሼቴል ትሮንቮልም መንግሥት “ለጅምላ ግፎች ተጠያቂነትን እያቀረበ ስለመሆኑ ምንም ዓይነት ማስረጃ የለም” በማለት የሽግግር ፍትህ ማዕቀፉ ግለሰቦችን ተጠያቂ ከማድረግ ይልቅ  መንግሥት “ትኩረትን ወደ ሌላ እያዞረ ነው” ብሏል። ይህ ትረካ ኢትዮጵያ የህግ የበላይነት የሌለባት እና የዜጎችን መብት የማታስከብር ሀገር መሆኗን በማሳየት፣ ለዓለም አቀፍ ተቋማት ጣልቃ ገብነት ወይም ለውጭ ተጽዕኖ ክፍት እንድትሆን ያደርጋል።

የጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶችን ማባባስ

ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ እና በጎረቤት ኤርትራ መካከል ስላለው ሊፈጠር ስለሚችል ጦርነት በመወያየት ውጥረቱን ያጠናክራል። አስተናጋጁ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን የባህር በር ፍላጎት (“የታሪክ ስህተትን ለማስተካከል”) እና የኢትዮጵያ ሠራዊት “ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል” መዘጋጀቱን በመጥቀስ ጦርነት ሊነሳ እንደሚችል ፍንጭ ይሰጣል። ፕሮፌሰር ሼቴል ትሮንቮልም ጦርነቱ “በቅርብ ጊዜ ይመጣል” (coming pretty soon) የሚል ትንበያ መስጠታቸው፣ የኢትዮጵያን መንግሥት እንደ ጠበኛ እና ስልጣን አስፋፊ በማቅረብ (Expansionism) የጂኦፖለቲካዊ ስጋት መፍጠር ላይ ትኩረት ያደርጋል። ይህ ደግሞ ቀጣናውን ወደ ከፋ ቀውስ ሊመራ የሚችል ሃሳብ በመሆኑ፣ የመረጃ ጦርነት ስልት አካል ነው።

የጥቃቱ ጠቅላላ አሉታዊ አንድምታ

በአጠቃላይ በዚህ የመሃዲ ሃሰን “ፊት ለፊት” የተሰኘ የሙግት ይዘት ያለው ፕሮግራም ጌታቸው ረዳ እንግዳ አድርጎ የተሰራውና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተመልካችና አድማጭ የቀረበው ፕሮግራም የኢትዮጵያን መንግሥት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ኢላማ ያደረገ የማጠልሸት፣ የማጣጣል፣ የመወንጀልና ስም ማጥፋትን ግቡ ያደረገ የመረጃ ጦርነት ጥቃት እንደሆነ መረዳት ይገባል። ጥቃቱ ኢትዮጵያ በቡድን 20 ሃገራት ጉባኤ በመሳተፍ እና የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ስብሰባ (COP32) ለማስተናገድ በመመረጥ ያገኘቸውን መልካም ስም፣ ተደማጭነት እና የአፍሪካ ድምፅና መሪ መሆኗን ለማደብዘዝ፣ እያንሰራራ ያለውን የቱሪስት ፍሰት ለማስተጓጎል፤ “ጋዜጠኞች” እና የፓርላማ አባላት የሚታሰሩባት ሀገር ናት በሚል እንደምታ መጪውን ምርጫ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ነጻ አይደለም በሚል ተዓማኒነት ከወዲሁ ለማሳጣት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ትኩረት ለማስቀየር፣ መተማመንና አንድነትን ለመሸርሸር ሆን ተብሎ ታቅዶና ተቀናጅቶ የተፈፀመ ከመሆኑም በላይ በአለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ አሉታዊ ገጽታ በመፍጠር ሌሎች ሃገራት ኢትዮጵያን ለወዳጅነትና ትብበር እንዳይመርጧት በማድረግ የሃራችንን የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የፋይናንስ እንቅስቃሴ የሚገዳደር ስትራቴጂያዊ የፖለቲካ ስጋት (Strategic Political Risk) በመፍጠር ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች እና አበዳሪዎች ኢትዮጵያን እንደ አደገኛ ገበያ እንዲፈርጇት፤ የኢኮኖሚው እንቅስቃሴ በእጅጉ እንዲዳከም፤ በውጤቱም የኑሮ ውድነት እየተባባሰ እንዲሄድና ያንን ተከትሎም በአንዳንድ ሐገራት በቅርቡ እንደታየው ዓይነት ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዲነሳ ለማድረግ ታቅዶ፣ ታስቦ፣ በጀት ተመድቦለትና በርካታ ገንዘብ ፈስሶበት የተደረገ ተዋናዮቹም ፊት ለፊት ከቀረቡት “ተላላኪዎች” ይልቅ ዓላማ ያላቸው ላኪዎች ያሉበት መሆኑን ያሳየ፤ በኢትዮጵያ ላይ ከታቀደው ሀገር የማፍረስ ዕቅድ አንዱ አካል የሆነ የመረጃ ጦርነት ዝግጅት ነው።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር እስከዳር አመጽ ለማቀጣጠል በተጠራው ስብሰባ “አስቻይ ሁኔታ የለም ተባለ” ጃዋር በድጋሚ አፈገፈገ

"በዋሽንግቶን ዲሲና ሎንዶን አገር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ...

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...