ዶክተር ተከስተ በአሜሪካ ለስደተኝነት የሚበቃቸውን ሂደት እያከናወኑ ነው

Date:

የትህነግ ከፍተኛ አመራር አብርሃም ተከስተ በአሜሪካ አገር ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚያችላቸውን ሒደት መጀመራቸው ተሰማ። ጥረገኝነት ለማግኘት የሚያችላቸው ሰነድ እንዲያሟሉና ቃለመጠይቅ እንዲያደርጉ ለቅዳሜ ጥቅምት 1፤ 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞላቸው እንደነበር የጀመሩትን ሂደት ከሚያሳየው መረጃ ለመረዳት ትችሏል።

ዶክተር አብርሃም ተከስተ በአሜሪካ ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚያስችል ሰነድ እንዲያዘጋጁ መልእክት እንደተላከላቸውና እና ቀደም ሲል የጀመሩት ሒደት መሰረት በአሜሪካ የሕክምና ማእከል ለ( American Medical Center) ሰነዶች ማስገባታቸው ታውቋል።

ዶክተር አብርሃም ተከስተ በትህነግ ከፍተኛ አመራር መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ባለፉት ዓመታት ተካሂዶ በነበረው ጦርነት ሰራዊት ከመሩት አመራሮች መካከል አንዱ እንደነበር የሚታወቅ ነው። እሳቸውን ጨምሮ የትህነግ አመራሮች በመሩት በዚሁ ጦርነት አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች ሕይወታቸው እንዳለፈ፣ በርካቶች አካላቸው እንደጎደለና በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ንብረት እንደወደመ የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በይፋ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

መንግስት “የህልውና ጦርነት” በሚል ባካሄደው ዘመቻ የቀድሞውን የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩትን ዶክተር አብርሃም ተከስተን ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር ከመሸጉበት ተይዘው ጥር 03 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ መግባታቸው አይዘነጋም።

የአሜሪካ መንግስት በጦርነቱ ተሳታፊ የነበሩ አመራሮች ከአገር እንዳይወጡ ክልከላ ጥሎ የነበረ ቢሆንም ያገኘነው መረጃ እንሚያመለክተው ዶክተር አብርሃም ተከስተ ጥገኝነት ለማግኘት የሚያስችለው ሒደት ጀምረዋል።

የትህነግ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር በተፈጠረው አለመግባባት ወደ ትግራይ ካቀኑት መካከል አንዱ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ሚልየኖች ሕይወት በቀጠፈው ጦርነት እጃቸው ካለበት አመራሮች ስሙ ተያይዞ ይነሳል።

አሁን ላይ በተገኘው መረጃ መሰረት ጥገኝነት ለማግኘት የሚያስችል ክትትል (Asylum Follow-to-Join) እያዘጋጀ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። 

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የዓለም የነዳጅ ቀውስ እና የኢትዮጵያ ፈተና [ታሪካዊ አርበኝነት ጥሪ] ወቅቱን ለሚመረምሩ ሁሉ

ኢትዮጵያን እንወዳለን፣ ኢትዮጵያ አገሬ ናት፣ ኢትዮጵያ እናቴ ናት፣ ሌላ...

ወሳኙ የአደዋ ድል ሚስጢር – የአፄ ምኒልክ አዋጅ

ይህ ማህበራዊ ውል መላውን ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር አስተሳስሯል።...

“አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ – ኢህአፓ አሳማነቷን በሊፒስቲክ ልትደብቅ?

በ1980ዎቹ ነበር፤ በዘመኑ ቀልድ የሚያበዛ ታዋቂ ጋዜጠኛ በአንድ የታወቀ...

ጃዋር መሐመድ የአመጽ ጥሪውን የሰረዘው ለአስቸኳይ ስራ ግብጽ ተልኮ መሆኑ ታወቀ

አዲስ ሪፖርተር - ባለፈው ማክሰኞ በኢትዮጵያ ሕዝብ አመጽ እንዲያቀጣጥል...