ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ” የምናደርገውና ልናደርግ ያሰበነው የሚገባቸው ጠላቶቻችን ናቸው” ያሉት ገና ወደ መሪነት መንበር እንደመጡ ነበር። አሁን ላይ ያለው ኢትዮጵያን የማዛልና በጦርነት የማዳከሙ ርብርብ ከዚህ የኢትዮጵያን መዳረሻ ከማወቅ የተነሳ እንደሆነ እየተገለጸ ነው። ለዚህም ይመስላል ዛሬም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለነዚህ ወገኖች “ሕልማችንን አናሰርቅም” ሲሉ መልዕክት ያስተላለፉት፡፡
“ህልማችንን አናሰርቅም” አሉ አብይ አሕመድ ተሳፋሪ እንዳሻው የሚያዘውንና የሚያሽከረክረውን የላዳ ታክሲ ሾፌር ግብር በማንሳት፡፡ ሰውየው የአውቶብስን የስራ ባህሪ አስከተሉ። አውቶቡስ ማንም “እዚህ ዙር፣ እዚህ ቁም” እንደማይለው፣ መነሻውን፣ መቆሚያውን/ ፌርማታውን፣ መድረሻውንና መዞሮሪያውን በማንም ትዕዛዝ እንደማይቀያይር አመለከቱ። ከተል አድርገው ኢትዮጵያ እንደ ላዳ ሾፌር እንደማትመራ አስታወቁ። ኢትዮጵያ የምትመራው እንደ አብውቶቡሱ ሾፌር መሆኑን አመለከቱ። መነሻዋን፣ መቆሚያዋንና መዳረሻዋን የምታውቅ አገር መሆኗን አስረገጡ።
“ሕልም አለን” በሚል መርሃቸው የሚታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፣ የላዳውንና የአውቶቡስን የስራ መለያየት አስረድተው ኢትዮጵያን ማንም “እዚህ ቁሚ፣ እዚህ ታጠፊ” እንደማይላት ገልጸው ሲያሳርጉ “ሕልማችንን አናሰርቅም” ነው ያሉት።
“ሕልማችን የኢትዮጵያን ብልጽግና ተግባራዊ ማድረግ ነው፣ ግራ ቀኝ አንልም” ያሉት አብይ አህመድ ኢትዮጵያ በ2032 ከአፍሪካ ሁለተኛ ፣ በ2036 አንደኛ በመሆን በኢኮኖሚ አናት ላይ እንደምትቀመጥ አስታውቀዋል። ይህ ሲሉ ” ማንም ይህን ከማሳካት አያስቆመንም” በሚል የመሪ ጀዝም ነው፤ አክለው ግን “በጋራ እንስራ” ሲሉ አሳስበዋል። ተጣርተዋል። በ”ታማኝ” ገብር ከፋዮች ፊት ያሉትን ደግመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በሰጡጡበት ወቅት ነው፣ ተመዘገበ ያሉትንና በድፍረት ኢትዮጵያ በ2036 ከአፍሪካ በኢኮኖሚ መሪ እንድትሆን ያስታወቁት በአሃዝ የተደገፉ፣ በጊዜ የተቀመጡ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን በመዘርዘር ነበር።
ዛሬ በኢትዮጵያ ያልተለመዱ ዜናዎች መስማት እየተለመደ ነው። ስለ ሶፍ ኦማር ዋሻ ሲናገሩ “እንዲሁ ማራከስ ልማድ ሆኖብን እንጂ” እንዳሉት አሁን አሁን በኢትዮጵያ የሚሰሙት ዜናዎች ዓይኑን ለገለጠ፣ ማሽተት ለቻለ የማደጓ ጉዳይ ሊሸፈን የሚችል እንዳልሆነ አስታውቀዋል።
ከአባይ ግድብ ምርቃት በሁዋላ ብቻ እንኳን የተሰሙት የፕሮጀክት ዝርዝሮች ኢትዮጵያ የቀደመ ታሪኳን የምታክምበት፣ በልመና የቆሸሸ ስሟን ዳግም የምታድስበት እንደሆነ አካሄዱ የገባቸው እየተናገሩ ነው። በዚያው መጠን የሚያራክሱም አሉ።
የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አየር ማረፊያ፣ የነዳጅ ድፍድፍ ማጣሪያ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ምርት፣ የተደራራቢ ግድቦች ስራ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ወደ ቀይ ባህር የተጀመረው ጉዞ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ምን እየሆነ ነው የሚያሰኝ እንደሆነ በርካቶች በገሃድ እየተናገሩ ነው።
26500 ኮሎሜትር የሚያካልል 346 የመንገድ ፕሮጀክቶችን በ1።5 ትሪሊዮን ብር፣ 1.4 ቢሊዮን ዶላርና፣ በ5 ቢሊዮን ኢዩሮ የግድብ ስራ እያከናወነች ያለችው ኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካዋን በሃያ አራት ወር ስታስመርቅ የግብርና ምርቷ አሁን ካለው በሁለት ዕጥፍ እንደሚያድግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል። ይህ ሁሉ አንድ ላይ ሲሳለጥ ኢትዮጵያ “ሰላሟ እንጂ” የሚል ቁጭት ያስነሳል።
“ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዝ፣ ማዳበሪያ፣ አውሮፕላን ማረፊያና ቤቶች ልማት ላይ የምንሰራው ስራ ጨዋታ ቀያሪ ነው። የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ ይቻላል። ይህም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ትልቅ እጥፋት ነው። ሌሎችም ሲጠናቀቁ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ይመጣል” ያሉት አብይ አሕመድ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም እንዳይሰፍን የሚደረገውን ርብርብም ጠቁመዋል።
“የኢትዮጵያን እድገት የማይሹ ሀገራት በጦርነት እንደማያሸንፉን ያውቁታል። ያላቸው ምርጫ ባንዳዎችን መላክ ነው። ኢትዮጵያን በቅጡ ያላወቁ የውስጥ ባንዳዎች ደግሞ ከጠላት ጋር በማበር ዓላማቸውን የሚያሳኩ ይመስላቸዋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ ፈጽሞ ሊሳካ የሚችል ሙከራ እንደሆነ አመልክተዋል።
“ይልቁኑም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስፈልገው ብቸኛው መንገድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ነው” በማለት “መንግስት ችግሮች አሉኝ ከሚሉ አካላት ጋር ቁጭ ብሎ በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም በሩ ክፍት ነው” ብለዋል።
የሰላምን አስፈላጊነት በጥልቅ እንደሚረዱ ያመለከቱት አብይ አሕመድ መንግስትና ፓርቲያቸው በተደጋጋሚ ለድርድ ዝግጁ መሆናቸውን ቢያስታውቁም ጠብ መንጃ ያነሱ ኃይሎች በውል በማያስቀምጡት ነጥብ ለመንግስትና ለክልሎች የሰላም ጥሪና የድርድር ግብዣ የተጠበቀውን ያህል ምላሽ አለመስጠታቸው በርካቶችን የሚያነጋግር ጉዳይ ነው።
ለድርድ ቁጭ ብለው ጥያቄያቸውን በማቅርበ መንግስት የማይቀበል ከሆነ ማሳወቅ እንደሚገባቸው የሚገልጹ ወገኖች ጠመንጃ ያነሱ ኃይሎች ደፍረው ወደ ንግግር እነዲመጡ ይጠይቃሉ። በተለይም በአማራ ክልል ከትምህርት ገባታቸው የተፈናቀሉ፣ ያመረቱትን ወስደው መሸጥና መለወጥ ያልቻሉ፣ ሕክምና የተጓደለባቸው፣ ትራንስፖርት የተዛነፈባቸው፣ ዝርፊያና ግብር ክፈሉ ያማረራቸው ዜጎች የሰላም ያለህ ማለታቸውን የሚያስታውሱ መንግስትም ከልቡ ብዙ ረቅት እንዲሄድ፣ ታጣቂዎቹም ከውጭ የሚወራውንና የሚላክላቸውን አጀንዳ ወደሁዋላ በመተው ለንግግር እንዲቀመጡ ይወተውታሉ። ሕጻናት በተለየ “እንማር” በሚል ጥሪ እያሰሙ ነው።





