ደሳለኝ ጫኔ ተጨማሪ ግድብ እንዲሰራ ጠየቁ፣ አሰብን አስመልክቶ ከኤርትራ ጋር ተመሳሳይ አቋም ይዘዋል

Date:

ራሳቸውን ከፍረጃ በመከላከል ንግግር ያደረጉት የፓርልማ አባል ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ የአባይን ግድብ መመርቅ አድነቀዋል። ማድነቅ ብቻ ሳይሆን መደሰታቸውን አመልክተዋል። በዛው አስታከው ተጨማሪ እንዲሰሩ ከተያዙት ግድቦች መካከል ሁለተኛው እንዲጀመር ጠይቀዋል።

በማመስገን የተንደረደሩት ዶክተር ደሳለኝ፣ የአሰብን ወደብ አስመልክቶ ግን በውጭ አገር ያሉ ተቃዋሚዎችና የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናትና በነሱ የሚደገፉ ሚዲያዎች የሚሉትን በመድገም ነበር አስተያየታቸውን የጀመሩት።

“መንግሥት የባህር በር የማግኘት አጀንዳን የህልውና ጉዳይ አድርጎታል” በሚል የሚሰሙ አስተያየቶችን እንደሚያደምጡ አስታወቀ፣ “መንግሥት ዋና ትኩረቱንና የፖለቲካ ጉልበቱን አጣዳፊ የውስጥ ቀውሶችን ከመፍታት ይልቅ በውጭ ጉዳዮች ላይ መጠመዱንና፣ የሕዝቡን ትኩረትና የውስጥ ችግሮች ወደ ውጭ ለመቀልበስ እየሠራ ነው” ያሉት ዶክተር ደሳለኝ፣ መንግስት ሞክሮ ያልተሳካለት ያሉዋቸውን የባህር በር ስምምነቶች አንስተዋል።

ከኤርትራ፣ ከሶማሊላንድ፣ ከጅቡቲ ታጁራ ወደብን፣ ከጠቃቀሱ በሁውላ እንዳልተሳካ አመልክተው በቱርክ መንግስት አማካይነት ከሶማሊያ ጋርም የተጀመረው ንግግር በተመሳሳይ ባለመሳከቱ አገሪቱ በጦርነት ዋዜማ ላይ እንደምትገኝ አመልክተዋል።

የአሰብ ወደብ አጀንዳ ሌሎች ጉዳዮችን ለማስቀየስ የሚደረግ ቅስቀሳ መሆኑን ያመለከቱት የፓርላማ አባሉ፣ ሕዝብ ጦርነት ስላንገሸገሸው መንግስት ከኤርትራ ጋር እንዲስማማ ጠይቀዋል። አክለውም መንግስት “ጽንፈኛ” እና “አሸባሪ” እያለ ከሚጠራቸውን ታጣቂዎች ጋር ከወታደራዊ አማራጭ ይልቅ ወደ ፖለቲካ መፍትሔ እንዲያተኩር መክረዋል። ይህን ሲሉ የታጠቁት ኃይሎችም ጠመንጃ አውረደው ወደ ሰላም እንዲመጡ አልጠየቁም።

ይህን ተከትሎ “አባሉ የጥላትን የፕሮፓጋንዳ ፍሬ ነጥብ (talking point) እንደራሳቸው በመውሰድ እና በፓርላማ ውስጥ በማስተጋባት ከሃገራቸው ብሄራዊ ጥቅም በተቃራኒ ከመቆማቸው ባለፈ አማራ እና ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያሉ የሽምቅ ተዋጊዎች መሳሪያቸውን ጥለው መንግስት ጋር በመደራደር እርቀ ሰላም እንዲያወርዱ ጥሪ ሲያቀርቡ አይስተዋልም። ይህ አግባብ አይደለም። አንዱን አትዋጋ ሌላውን ተዋጋ እንደማለት ነው” የሚል አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል።

አቋማቸውን የተረዳ አስተያየት ሰጪ “የሠላም ሚንስቴር የሰላም ኮሚቴ ግብረ ሃይል በማቋቋምና የተከበሩ አቶ ደሳለኝን የኮሚቴው ሰብሳቢ በማድረግ ወደ አማራ ክልል በመላክ የመንግስት የሳላም ጥሪ ጥረት አካል ይሁኑ” በማለት ማሳሰቡን አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድም አስተያየታቸው ገንቢ ብለው ከተቀበሉ በሁዋላ የአሰብ ወደን አስመልክቶ ስለሰጡት አስተያየት ሲለምልሱ ዶክተር ደሳለኝ የሰጡት አስተያየት የኤርትራ ባለስልታኖችና ተከታዮቻቸው ከሚሰጡት ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን አመልክተዋል። አያይዘውም አስገራሚው ጉዳይ “በየት በኩል ዞሮ እዚህ መጣ የሚለው ነው” ሲሉ አቋቋማቸውን የፈተሸ ምላሽ ሰጥተዋቸዋል።

የኤርትራ ባለስልጣናት፣ የኤርትራ አክቲቪስቶችና በኤርትራ መንግስት እንደሚደገፉ የሚነገርባቸው “ኢትዮጵያዊ የማህበራዊ ሚዲያ ጋዜጠኞች” በተመሳሳይ መንግስት አሰብን ለውስጥ ችግር መቀልበሻነት እንደሚጠቀም ዛሬ ድረስ ይናገራሉ።

ለዚህ ነው መስለ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለዚህ ተደጋጋሚና ወጥ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ጠቅልለው ጉዳዩን ከስር ለማስረዳት መርጠዋል። ሲያብራሩም ከዚህ በፊት በተለያዩ አጋብቦች ሲሰሙ የነበሩ ጉዳዮችን ከስር መሰረቱ አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ሰላም ሲፈጠር መጀመሪያ ወደ አስመራ መጓዛቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ፣ በተመሳሳይ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያ ሲመጡ የመጀመሪያውን መድረክ ሚሊኒየም አዳራሽ እንደነበር አስታውሰዋል። ብዙ ህዝብ ባለበት በቀጥታ ስርጭት የተላለፈ ዝግጅት እንደነበር አስታውሰው “ካላያችሁት አሁን ዩትዩብ ላይ ግቡና ስሙት/ እዩት” ካሉ በሁዋላ የመጀመሪያው ስብሰባ ላይ የመጀመሪያ ጉዳይ የሆነው የአሰብ ጉዳይ እንደነበር አስታውቀዋል። ይህም የሆነው ለህዝብ በሚገባው ልክ እንደነበርም ጠቁመዋል።

“ኤርትራ ስመላለስ አስመራን ካየው በኋላ ከክቡር ፕሬዚዳንቱ ጋራ አሰብ መሄድ እፈልጋለሁ ብዬ አሰብ ሄጄ ባህሩ ጋር ቆመን ያወራነው ነገር ምንድነው? ስለ ወደብ ነው። ካልሰማችሁ ዩቲኡብ ላይ አለ እዩ። የት ? ኤርትራ ምድር ውስጥ።” በማለት አዲስ አሳብ እንደሆነ አንስተው ለሚናገሩ ምላሽ ሰጥተዋል።

“የመደመር ትውልድ መፅሀፍ ውስጥ በግልጽ ጂዮ ፖለቲክስን አስፍሬ የአሰብ ጉዳይን አስቀምጬ ለኤርትራ ባለስልጣናት በስጦታ ልኬላቸዋለሁ። ሚስጥር አይደለም። ያውቁታል። ለሁሉም በግል ሌኬላቸዋለሁ” ብለዋል።

የዛሬ 6 እና 5 ዓመት የባህር ኃይል መቋቋሙን አንስተው አጠገባቸው ያለውን ብርጭቆ በማንሳትና በማሳየት ባህር ኃይል ህየተቋቋመው “እዚህ ውስጥ (የብርጭቆ ውሃ ውስጥ) ልንዋኝ ነው ባህር ኃይል ያቋቋምነው ? ለምን ሰዎች ይሄን ደምረው ማየት እንደሚቸገሩ አይገበኝም” ሲሉ በጋለ ስሜት ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ቀይ ባህር እንደሚያስፈልጋት ከለውጡ በፊትም እንናገር ነበር ያኔ መደመጥ አንችልም ነበር። ወደ ስልታን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ንግግሩ እንዳለ አመልክተው በሰላማዊ መንገድ መሆን እንዳለበት አስታውቀዋል።

ይህን ካስረዱ በሁዋላ “የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ እንዳነሱት ከኤርትራ መንግሥት ጋር ተስማምተን ከዚህ ወደ አሰብ የሚወስደውን መንገድ ጠግነናል። ከጠገንን በኃላ ችግር አለብን ፖርቱ ተዳክሟል አሉን። አንዳንድ ሰው ፀቡ በአንድ ምሽት የመጣ ይመስለዋል እንደዛ አይደለም ታሪኩ ስለማንናገር ነው” በሚል ከኤርትራ በኩል ሲሰጡ የነበሩትን ግብረ መልሶች ገልጸዋል።

“ወደ አሰብ መንገድ ጠግነን ከጨረስን በኃላ ፖርቱ ችግር አለበት ሲሉ የጋራ ወዳጅ የሆነ ሀገር ለምንነን ጀነሬተር እና ክሬን በእርዳታ ወደ ኤርትራ እንዲመጣ አድርገን አሰብ ወደብ ሲደርስ የኤርትራ መንግስት አልፈልግም ብሎ መለሰ። ያኔ ነው ይሄ ነገር ተስፋ የለውም የሚለው የገባን” በማለት መንግስታቸው የሄድበትን ርቀት አመላክተዋል።

“መንገድ ጠገንን፣ ለምንነን ክሬን ብናመጣም ፍላጎት አልነበረም። ልክ እንደ ሱዳን ፣ ልክ እንደ ጅቡቲ በኛ ወጪ የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ኤርትራ ቀጥለን ኃይል እንስጣችሁ ጀነሬተር አትጠቀሙ ብንልም ቆይ እናስብበት ነው የተባለው” ሲሉ የአሰብን ጉዳይ ለማሳካት የተሞከሩትን መነገዶች አስረድተዋል።

የአሰብ ጉብኘታቸውን ሲያስረዱ፣ ” አሰብ ቤት አለ፣ በር አለው፣ ሰው የለም፤ ይሄ እውነተኛ ታሪክ ነው” በማለት አሰብ ኦና መሆኗን ጠቆሙ፤ አክለውም “ይሄን ከተማ መልሰን ህይወት እንስጠው፤ ስራ ነው ህይወት የሚያመጣለት፤ የሚል በየጊዜው ተነጋግረናል። ሁሉም የሚሄድ ልዑክ ተነጋግሮበታል” ሲሉ ውሃ ቢወቅጡት ዓይነት ንግግር መሆኑን አስታወቁ።

“በኤርትራ በኩል በግልጽ ባላወቅነው መንገድ ለዚያ ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ብዙ ዝግጁ አልነበሩም” ያሉት አብይ አሕመድ፣ እሱ ቀርቶ የከፈትናቸውን ድንበሮች በሰሜን በኩል ወዲያው ተዘጉ። የተዘጉት ሌሎች ችግር እንዳለእንኳ ሳይሰሙ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።

ይህንን ቢሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኤርትራን ህዝብ አሁንም ወንድም ህዝብ መሆኑን አስምረውበታል። ሕዝቡ ምስኪን ህዝብ ነው ፤ ሀገሩን ለቆ እየተሰደደ ያለ ህዝብ ነው፤ ከዚህ ህዝብ ጋር መስራት መተባበር ፍላጎታችን ነው፤ በፍጹም የውጊያ መሻት የለንም። በህጋዊ መንገድ እና በንግግር ሊፈታ ይችላል” ሲሉ ሕዝቡን አበረታተዋል።

ዶከተር ደሳለኝ ጫኔ ባነሱት “ተስማሙ” የሚለው ሃሳብ ላይ፣ “ለብዙ ሀገራት በተናጠል ተናግሪያለሁ። ምክር ቤት መስማት ከፈለገ ግን” ብለው ለአሜሪካ፣ ለቻይና ፣ለራሽያ፣ ለአውሮፓ ለአፍሪካ ህብረት መወትወታቸውን አስታውቀዋል።

ለሰማ የተኬደበትን ርቀት ካስታወቁ በሁዋላ፣ “በተከበረው ምክር ቤት ፊት መግለጽ የምፈልገው ነገር የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጠቃሚነት ጉዳይ አይቀሬ ነው” ሲሉ ቁርጥ ያለውን አስታወቅዋል። አክለውም “ቅድሚያ የምንሰጠው ሰላምና ንግግር ስለሆነ እባካችሁ ሸምግሉን እና መፍትሄ አምጡልን። ይኸው ጥያቄያችን” ሲሉ ውይይት በኢትዮጵያ በኩል የቀድሚያ ቅድሚያ መሆኑን አስታውቅዋል።

“አዎ እንሸመግልላችኋለን ፣ ሰላም ያስፈልጋል ‘ እያሉ ማዘናጋት ከሆነ ግን ብዙ የሚስኬድ አይመስለኝም። ይሄ እኔ ሰለፈለኩ እናተ ስለፈለጋችሁ አይደለም በተፈጥሮ ህግም አይሆንም። በአንድ ቀን እንመልሰውም በአንድ ቀን አላጣነውም። የተፈጥሮ ሂደቱን ተከትሎ ይሄዳል። ” ሲሉ የሰላም አግባቡ ከተሟጠጠ ሊሆን የሚችለውን አመላክተዋል።

በተጨማሪም “እኔ ልክ እንደባለፈው አስመራ የመሄድ ፍላጎት አለኝ ችግር የለብኝም። ምን ከሆነ ? ትርፍ ካለው ነው ትርፍ ከሌለው ጊዜ ማባከን ነው እኔ ባሌ የምመላለስበትን ጊዜ ዝም ብዬ አስመራ ልመላለስበት አልችልም ጊዜ የለኝም። ሥራ አለኝ” ሲሉ ተደምጠዋል።

“ጦርነት አንፈልግም የምንለው በምክንያት ነው። እኛ ማንም እንደሚያየው ብዙ የሚያጓጓ ፕሮጀክቶች አሉን። የ10 ቢሊዮን ብር [ዶላር] ኤርፖርት እንገነባለን፤ በ10 ቢሊዮን ዶላር ነዳጅ ማዳበሪያ እንገነባለን የብዙ ቢሊዮን ብር ቤቶች እንገነባለን፣ ኮሊደር እንገነባለን  ይሄ ሁሉ የሚያጓጓ ስራ እያለ ሰው ጦርነት ሊያስብ አይችልም” ሲሉ መንግስታቸው ትኩረቱ ልማት መሆኑን አስታውቀዋል።

ስለአስመራው መንግስት ሲያነሱ፣ “ጦርነት የሚያስብ ሥራ የሌለው ብቻ ነው። እኛ የሚያጓጓ የምንተጋለት፣ የምንለፋለት የልማት ሥራዎች አሉ ከማንም ጋር የመዋጋት ፍላጎት የለንም” የለንም ብለዋል።

“ውጊያው ከተነሳ” ግን አሉ አብይ፣ “ውጊያው ከተነሳ ውጤቱ ግልጽ ነው። ከዛ በኋላ እዬዬ አይሰራም። አሁን ነው አለመጀመር ” ሲሉ ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ በቂ ዝግጅት እንዳላት ይፋ ተናግረዋል።

ውጊያ ከተጀመረ እገሌ ወይም እገሌ እንደሚያግዝ ተስፋ ማድረግ ከዩክሬንና ፍልስጤም አለመማር መሆኑ አስረግጠው ያስታወቁት አብይ አሕመድ፣ የሚያወራው ወሬ ብቻ መሆኑ ገልጸው ” ማንም አይሞትልህም። ሞራል ይሰጥኻል እንጂ አይሞትልህም። መጨረሻ የምትሞተው አንተው ነህ አያዋጣም።” ሲሉ መክረዋል። እንረዳለን የሚሉት ግፋ ቢል ጥይት ያቀበሉ አክለሆነ በቀር ሌላ የሚያደርጉት ነገር እንደሌለም ገልጸዋል።

ስለሆነም “እኛ አንፈልግም ልማት ነው የምንፈልገው፤ ሰላም ነው የምንፈልገው፣ ከማንም ጋር ግጭት ለማድረግ ፍላጎት የለንም ከገባን ግን ግልጽ ነው ውጤቱ። አስተማማኝ አቅም ነው ያለን፤ ማንም አያቆመንም። ይሄ ግልጽ መሆን አለበት ማንም አያቆመንም። ወደዚያ እንዳንሄድ (በኃላፊነት) መስራት አስፈላጊ ይመስለኛል። ” ሲሉም ምክርና ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኃይሌ ገብረስላሴ “አረቄን እጠቀም ነበር” በማለቱ ዕግድ ተጣለበት፤ እግዱ ለዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ማህበራት ተበትኗል

አዲስ ሪፖርተር - አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አረቄን ከዶፒንግ ጋር...

“የኢትዮጵያዊያ መከራ የሆነውን ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያና ትግራይ ምድር መንቀል ዋና ዓላማችን ነው”

አዲስ ሪፖርተር - እስካሁን በመላው ኢትዮጵያ ለተፈጠሩ ምስቅልቅሎች፣ በትግራይ...

የአማራ ክልል የወሲባዊ ጥቃት አሳስቧል፤ “በማንና እንዴት ይፈጸማል? ለሚለው በጥናት የተረጋገጠ መረጃ የለም” ጤና ቢሮ  

አዲስ ሪፖርተር - በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ጦርነትና...

በሻዕቢያና ህወሃት መካከል አለመተማመኑ ሰፍቷል፤ የሚታወቁ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ከእነ ሞንጆሪኖ ቡድን እየወጡ ነው

ስጋት ትልቁ ምክንያት ነው። ሻዕቢያ በተግባር የተፈተሸ ከሃጂ በመሆኑ...