በአሪ ዞን  በመሬት መንሸራተት የተፈናቀሉ ዜጎች ” ችግር ላይ ናቸው” ሲል ወረዳው አስታወቀ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በመሬት መደርመስ አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎች ሲደረግላቸው የነበረው ድጋፍ በመቋረጡ፣ ተጠልለው ባሉበት በምግብ፣ በመጠጥና መጠለያ ችግር ላይ መሆናቸው ተመለከተ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ኮመር ቀበሌ ሐምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም በደረሰው የመሬት መደርመስ አደጋ 5 የአንድ ቤተሰብ አባላት ሕይወታቸውን ሲያጡ ከአንድ ሺሕ አራት መቶ በላይ ነዋሪዎች ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።

የወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ ግዛው ኃይሉ ለአዲስ ሪፖርተር እንደገለፁት፣ተፈናቃዮች በኃይማኖት ተቋማት ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ መሆናቸውንና ፤ከአደጋው ማግስት በተለያዩ አካላት የተወሰኑ ድጋፍ ከተደረገላቸው በኋላ አሁን ላይ የትኛውም አካል ድጋፍ ማድረግ ማቆሙን ነግረውናል።

በአደጋው ከቤት ንብረታቸው ከተፈናቀሉት ውስጥ ለወሊድ የተቃረቡ ፤ ነፍስ ጥሩ እናቶች ፣ ወላጆች ፣ ልጆች መኖራቸውን ያክላሉ።

ለተፈናቃይ ዜጎች የሚሆን በቂ የእህል፤መጠጥ  ፣መጠለያ ፤አልባሳት ፣የሕክምና መሰሪያዎች ፣መድኃኒቶች የአቅርቦት እጥረት ማጋጠሙን ገልፀዋል። የክልሉ እና የዞኑ መንግሥት በቂ የማይባል ድጋፍ እንዳደረጉ ጠቁመው ፤ፌድራል መንግሥት እስካሁን ምንም አይነት ድጋፍ አለማድረጉን ነግረውናል።በመጠባበቂያነት በመጋዘኖች ውስጥ የነበሩ እህል ነክ እና የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች እያለቁ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

በተጠቀሱ ምክንያቶች ዜጎች ለከፋ ችግር እንደተጋለጡ ይናገራሉ።አስተዳዳሪው በተጨማሪም ፤የፌድራል ፣የክልል ፣የዞን መንግሥታት እንዲሁም ሌሎች ተራድኦ ድርጅቶች ፣ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ለተፈናቃዮች የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር እስከዳር አመጽ ለማቀጣጠል በተጠራው ስብሰባ “አስቻይ ሁኔታ የለም ተባለ” ጃዋር በድጋሚ አፈገፈገ

"በዋሽንግቶን ዲሲና ሎንዶን አገር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ...

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...