የ – አብሮነት የህቡዕ ስራ አስፈጻሚ ይፋ ሆነ፤ የአብሮነትን የሚውጥ ሌላ የህቡዕ ድርጅት ተመሰረተ – ሪፖርት ከዲሲ

Date:

ከምርጫው በሁዋላ የሕዝብ ግንኙነት ሆነው የተመረጡት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል “የገባነው ልናፈርሰው ነው፤ እነዚህ አይታመኑም። የሌሎችን ብሄሮች ስብጥርና ማንነት በእኩል አይቀበሉም፣ እኛ ያቋቋምነው አዲስ ድርጅት አለ። የሚፈለጉትን መርጠን እንወስዳቸዋለን” ብለዋል። ፕሮእፌሰሩ በምስራቅ ኢትዮጵያ የኦብነግን አፍንጋጭ ቡድን ከኦነሠ ጋር እንዲያስተባበሩ መሾማቸው እየታወቀ “በሰላማዊ ትግል ለመታገል ተቋቋምኩ” በሚለው የአቶ ልደቱ ማህበር ውስጥ የሕዝብ ግንኙነቱን ስራ እንዲሰሩ መመረጣቸው አስገራሚ መሆኑን ከተሰብሳቢዎቹ መካከል ለአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ ነገረዋል።

አዲስ ሪፖርተር – በሰላማዊ ትግል መንግስት ለመጣል ማቀዱን አስታውቆ ሃያ አንድ ቦርድ አባላትን ሰይሞ የሰነበተው የአብሮነት ማህበር ሰባት ስራ አስፈጻሚዎችን መምረጡ ታወቀ። ማህበሩ “ለቦርድ አባላት” በሚል ባሰራጨው የ” እንኳን አደረሳችሁ” መልዕክት አቶ ልደቱ፣ ከአማራ የመሰረቱት ማህበር ፕሬዚዳንት ሆነዋል። መቅደስ አዳነ ከወላይታ፣ አሸናፊ አብርሃም ጽሐፊ ከደቡብ፣ ገንዘብ ያዥ ከአማራ ሙሉጌታ ዘለቀ፣ የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ / በተለይ እንግሊዘኛና ትግርኛ ጠንቀቀው ስለሚያውቁ/ ከኦሮሞ ፣ የድርጅት አስተባባሪ ኢሳሜል ጎርሴ ከሶማሌ፣ የውጭ ግንኙነት ኦፊሰር መስፍን ከትግራይ መመረጣቸው ይፋ አድርጓል።

ቀደም ሲል ምርጫው ከመደረጉ በፊት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባላቶች ህቡዕ እንደሚሆኑ ተመክቶ እንደነበር የስብሰባው ተሳታፊዎችን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። ያለፈው ሳምንት ባለመግባባት ምርጫው ሳይካሄድ ከቀር በሁዋላ ሃሳብ ተቀይሮ ህቡዕ እንዲሆኑ ተወስኖ የነበረው የስራ አስፈጻሚዎች ዝርዝር ታውቋል።

በተከታታይ ለዲሲ የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ መረጃ የሚሰጡት ወገኖች እንዳሉት ከሆነ ሰኞ ዕለት በተካሄደው ምርጫ ቀደም ሲል አቶ ልደቱ በግል እንዳይመረጥ ቅስቀውሳ ያደረጉበት የረዕዮት ሚዲያ ባለቤት ቴዎድሮስ ጸጋዬ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሳይሆን ቀርቷል። ቴዎድሮስ ባለፈው ሳምንት ባለመግባባት ምርጫ ማድረግ ሳይቻል በተበተነው ስብሰባ ላይ እጁን ሳያወጣ በተደጋጋሚ በመናገር ስብሰባውን በመበጥበጡ፣ ከሁሉም በላይ ግን ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ያላቸውን አጥብቆ ስለሚቃወም፣ በተቃራኒው ሻዕቢያን የሚቃወሙትን ስለሚደግፍ ነበር አቶ ልደቱ በግል ስልክ እይደወሉ ምርጫ ውስጥ እንዳይገባ የቀሰቀሱበት።

በስልክ አቶ ልደቱ ያላፈው ስብሰባ ከተበተነ በሁዋላ ቴዎድሮስ ስራ አስፈጻሚ ውስጥ እንዳይመረጥ ካነጋገሯቸው መካከል ሁለቱ ለአዲስ ሪፖርተር እንዳሉት ” ቴዎድሮስ ከሰማ የሚዲያ ዘመቻ ስለሚከፍትብን ሚስጢር ይሁን” ሲሉ አቶ ልደቱ ማናገራቸውን አመልክተዋል። አቶ ልደቱን በግል ስልካቸው በማግኘት ለማነጋገር ተባባሪያችን ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

  • ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ምርጫው እየተደረገ ሳለ ” diversity አትከተሉም” በማለት አስቀድመው ተቃውሞ አሰምተው እንደነበር የተናገሩት የመረጃው ባለቤቶች፣ ስብሰባው ካለቀ በሁዋላ እንደሰሙት ከሆነ መመረጣቸው ከተነገራቸው መካከል መልቀቂያ ያስገቡ አሉ።

ከአቶ ስብሃት ነጋና ከሻዕቢያ ሰዎች ጋር አብረው እንደሚሰሩ፣ በምስራቅ ኢትዮጵያ አቅጣጫ የተጀመሩ ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን ለማስተጓጎልና ጦርነቱን ለማስፋት በግብጽ መሾማቸው የተሰማባቸው ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል፣ ከሚቀርቧቸው ሰዎች ጋር ሆነው አብሮነት እንደሚፈርስ ስብሰባ በተደረገ በአንድ ቀን ውስጥ መናገራቸው ተሰምቷል።

” እኔና መስፍን አየነው የገባነው ስብስቡን ለማፍረስ ነው” በማለት ፕሮፌሰሩ መናገራቸውን የሰሙት እነ አቶ ስብሃት ነጋ የሚመሩትን ቡድን የሚቃወሙ ሌላኛው የትግራይ ቡድን ደጋፊዎች ሲሆኑ፣ ሕዝቅዔል ” አዲስ የተቋቋመ አደረጃጀት አለ። ከአብሮነት ውስጥ የሚፈለጉትን ወደዛ እንወስዳለን። የአብሮነት ነገር አይታመንም። የሌሎችን መብትና ስብጥር አያከብርም” ማለታቸው ታውቋል። እሳቸውንም በግል ስልካቸው ለማግኘት በተደጋጋሚ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም።

እነዚሁ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የመረጃ ምንጮች ለተባባሪያችን እንዳሉት ሕዝቅዔል አዲስ የተመሰረተ ያሉት አደረጃጀት እሳቸው ያሉበት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሓቅ ያደራጁትና እነ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ከሁዋላ የሚመሩት ነው።

ከሃያ አንዱ የቦርድ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ታምራት ላይኔ፣ አስቀድመው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ለመሆን ፈቃደኛ ሆነው የነበሩ ቢሆንም፣ በስለማዊና የትጥቅ ትግል ስልት ላይ ክርከር ከተካሄደ በሁዋላ በሰኞው ዕለት ምርጫ ርሳቸውን ከስራ አስፈጻሚነት ተወዳዳሪነት ማግለላቸውን በስብሰባው የተካፈሉ አስታወቀዋል።

አብሮነትን አብረው አጅበው የነበሩት እነ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ ኢተና ወዘተ የመሳሰሉት ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን ማግለላቸውን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። ይህም የሆነው በአገር ውስጥ የኦሮሞ ተወላጆች በሰንበዘሩባቸው ተቃውሞ መሆኑ አይዘነጋም።

ቡድኑ ስራ ሲጀምር በአገር ውስጥ የሕቡዕ አደረጃጀት በማስፋፋት የተቃውሞና አድማ እንደሚያደራጅ አቶ ልደቱ በተደጋጋሚ ማናገራቸው አይዘነጋም። አብሮነት ከአገር ውስጥ አብሮ ካሉ የተወሰኑ ድርጅቶች ጋር እንደሚሰራ፣ አንዳንዶቹም በጅምሩ ወቅት በይፋ በዙም ስብሰባ ይካፈሉ እንደበር የሚታወስ ነው።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related