ሰኞ , ታህሳስ 1, 2025

የዶክተር አንዷለም ገዳይ ሃያ ዓምስት ዓመት ተፈረደበት፤

Date:

አዲስ ሪፖርተር – “ዶ.ር አንዷለም በዩኒቨርሲቲያችን፣ ብሎም በአገራችን  አሉን ከምንላቸው በቁጥር ትንሽ የዘርፉ ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞቻችን ውስጥ አንዱ የነበሩ ሲሆን ከስራ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ በአጋጠማቸው ግድያ ህይወታቸውን አጥተዋል።  በሐኪማችን ላይ ያጋጠመውን ግድያ እና በተደጋጋሚ በዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ያልተገባ መሰል ድርጊት ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በጥብቅ ያወግዛል። በየትኛውም አካል ሊሰነዘር የሚችል ይሄን አይነት መሰል ድርጊትም ለአገርም ሆነ ለወገን አጉዳይ እንጅ አንዳች የሚጨምር ነገር እንደሌለ ሁሉም ሊገነዘበው የሚገባ ጉዳይ ነው” ሲል የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ሃዘኑን የገለጸላቸው ተወዳጅ በለሙያ ነበሩ 

በቅጥር ነበሰገዳይ መገደላቸው እንደተሰማ ከየአቅጣቻው በሰዎች ደም መነገድ የሚፈልጉና አሁን ድረስ የንጹሃንን ግድያ የግል ፖለቲካ መጠቀሚያ ማገዶ የሚያደርጉት ወገኖች ዜናውን የአመጽ ማቀጣጠያ ለማድረግ ታትረው ነበር። ሆኖም ኝ ዩኒቨርስቲው፣ ባልደረቦቻቸውና እማኞች በሰጡት ምስክርነት ነገሩ መስመሩን ሳይቀይር ገዳይ ተያዘ።   

የአማራ ክልል ሁከት ካጋጠመው ጀምሮ ሊረሱ የማይችሉ ልጆቹን አጥቷል። ክልሉን ከሚመሩት ከፈተኛ ባለስልጣናት ጀምሮ በሚታወቅ ደረጃ ሕይወታቸው የተቀጠፈው የአማራ ክልል ተወላጆች ግድያው የተፈጸመባቸው በራሳቸው ክልል፣ በራሳቸው ክልል ነዋሪዎች መሆኑ ሃዘኑን ከፍ እንደሚያደርገው በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል።   

በዚሁ አሳዛኝና ትርጉም አልባ ውሳኔ ሕይወታቸው ከተቀጠፉት መካከል በባህር ዳር ዩንቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስር በሚገኘው የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ አንዱ ናቸው። ያስተማራቸውን ሕዝብና አገር መጥቀም በሚችሉበት ዕድሚያቸው በድንገት በጥይት እሩምታ የተገደሉት ዶክተር አንዱዓለም ገዳይ ፍርድ ማግኘቱ ተዋቋል።   

ዶክተሩን መግደሉን በተረጋገጠበት ነብሰገዳይ ግለሰብ ላይ የ25 ዓመት ፅኑ እስራት መበየኑን የባሕርዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው ያስታወቀው።  

እሱባለው ነበረ የተባለው ግለሰብ ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 1:30 ገደማ በከተማው ሰባታሚት “ቆሼ” ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ዶክተሩ የግል መኪናቸውን እያሽከረከረ ሳለ ሁለት ግዜ በመተኮስ እንደገደላቸው፣ የወንጀሉን ፈፃሚ ለማግኘት በተቋቋመው ግብረሀይል በኩል በተገኘው መረጃና ማስረጃ መሰረት ውሳኔውን ማስተላለፉን ፍርድ ቤቱ ገልጿል።  

በዕለቱ ዶ/ር አንዱአለም ከፈለገ ህይወት ሆስፒታል ለታካሚዎቻቸው የቀዶ ህክምና አገልግሎት ሲሰጡ አምሽተው ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝ ሆስፒታል ወደ ሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እየሄዱ በነበሩበት ወቅት በሚያሽከረክሩት መኪና ላይ በቀኝ በኩል በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን በወቅቱ ፖሊስ መረጃውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።  

ፓሊስ በዚህ የምርመራ ሒደት ከክልሉ ፖሊስ ዋና መምሪያ እና ከከተማ አስተዳደሩ የምርመራ ቡድን ተዋቅሮ መረጃና ማስረጃዎችን በማሰባሰብ የወንጀሉን አፈፃፀምና ፈጻሚውን ማወቅ እንደተቻለ ይፋም አድርጎ ነበር።  

ፍርድ ቤቱም የቀረቡለትን የምርመራ ውጤቶች መሰረት በማድረግ  ወንጀሉን በፈጸመው ግለሰብ እሱባለው ነበረ ላይ የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ወስኖበታል።  

ዶክተሩ በተገደሉበት ምሽትም በተመሳሳይ በሌላ የሕክምና ዶክተር ላይ ጥይት በመተኮስ የመኪናውን አካል በመምታት የግድያ ወንጀል ሙከራ ስለመደረጉም ፍርድ ቤቱ አመልክቷል። በወቅቱ “ዶክተር አንዷለም ተተኩሶበት ተመትቶ የተገኘው መኪናው ውስጥ ነው ። አንድ ሀኪማችንም ተተኩሶበት መኪናው ሁለት፤ ሦስቴ ተመትቶታል” የጤና ኮሌጁ ሰራተኞች እማኝነታቸውን ገልጸዋል በሚል መዘገቡ ይታወሳል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
tiktalk – https://www.tiktok.com/@addisreporter3
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related