ሰኞ , ታህሳስ 1, 2025

የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ (AFRICOM) አዛዥ ጉብኝታቸው ኢትዮጵያና አሜሪካ በአፍሪቃ ቀንድ “የጋራ ስጋቶች” ስላሏቸው እንደሆነ አስታወቁ

Date:

አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በምሥራቅ አፍሪካ የባህር ዳርቻ ላይ እየጨመረ የመጣውን የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴ ለመዋጋት የሚደረገው የጋራ ጥረት ከመቼውም ጊዜ በላይ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ ሪፓርተር አዲስ አበባ፡- የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ (AFRICOM) አዛዥ ሆነው በፕሬዝዳንት ትራምፕ የተሾሙት ጄኔራል ዳግቪን  አር.ኤም. አንደርሰን  አዲስ አበባን ጎብኙ። በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳስታወቀው፣ የጉብኝቱ ዓላማ የአሜሪካ መንግሥት በአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ መረጋጋትን ለማረጋገጥ ያለውን ቁርጠኝነት ለማሳየት ነው። በቆይታቸው ጄኔራል አንደርሰን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት እና የጦር አመራሮች ጋር ወሳኝ ውይይቶችን አድርገዋል።

ኤምባሲው ባሰራጨው ቪዲዮ መሠረት ጄኔራል አንደርሰን ጉብኝታቸው የተመሰረተው   የጋራ ስጋቶች በመኖራቸው እንደሆነ ገልጸዋል። “ዛሬ እዚህ የመጣሁበት ዋነኛ ምክንያት የጋራ ስጋቶች ስላሉን ነው” ያሉት ጄኔራሉ፣ አሜሪካውያን አጋሮቻቸውን እነዚህን ስጋቶች በአንድነት ለመፍታት ለማብቃት መገኘታቸውን አስረድተዋል። በተለይም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ትኩረቱ ድንበር ተሻጋሪ ሽብርተኝነትን እንዴት መዋጋት እና ለቀጠናው መረጋጋት በጋራ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚቻል ላይ መወያየት ነበር። ጄኔራሉ አክለውም ኢትዮጵያ ለእነዚህ ሁለት የጋራ ጉዳዮች ወሳኝ ሀገር ናት  በማለት የኢትዮጵያን ቁልፍ ሚና አጉልተዋል።

በምሥራቅ አፍሪካ፣ በሳሄል እና በምዕራብ አፍሪካ የባህር ዳርቻ ክልሎች እየጨመረ የመጣውን የአሸባሪዎች እንቅስቃሴ ለመዋጋት የሚደረገው የጋራ ጥረት ከመቼውም ጊዜ በላይ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ጄኔራል አንደርሰን፣ ይህንን ውይይት ከኢትዮጵያ አመራሮች እና ከአፍሪካ ኅብረት ጋር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። በመጨረሻም፣ “በጋራ በመሥራት ለአሜሪካ፣ ለኢትዮጵያ፣ ለአፍሪካ እና ከሁሉም በላይ ለልጆቻችን የበለጸገና አስተማማኝ የወደፊት ጊዜ መገንባት እንደምንችል አምናለሁ” በሚል ንግግራቸውን ደምድመዋል።

ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የደህንነት ስጋት እንዳለባት በመግለጽ ወደ ቀይ ባህር የመመለስ ህጋዊና ሰላማዊ ጥያቄ ስታቀርብ መቆየቷ ይታወሳል። የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዝዥ በተመሳሳይ ይህን ስጋት የጋራ አድርገው ማቅረባቸው ኢትዮጵያ እያነሳች ላለው የባህር በር ጥያቄ አሜሪካ ምላሿ ቀና መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ አመላካች መሆኑን ገልጸው የዘገቡ ጥቂት አይደሉም።

“ሁለቱ አጋራት የጋራ ስጋት አላቸው፣ ይህም በቀይ ባህር ላይ ነው፤ ይህንኑ የጋራ ስጋታቸውን ለማስወገድ በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቀዋል። በግራ ከሰሩ ደግሞ ከቀይ ባሕር እስከ ህንድ ውቂያኒሽ ጫፍ እንጂ ኝፍሌው ወንዝ ላይ አይደለም” ሲሉ አስተያየት የሰጡ የሰውየው አስተያየት ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር ለመግባት የጀመረቸውን እንቅስቃሴ የመደገፍ ያህል ነው” ብለዋል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related