የጎጃምና አካባቢው ሃብታሞች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ ተጀምሮ የነበረው ጥረት ዳግም ሊጀመር ነው፤ ደመቀ መኮንን ለምን ዝም አሉ?

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በሌሉበት ክስ የተመሰረተባቸው ዋና ዋናዎቹ የጎጃምና የአካባቢው በላሃቶች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ ተጀምሮ የነበረው እንቅስቃሴ ዳግም ሊጀመር እንደሆነ አዲስ ሪፖተር ስምታለች። የዋሽንግቶን ተባባሪያችን እንዳለው ቀደም ሲል በጁላይ ተጀምሮ የነበረው እንቅስቃሴ የወቅቱ ዲፕሎማት አስቴር ማሞ በሚገባ ሊያስኬዱት ባለመቻላቸው ነበር የተስተጓጎለው። አሁን ላይ ከባህር ዳር ያገኘነው መረጃ ተቋርጦ የነበረው ባለሃብቱና መንግስትን የማስማማት ሂደት እንደሚጀመር ነው። ወ/ሮ አስቴር ማሞ በግል ስልካቸው ጉዳዩን አስመልክቶ የሚያውቁትን እንዲናገሩ ቢጠየቁም ፈቃደኛ አልሆኑም። የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የአማራ ክልልን ሰላም ከማስፈን አንጻር ዝምታቸው እያነጋገረ መሆኑ ተመልክቷል።

ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ በሰላም ከሚኖሩበት መንደራቸው ሳይቀር ሁከት፣ ዝርፊያ፣ ግድያ፣ እገታ፣ የማዳበሪያ አቅርቦት፣ ሕክምና፣ ትምህርት ቤት፣ ማህበራዊ አገልግሎት፣ የትራንስፖርት አቅርቦት፣ የሸቀጦች ፍሰት ወዘተ ለተናጋበት የአማራ ሕዝብ ዜናው በጎ ነገሮችን ይዞ እንደሚመጣ ዜናውን ያካፈሉን ወገኖች አስታውቀዋል። በተቃራኒው ዜናው በክልሉ ባለው ቀውስ አትራፊ ለሆኑ ሚዲያዎች፣ አክቲቪስት ነን ለሚሉና ራሳቸውን “ታጋይ” ብለው ለፈረጁ የሶሰተኛ ወገን አገልጋዮች መርዶ እንደሚሆን ተመልክቷል።

ለባህር ዳር የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ መረጃ የሰጡ የሚታወቁ ነጋዴ “ባለፈው በጁላይ ተጀምሮ ያልተሳካው ባለሃብቶቹን ከመንግስት ጋር የማስማማት ስራ ዳግም እንዲጀመር ሁኔታዎች ተመቻችተዋል” ብለዋል። ይሁን እንጂ መቼ እና እንዴት እንደሚጀመር ቆርጠው አላስታወቁም። አክለውም ውጭ የወጡት ብቻ ሳይሆኑ በአገር ቤት ውስጥ ሆነው በቂም በቀል፣ በጥላቻ፣ በምቀኝነት ያልሆነ ጥቆማ እየቀረበባቸው የሚሰቃዩ ባለሃብቶች ጉዳይም ሊታይ እንደሚገባ አመልክተዋል።

“አጋጣሚውን በመጠቀም ባለሃብቶችን በማስፈራርትና የተሳሳተ ጥቆማ በመስጠት የሚያስበርግጉ በክልሉ ውስጥ አሉ። እነዚህን አካላት መንግስት ሊለያቸው ይገባል” ያሉት የባህር ዳሩ ነጋዴ ” አሁን ሕዝብ በቃኝ ብሏል። መንግስት የተጠናና ውጤታማ ሊያደርገው የሚችለውን አካሄድ በመከተል የክልሉን ሰላም ለማስከበር መንቀሳቀስ አለበት” ብለዋል። በአማራ ክልል የቢሮ ውስጥ ፋኖዎች፣ በጫካ ካሉት ጋር ተናበው እንደሚሰሩ አዲስ ሪፖርተር ከባንክ የሂሳብ ቁጥራቸው ጋር የተያያዘ መረጃ ደርሷታል።

እኚሁ ነጋዴ በውጭ አገር በስደት ያሉ የአካባቢው ተወላጅ ባለሃብቶች መካከል ስማቸውን ካልዘረዘሯቸው ባንኮች ከፍተኛ ገንዘብ ይዘው መሸሻቸው እንደ አንድ የሰላም ሂደቱ ተግዳሮት አንስተዋል። ከባንኮቹ የተወሰደው ከፍተኛ ሃብት አስመልክቶ ራሱን የቻለ ድርድር የሚጠየቅ እንደሆነም አመልክተዋል። “ብሩ ብዙ ነው። ብሩ የሕዝብ ነው። ብሩ መመለስ ይገባዋል” ያሉት የመረጃው ምንጭ ” መንግስት ሁሉንም አስታሞ መፍትሄ ከፍለገለት ስምምነት ላይ ይደረሳል” ብለዋል።

የዋሽንግቶን ዲሲ ተባባሪያችን ያሰባሰባቸውን መረጃዎች ጠቅሶ እንዳለው ታዋቂ የሚባሉት ባለሃብቶች ወደ አገር ቤት መግባት ይፈልጋሉ። በስም ያልጠቀሳቸውን አንዱን ጠቅሶ እንዳለው ” መተማመኛ ካገኘሁ አገሬ እገባለሁ” ብለዋል።

ባለሃብቱ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ጥረት ለማድረግ ከተነሱት መካከል የሆኑት ” ገና ስለሆነ ብዙ ማለት አይቻልም። ይሁን እንጂ አምባሳደር ብናልፍ ብዙዎቹን ስለሚያውቋቸው እንደ ቀደመው ንግግር መተማመኑ ያመዝናል የሚል ግምት የለኝም” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

በእርቅ ጉዳይ ሰፊ ልምድ ያላቸውና ነዋሪነታቸው አሜሪካ የሆነ ባለሙያ “አቶ ደመቀ መኮንን የጎጃም ባለሃብቶችን በድንብ እንደሚያውቋቸው፣ ብዙም ጉዳዮች አብረው እንዳከናወኑ ይታወቃል። ለምን ይህን ኃላፊነት ወስደው ክልሉን ያረጋጉም? ይህን ቢያደርጉ በስልጣን ዘመናቸው ከባህር ዳር ጀመሮ ላጠፉትም ጥፋት ማካካሻ ይሆንላቸዋል።” ሲሉ ጥቆማና አስተያየት ሰጥተዋል።

የአቶ ደመቀ ከስልጣን ከተነሱ በሁዋላ ዝም ብሎ መቀመጥ በርካታ ጉዳዮችን እንዲያነሱ እንዳስገደዳቸው የጠቀሱት እኚሁ የግጭት አወጋገድ ባለሙያ፣ “አቶ ደመቀ መኮንን በማራ ክልል በጸጥታ መዋቅር፣ በክልሉ ፓርቲ መሪነት ለረዝም ጊዜ ሳይነኩ የሰሩ በመሆናቸው ብዙ ነገር መቀየር እንደሚችሉ አምናለሁ። ለዚሁም ብዙ ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል” ብለዋል። አቶ ደመቀን በስልክ በማግኘት ወይም በአካላ በማነጋገር በቀጣይ ከደረሱን በርካታ ጥቆማዎችና መረጃዎች መሰረት አነጋገረን ይፋ እናደርጋለን። አቶ ደመቀ በምክትል ጠ.ሚኒስትርነትና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉ ከፍተኛ ባለስልጣን እንደመሆናቸው፣ የክልሉ ፓርቲ የረዥም ጊዜ መሪ መሆናቸውን በማንሳት ሰፊ ትችት እየተሰነዘረባቸው ነው። አዲስ ሪፖርተር ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ ተጀመሮ በነበረው ምርመራ የአቶ ደመቀን አሻራ የሚያሳይ መረጃ እጇ ስለገባ ይህኑኑ መረጃ በቅርቡ ልፋ እንደምታደርግ ከወዲሁ ታስታውቃለች።

አቶ ደመቀ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አቶ ብናልፍ ጓደኛና የቅርብ ሰው መሆናቸውን፣ ከታችኛው የሕይወት እርከን ጀምሮ የሚተዋወቁ ስለሆነ አሁን ሊጀመር ነው የተባለውን የዕርቅ አሳብ ሊያግዙና ውጤታማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ አስተያየት የሰጡን እምነታቸውን ገልጸዋል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር እስከዳር አመጽ ለማቀጣጠል በተጠራው ስብሰባ “አስቻይ ሁኔታ የለም ተባለ” ጃዋር በድጋሚ አፈገፈገ

"በዋሽንግቶን ዲሲና ሎንዶን አገር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ...

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...