ሁለቱንም ባለብረቶች ገድሏቸው፤ የአቶ አያልነህ አሳዛኝ ታሪክ ከባህር ዳር እስከ አዲስ አበባ ” ልጅ ያልህ ነግ በእኔ ነው” ለሰበር ዜና አብሳሪዎች

Date:

አዲስ ሪፖርተር – አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ግድም ያገኘዋቸው አቶ አያልነህ /ስም የተለወጠ/ የከባድ ጭነት መኪና አሽከርካሪ የባሕር ዳር ዙሪያ ነዋሪ እንደሆኑና ሦስት ልጆች እንዳሏቸውም አጫወቱኝ፡፡ ከባህር ዳር ከነቤተሰቦቻቸው ነቅለው ወደ አዲስ አበባ የመጣታቸው ጉዳይ ልቤንም ቀልቤንም ሰጥቼ እንዳደምጣቸው አሰገደደኝ።

አቶ አያልነህ ለምምና እንዴት የሚወዷትን ባህር ዳር ለቀው እንደመጡ ሲያጫውቱኝ “ሰለምን በወገኖቻችን መከራ ውስጥ ራሳችንን ከተነ ማሰብ ተሳነን” የሚል ሞጋች ጥያቄ ለራሴና “ጋዜጠኛ ነን” ለምንለው ሁሉ እንዳነሳ ተገደድኩ።

ወደ አቶ አያልነህ ጉዳይ ከማለፌ በፊት አንድ አባት ” ግን ምን ነካን? ምን ተጸናወተን? ምን ዓይነት መንፈስ ዘለቀብን? እንዴት በዚህ ደረጃ ተጨካከንን? እንባ፣ ደም፣ መፈናቀል፣ የሕጻናት ስቃይ፣ የእናቶች ጣር፣ የአዛውንቶች ሮሮ፣ ወዘተ ንግድ ሆነ?” ያሉት ታወሰኝ። መፈናቀል፣ ሞት፣ ስደት፣ እገታ፣ አስገድዶ መድፈር ወዘተ “ሰበር ዜና” በሚል የላይክና ሳንቲም መልቀሚያ የሆነባት ኢትዮጵያ እርግጥም አቅላችንን በሳትን “ጋዜጠኛ” ተብዬዎች መከራ እየተጋተች ነው። አያያዙ ያስፈራል። ወደ አቶ አያልነህ ልመለስ።
አቶ አያልነህ ከተወዱበት፣ ካደጉበት፣ ጎልምሰው ትዳር ከመሰረቱበት፣ ልጆች ካፈሩበት የሞቀ ቤታቸው ውልቅ ካሉ የሮጠውን ጊዜ ቆጥረው ካላስታወሱት በስተቀር ከመከራው ጋር ተዳምሮ የዘመን ያህል ርቆባቸዋል። ከመንደራቸው ወጥተው ሁሉን ክትት አድርጋ በምታጎርሰው አዲስ አበባ መኖር ከጀመሩ በኡዋላ አሁን አሁን ተስፋ ቢጤ ቢታያቸውም የተለመደውን ሥራቸውን ግን መጀመር አልቻሉም፡፡

ለሥራቸው ማቆምና አማራ ክልልን ለቅቀው መውጣታቸው ምክንያት የሆናቸው ደግሞ በክልል ደረጃ የተከሰተው ግጭት እና አለመረጋጋት እንደሆነ ሲናገሩ “ሰሚ” ለሆነ ሁሉ ከላይ እንደገለጽኩዋቸው አባት “ግን ምን ነካን?” ከማለት ውጭ ሌላ ምን እንደሚባል የዚህ ሪፖርት አቅራቢ ለጊዜው የሚለው ነገር አልነበርርውም።

በሹፍርና ሲተዳደሩ ጥሩ የሚባል ገቢ የነበራቸው፣ ልጆቻቸውን በግል ትምህርት ቤት ከፍለው ያስተምሩ የነበርሩና በኑሯቸው ደስተኛ ከሚባሉት ተርታ እንደሚመደቡ ዝርዝር ጉዳዮችን አንስተው ያጫወቱኝ አቶ አያልነህ፣ አልፎ አልፎ የሚታየው ተለዋዋጭ የፊታቸው ገጽታ ” ምን እየሆነ እንደሆነ አለገባኝም፣ ሊገባኝ አይችልም፣ ተምታቶብኛል፣ ሲያልቅ አያምር፣ የፈጣሪ ያለህ …” ብዙ ይናገራል።

“እንዴት ስራዎትን ጥለው ወደ አዲስ አበባ ተሰደዱ” የሚል ጥያቄ አፌን እሬት እሬት እያለው አነሳሁላቸው። ተነፈሱና አንታቸውን አከክ አከክ እያደረጉ ” ግጭቱን ተከትሎ ፋኖ የተሽከርካሪውን ባለቤት የመንግሥት ደጋፊ ነህ ፣ለእኛ የገንዘብ ድጋፍ አታደርግም በማለት ሙሉ ንብረቱ በመዝረፍ መኪናው ማቃጠላቸው ምክንያት ሥራዬን አጣሁ” አሉና ዓይናቸውን ወደ ቡናው ስኒ መልሰው የተረፈችውን ጨለጧት። አፋቸውን እያጸዳዱ ” ይኸው ነው፤ ተወኝ ባክህ” አሉ። ብተዋቸው ደስ ባለኝ … ግን የት? እንዴ፣ ምን እየበሉ ይኖራሉ? ልጆቻቸውስ?

አቶ አያልነህ ኑሮ አርጩሜ ያነሳችባቸው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው። ሥራ ባቆምኩበት ማግስት በሹፍራና ስራ ለመቀጠር ሌሎች ባለተሽከርካሪዎችን ቢያናግሩም አልሆነም። ችግሩ በየደረጃው ሁሉም ጋር ያንኳኳ፣ ስጋት ያስከተለ፣ የፍርሃት ቆፈን የዘራ በመሆኑ አማራጭ ጠፋ። ለጥቂት ወራቶች ያጠራቀሟትን እየመነዘሩ ልጆቻቸውን በነበሩበት ትምህርት ቤት አስቀጠሉ። የኑሮ አርጩሜዋ ቀስ እያለ እየለበለባቸው ሄደ። ገቢ ቆሟል። ወጪ ብቻ!! በዚያ ላይ ስጋት!!

“አንድ ቀን እሑድ እኔ እና ባለቤቴ ልጆቻችን ይዘን ቤተክርስቲያን ሄድን፤ ስንመለስ የሚበላ የለም ኪሴን ዳበስኩ አስር ብር ብቻ አለችኝ በዛች አስር ብር ለልጆቹ ብስኩት በመግዛት ሰጠኋቸውና ሲበሉ አየሁ ብስኩቷ እንዳላጠገበቻቸው ሳይ በጣም አዘንኩ እንባየ ተናነቀኝ”ሲሉ ኑሮ ወዴት እየገፋቸው እንደሆነ በተሰበረ መንፈስ መተረክ ጀመሩ። አልፎ አልፎ “እንደዚህ የማናዝዛቸው ምን ልፈይድላቸው ነው” የሚል ሙግት ውስጤን ይፈትነዋል። እኚህንና እኚህን መሰል ዜጎች ላይ በሚደርስ ቀውስ ውስጥ የስልጣን ጥመኞችን ስሜት ለማርካት እየተከፈለን የሁከት ማገዶ የምናቀጣጥል እኛው አይደለን? ሰበር ዜና እያልን ሰላም የተቀመጡትን የምናተራምስ ቅጥረኞች ራሳችን እናው ሚድኪያ ውስጥ የተቀረቀርን ከርሳሞች አይደለን፣ ፖለቲካ፣ የፖለቲካ ልዩነት፣ አገር፣ ህዝብና ብሄራዊ ጉዳይን ቀላቅለን …. ዘመን ፈራጁ ወደፊት በየትኛው ወንፊት ያበጥረን ይሆን?

የአቶ አያልነህን ዓይነት ሚሊዮኖችን ስቃይ ሰበር ዜና፣ ዜና ትንታኔ፣ ወዘተ ያለማቋረጠ እያቀረቡ ማጠቃለያ ላይ ” አገልግሎታችን ደግፉ” በማለት ልመና ላይ የተሰማራነው “ጋዜጠኛ” ተብዬዎች መካከል ህዝብን ለገቢያቸው እያጫረሱ ከሙሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር ለልደት ጀርመን፣ ኳስ ለማየት ሎንዶን እየተንሸራሸሩ ፎቶ ይልኩልናል። ደረጀ ፌስ ቡክ ላይ ግቡና የአማራ ክልል ተፈናቃዮችን እያሰባችሁ እዩት። ይቅርታ “ጋዜጠኛ የሕዝብ ልጅ” ድንቄም!!

“ማታ ማታ የማሰራጨው የላይቭ ፕሮግራም ልጆቼን እየረበሻቸው ፣ ሁሌ ማታታ ማታ በምናገረው ነገር እየተሳቀቁ ቤት ውስጥ ችግር ስለሆነ ዲሲ ምድር ቤት ውስጥ ተከራየሁ” ሲል ሃብታሙ አያሌው ቤቱን ላከፍራየው ሰው ባልደረባ የተናገረውን ዛሬ ደፍሬ ሪፖርቴ ውስጥ አካተትኩት፤ አቶ አያልነህና ቤሰቦቻቸው፣ ዛሬ ለልመና የተዳረጉት ልጆቻቸው አምላክ ፍርድ አይሰጥ ይሆን?

አንድ ቀን “ትልቁን ልጄን ይዠ እኖርበት ከነበረው አካባቢ እርቄ ሄድኩ” የሚሉት አቶ አይልነህ “አላፊ አገዳሚው በሚበዛበት ቦታ ላይ ልጄን ቁጭ አደረኩና ፌስታል ዘርግቼ መለመን ጀመርኩ” ሲሉ ተወልደው ባደጉበት፣ በከበሩበት መንደራቸው ደጅ የወጡበትን ቀን አስተዋወቁኝ።

“ልጄ አይን አይኔን ያየኛል። ግራ ተጋብቷል፤ ሰዎች አለባበሳችንን አይተው እየተገረሙ ብር እየጣሉልን ማለፍ ጀመሩ። ሲሉ ተምሮ ራሱን ይችላል ብለው የግል ትምህርት ቤት እየከፈሉ ያስተማሩትን ልጃቸውን ለማኝ የእኔ ቢጤ ያደረጉበትን የፋኖ ገጸ በረከት አወጉኝ። ሰሞኑን “በቃኝ” ብሎ እጁን የሰጠው ማስረሻ ሰጤ “ውሻዬን ሸጬ ቀበሮ ገዛሁ” ያለው ብሂል እዚህ ላይ ቢነሳ አግባብ መስለኝ። ግን እሱ ያሰማራቸው ፋኖዎችስ ቢሆኑ አቶ አያልነህን ከነልጆቻቸው ለማኝ ያደረጓቸው? አይ ግዜ!! ሸኔ ዘርፎ፣ ገድሎ፣ አፋናቅሎ እጁ ይዘጥና ኮብራ ይነዳል!! ፋኖ ገሎ፣ ገርፎ፣ እጅ ቆርጦ፣ አስተማሪዎችን ረሽኖ እጅ ሲሰጥ ጀኛ ይባልና ይወደሳል። ሌብነቱ ያልበቃቸው ግፈኞችና ቅጥረኞች እጅ የሰጡትን “ከሃጂ” እያሉ በእነኤው የሙያ ተብዬው ባልደረቦች በኩል ያሳደባሉ፣ ለሌላ ግፍና መከራ ይማማላሉ። ኢትዮጵያ እንዴት ያለ ቆዳ ይሆን ያላት? ድንቅ ሕዝብ!!

የአቶ አያልነህ ልምና አዲስ ኢንቨስተመንት ሆኗል። ፋኖ ያጸደቀላቸው፣ እሳቸው ብቻ ሳይሆን በርካቶች ቤት ይቁጠራቸው፣ “በተጣለልኝ ገንዘብ ለባለቤቴ እና ለልጆቸ ምን አይነት ምግብ ገዝቸ እንደምገባ እያሰላሰልኩ እያለ ድንገት ስሜ ሲጠራ ሰማሁ” የሚሉት አቶ አያልነህ፣ ቀና ስል የጠራኝ በኪራይ ከምኖርበት ቤት አካባቢ የሚኖር ጎረቤቴ ነው። እንዳየሁት በጣም አፈርኩ” የሚሉት አቶ አያልነህ፣ “ምነው ?ሲለኝ እንባየን መቆጣጠር አቃተኝ። ዝም ብሎ እንደ ጅረት ወረደ። ፊቴ በቅጽበት ራሰ። አፍረት አንገቴን ሳይሆን ልቤን ደቃው፣ መሬት ብትወጠኝ …. ጓደኛየ ደነገጠ። መጣና አቀፈኝ። ምንድን ነው የተፈጠረው? ብሎ ጠየቀኝ። ያሳለፍኩትን እና እያሳለፍኩት ያለውን ፈተና ከእንባዬ ጋር አብረን አወጋንለት”

“ጎረቤቴ በጣም አዘነ። አይኑ እንባ አቅርሯል፤ የዘረጋሁትን ላስቲክ እስከ ብሩ ሽክፍ አድርጎ አነሳው። በልና ተነስ እንሂድ አለኝ፤ ቆይ ትንሽ ልለምን አልኩት። በፍጹም አንተ አትለምንም፤ እንሂድ ብሎ እኔ እና ልጄን ይዞን ወደ ሰፈር ሄደ” አቶ አያልነህ ጎረቤታቸው ጋር ሆነው ሰፈር እንደደረሱ የአካባቢው ሰው የሚበላ ሰጡዋቸው። የሰጡዋቸውን እየቀመሱ እሳቸው ያስቡ የነበረርው ለምነው ባገኙት ሳንቲም ቤት ሊሚጠብቋቸው ልጆቸ እና ለባለቤታቸው ምን ይዘው እንደሚገቡ ነበር።

ትንሽ ቀማምሰው ወደ ቤታቸው ይዘውት የሚሄዱት ምግብ ሰጧቸው። ይዘውት የመጡትን ምግብ ለልጆቸ እና ለባለቤታቸው አጋሩ። “ልጆቻችን በልተው የሚጠግቡ አልመስለንም፤ የልጆቻችን መጥገብ ስናይ እኛ መብላት ጀመርን።” ካሉ በሁዋላ “ባለቤቴን ትኩር ብየ አየኋት። አሉ ቆንጆ ነበረች” በማለት በድንገት አዕምሯቸው ውስጥ የተሰነቀረውን ስሜታቸውን በደበዘዘ ፈገግታ አስታወሱ።

ልብ ብለው ሲስያኡዋት በፊት በምቾቱ ወቅት ከፊቷ የሚቀዳው ወዘና ረግፏል።፤ ከልመና መልስ ምግብ ይዘው ቤት ሲገቡ ልብ ብለው እንዳስተዋሏት ሲናገሩ ጠቁራለጭ ተጎድታባቸዋለች። ይህ ሁሉ የሆነው በሰላም እየኖሩ ባለበት መንደራቸው፣ በሚሰሩበት ከተማ አንድም የጠላት ኃይል ሳይመጣ ፋኖ በሚባለው ታጣቂ ኃይል አማካይነት የተሰጣቸው ስጦታ ነው። ስንቶች እሳቸውን መሳዮች እንዳሉ ቤትና ፈጣሪ ይቁጠረው።

“ዛሬስ እንዲህ መልኩ በላን። በቀጣይ ምን ማድረግ ነው ያለብኝ? ምንድን ነው የምሠራው? ብየ ከራሴ ጋር መታገል ጀመርኩ” እንዴት ነው ትዳሬን ምመራው? ልጆቸንስ እንዴት ነው የማሳድጋቸው? ይህ አኗኗር እስከመቸ ነው የሚቀጥል? ግራ ግብት ብሎኛል በማለት ከዛሬ በላይ ነገ እንዳስፈራቸው አወጡ አወረዱ።

በዚህ መሀል አንድ ቀን በድንገት በራቸው ተቆረቆረ እና “እንዴት ዋላችሁ” በማለት መንገድ ላይ ሲለምኑ ያገኛቸው ጎረቤታቸው እና አንድ ሰው ወደ ውስጥ ዘልቀው ቁጭ አሉ። ተከታትለው ሌሎች ሴቶች ጎረቤቶቻቸው በማዳበሪያ የጤፍ ዱቄት፣ እንጀራ በትሪ ይዘው ገቡ። ለአቶ አያልነህ ህልም የሆነው ይህ እውነት ተስፋቸውን አለመለመው። ይህን ስሰማ ይህን ከመስለ ማህብረሰብ የተወለዱ ሽፍቶች እንዴት በዚህ ደረጃ ለወጡበት ሕብረተሰብ ” ቀበሮ” ሆኑበት?

እንግዶቹ ቤት እንደገቡ ድራማ ሆነ። “ባለቤቴ ባየችው ነገር ተደናግጣ ጥግ ይዛ ቆማ የሚሆነውን ታያለች፤ መጀመሪያ ያገኘኝ ጎረቤቴ እኛ እያለን አንተ በዚህ ሁኔታ አትቀጥልም፤ ለጊዜው ይህ ከሰፈር ሰዎች የተሠበሠበ ነው ብሎ የተጠቀለለ ብር ሰጠኝ፤ ሁለተኛው ሰው ልጆችም ትምህርት ቤት እንዳቋረጡ ሰምተናል ከነገ ጀምሮ ትምህር ቤት እንዲጀምሩ አድርግ እስኪመቻች ድረስ ክፍያውን እኛ እንሸፍናለን አሉኝ፤ ይህ ጊዜ ያልፋል ዋናው እኛ ደህና እንሁን ሁሉም ነገር ይስተካከላል አይዞህ አሉኝ” አሉና አይናቸው ወደላይ ወደ ዋና ጌታ እያመለክቱ ከንፈራቸውን በለሆሳስ ንግግር አንቀሳቀሱ። ልባቸውን ጌታቸው ፊት እያፈሰሱ ስለመሆኑ የሃና ጸሎት አስታወሰኝ። ብቻ አይናቸውን ወደ ሰማይ ሰክተው አነቡ። እየሰምሁዋቸው አያቸው ነበር። አሁን እሳቸውን ማየት ስላተቻለኝ አንገቴን ደፋሁ። ሳልሳበው ስሜቴን መቆጣጠር አቃተኝና ራሴን እየረገምኩ በጸጸት ስሜት ለእነ ደረጃ፣ ሃብታሙ፣ ማንም አነባሁ። ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ይህን እንዲያነቡ የሚያውቋቸው እንዲልኩላቸው ጽለይኩ።

ሀባታሙ አያሌው፣ ደረጀ ሃብተወልድ፣ እነ ፋሲል የኔአለም፣ የሎንዶን ምናለ ዛሬዎች፣ በብር የተቧቀሳችሁት 360ዎች እነ ታማኝ በየነ፣ እነ አቶ ለገሰ፣ ከአዲስ አበባ ጀምሮ በስኳር አክሲዮን ሌብነት የሽፈትከው ምናላቸው ወዘተ እንደኔ ያላችሁ ወጠጤ ተንታኞች ሚስቶቻችሁ የሚያጌጡት፣ ልጆቻችሁ የሚለብሱትና የሚመገቡት በደም ንግድ በተሚገኝ ገንዘብ ነውና ይህን እርም ማግበስበስ አቁሙ። በተለይ ሚስቶች ለልጆቻችሁ እርም አታስቀምጡ። ይህ የእነ አቶ አያልነህ መሰል ቤተሰቦች መልዕክት ነው። የፍርድ ለዚያውም የሰማያዊው ፍርድ የሚያመቻች እምባና ግፋ ሰማይ ደሷል። ከነዚሁ ቀመኞች ጋር የገጠማችሁ ካድሬዎችም ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ!!

“ምንም ቃል ሳላወጣ እንባየ ይወርዳል፣ ባለቤቴም ታለቅሳለች። ልጆቸ አንጋጠው እኛን ያያሉ በቃ አሁን እኮ ሁሉም ነገር ተስተካከለ። በቃ አለ መጀመሪያ ያገኘኝ ጎረቤቴ” ሲሉ በትዝታ ውስጥ ሆነው የሆነውን ሁሉ ተረኩት።

“ጎረቤት ማለት እኮ በደስታ ጊዜ ሲኖርህ ብቻ እየተጠራራህ፣ እየደገስክ በፌሽታ እና በደስታ ማሳለፍ ብቻ አይደለም። እንዲህም ችግር ሲኖር ተነጋግረን ችግሩን ተጋርተን ማለፍ መቻል ነው ያለብን። እኛን ሳታማክር ለመለመን መወሰንህ ትክክል አይደለም። በጣም አጥፍተሀል ብለው ወቀሱኝ።

ወቀሳው ልክ መሆኑንን አምነው ይቅርታ ጠየቁ። አቶ አያልነህ ኪሳቸው በቀራቻቸው አስር ብር ለልጆቸ ብስኩት ገዝተ ሲበሉ ካዩ በሁዋላ የተሰማቸው ስሜት ገፍቷቸው ለምና ያወጣቸው ታሪክ በወዳጆቻቸው ተቀየረ። የሆነውን ሲያዩ ተደነቁ። “ፍልቅልቅ ፊታቸውን እያየሁ ከጎረቤቶቸ ጋር እየተጨዋወትን የተፈላውን ቡና መጠጣት ጀመርን፤ ቡናው እንዳበቃ ከዚህ በኋላ ይቸግረኛል ብለህ እንዳታስብ ሁሉም ነገር መስመር ይይዛል ብለው ተሰናብተውን ወጡ፤ እኔም ምሥጋናየ ያደረጉልኝን እንደማይመጥን ባውቅም ምሥጋናየን አዥጎድጉጀ ሸኘኋቸው” የፋኖ ክፋትና የፋኖ ነን ባዬች ወላጆች ደግነት በአንድ መንደር!! ባህር ዳር ዙሪያ!!

“ዛሬ ይህን ያደረገ አምላክ ነገም እንደማይተወኝ በማመን ከባለቤቴ እና ከልጆቸ ጋር ደስ ብሎን ስንጫዎት አሳለፍን” በዚህ መልኩ ትንሽ ጊዜያት አለፉ።

አንድ ቀን ታዲያ የማላውቀው ስልክ ተደወለልኝ እና ለጊዜው የከተማ ታክሲ ሥራ እንደተገኘልኝ ነግረው መጀመር እንደምችል አበሰሩኝ፤ አሁን የታክሲ ሥራ እየሠራሁ ቤቴን መምራት እና ልጆቸን ማስተማር ጀምሬያለሁ። እግዚአብሔር ይመሥገን ዕድሜ ለጎረቤቶቸ በማለት ያሳለፉትን ከባድ የችግር ጊዜ እንዴት እንደተቀየረ አወጉኝ፡፡

ነገሮች እየተወሳሰቡ የመጡት ከዚህ በኃላ እንደሆነ ባለ ታሪኩ አቶ አያልነህ አስረድተውናል “አዲስ የታክሲ ሥራን ተቀጥሬ መስራት ከጀመርሁ ወዲህ ፋኖ አልፎ አልፎ እየመጣ የጥይት ድምፅ ስለሚያሰማ ስራችንን በሰቀቀን ነበረ የምንሰራው። ግን ተመስገን እያሉ ከረሙ።

“ውሎ አድሮ እንደ መጀመሪያ እንደሆነው አዲስ የተቀጠሩበት የመኪናው ባለቤት ፋኖ የመንግሥት ደጋፊ ነህ’ በማለት ገደሉዋቸው።ይሕም አልበቃ ብሏቸው በመኖሪያ ግቢያቸው ውስጥ ያቆምኩት ታክሲ ተሰርቆ አደረ” ሲሉ ዳግም ህይወታቸው መጨለሙን በአዲስ የታሪክ ምዕራፍ አወጉኝ። ድጋሚ የሰውን ፊት ማየቱን ሲያስቡት ተደበላለቀባቸው።

“በተከታታይ የያዝኳቸው መኪኖች ባለንብረቶች መገደላቸው እድለ ቢስነት ፣እንዲሁም ለፋኖ መረጃ አንተ ነህ የምትሰጠው ተብዬ በአከባቢው ሰው መፈረጄ ችግሬን አወሳሰበብኝ” ሲሉ የመከራቸውን መወሳሰብ አዲሱ መከራቸው የከረረ መሆኑን ነገሩኝ።

“ቢያንሰ በሚያውቁኝ አካባቢ በልመና ከምተዳደር ማንም በማያውቀኝ ፣እኔም ማንንም በማላውቅበት አካባቢ ብሰራ ይሻለኛል ብዬ ልጆቼንና ባለቤቴን ጥዬ አዲስ አበባ መጣሁ” ሲሉ ስደት የወጡበትን ምክንያት ይፋ አደረጉልኝ።

አዲስ አበባ መጥተው ጎዳና አደሩ፣ ተሰቃዩ፣ ነገሮች ሁሉ ከትክጀሻቸው በላይ ሆኑባቸው። ውሎ ሲያድር ተላምደው አሁን በተለያዩ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ላይ በመሰማራት እየሰሩ ነው። ሲጎድልም አልፎ ደግሞ በልመና የጎድለውን ያሟላሉ።

እንደ ማሳያ የአንድ ግለሰብ ታሪክ አነሳን እንጅ በአማራ ክልል በአሁን ወቅት ግጭቶች ምክንያት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ሥራ መሥራት፣ በሰላም ወጥቶ መግባት አዳጋች መሆኑ ብቻ ሳይሆን ለመስማት የሚከብዱ መረጃዎች እየወጡ ነው።

ሰላም ምን ያክል ዋጋ እንዳለው የሚያውቀው ሰላም ያጣ ሰው ነው፤ በተለይ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ይሠሩ በነበሩ ዜጎች እና አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው እንግልት፣ ድብደባ፣ በጫኑት ጭነት ያለአግባብ በየቦታው ቀረጥ መቀረጥ እና ከሥራ መፈናቀል የተጎዱት ጥቂት የሚባሉ አይደሉም፡፡ መኖሪያቸውን፣ ንግዳቸውን፣ ቅዬያቸውን ለቀው የተሰደዱ ቁጥራቸውን የሚያውቀው ፈጣሪና ቤተሰቦቻቸው ብቻ ናቸው።

ምን ያህሎች የአካል እና የሥነ ልቦና ጉዳት ገጥሟቸዋል? በነሱ ስር ስንት ቤተሰቦች የችግሩ ሰለባ ሁነዋል? ልጆቻቸው በምን ሁኔታ ላይ ነው ያሉ? ስንቶች ትምህርታቸውን አቋርጠዋል? የቤት ውስጥ ሰራተኛ ሆነው ተቀጥረዋል። ተሰደው ሴተኛ አዳሪ ሆነዋ? ክልሉ እንደ ክልል ወድየትኛው አዘቅት እየተሽቆለቆቅለ እየወረደ ነው? የአማራ ሕዝብ ላይ ትህነግ በጅምላና በተናጠል ነፍጠኛ ብሎ ፈርጆ ካደረሰ ጉዳትና ግፍ ጀመሮ አሁን ላይም የሚፈጸሙ ጥቃቶችን መርምሮ፣ ምንጩን አጥርቶ፣ ሌሎች ሊገዙት የሚችሉት የትግል ስልት በማዘጋጀት መታገል ሲገባ፡ሙስሊሙን ህዝብ፣ ሌሎችን ብሄረሰቦችና አካባቢዎች የሚያስደነብር የደነቆረ የትግል ስልት ተመርጦ የአማራ ሕዝብ እንዲከፍል እየተደረገ ያለው በጊዘ እንዲቆም ካተደረገ የክልሉ አውዳደቅ፣ የሕዝቡ ስቃይ፣ ከምንም በላይ እንደ አገውር ኢትዮጵያን የጠላት መፈንጪያ ከማድረግ የዘለለ ፋይዳ የለውምና ቅድሚያ ለውውይትና ለበስለ ፖለቲካ ቢሰጥ መልካም ነው ባይ ነኝ፤ “ንገ በእኔ” ነውና የሰበር ዜና ነጋዴዎች ልብ እንግዛ

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእናት ሀገር ጥሪ ተሳትፎና ኮሎኔል መንግሥቱ

የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ...

ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ፤ ኢትዮጵያን ወደ መፃኤ ዘመን የሚያሻግር የሎጂስቲክስ አብዮት

ኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ ሰማይ ስር የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ካርታዋን እንደገና ለመሳል...

“ጥርስ የሌለው ውሻ” የሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም መፃኢ እጣፈንታ

አዲስ ሪፖርተር - ፕሬዛዳንት ትራምፕ አሜሪካን ከተባበሩት መንግስታት ደርጅት...

በዘመነ ትራምፕ ጫና ውስጥ የወደቀችው ሶማሊያ እና ለሶማሌ ላንድ ተስፋን ያለመለመው አዋጅ

አዲስ ሪፓርተር - ከሶማሌላንድ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና ከእስራኤል እውቅና...