ሰክረው የሕክምና ስሕተት በፈጸሙ ከ 41 በላይ የጤና ባለሞያዎች የሙያ ፍቃድ ተሰረዘ፤ በግል የሕክምና ተቋማት ክፍያው አማሯል

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በአዲስ አበባ ከተማ አልኮል ጠጥተው እና በቸልተኝነት በፈጸሙት የሕክምና ስህተት ምክንያት ሕሙማንን ለሞት፣ ለከፋ አደጋ ከዚህም አለፍ ሲል ለተለያዩ በሽታዎች ያጋለጡ አርባ አንድ የጤና ባለሞያዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የከተማ አስተዳደሩ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ለአዲስ ሪፖርተር አስታወቀ።

ከቀላል እስከ ከፍተኛ ቀዶ ጥገና መደረግ ባልነበረባቸው ታካሚዎች ላይ ስህተት መፈጸሙን፣አግባብ የሕክምና የጎደለው አገልገሎቱ ማከናወንና ምንነታቸው የማይታወቅ መድኃኒቶችን ያለአግባብ በመርፌ መልክ የሰጡ ባለሙያዎች ላይ የሙያ ፍቃድ እንዲሰረዘ መደረጉን በባለስልጣኑ የጤና ተቋማትና ባለሙዎች ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ገልገሎ ኦልጅራ ናቸው ለአዲስ ሪፖርተር የገለጹት።

ዳይሬክተሩ አክለውም፤ በዋናነት ስህተቶቹ የሚፈጸሙት የአልኮል መጠጥ በምጠጡና፣ ጠጥተው የሕክምና አገልግሎት በሚሰጡ ቸልተኛ ባለሙያዎች ነው። ይህም በመሆኑ ታካሚዎች ለሞት፣ ለከፋ አደጋና ለተጓዳኝ በሽታዎች መጋለጣቸውን አመልክተዋል።

በተደጋጋሚ ከሚስተዋሉ ስህተቶች ውስጥም አላስፈላጊ ቀዶ ጥገና ማድረግና ያለአግባብ የሰውነት ክፍሎች ላይ መድኃኒቶችን በመርፌ መልክ መሰጠት እንደሆነ ዳይሬክተሩ አመልክተዋል።

በተወሰደው እርምጃዎች መሠረትም፤ ዳግም ወደ ሙያው እንዳይመለሱ እንዲሁም የትምህርት ማዕረጋቸው እንዲነጠቅ መደረጉን አንስተው በአርባ አንዱ ባለሙያዎች ላይ እርምጃው የተወሰደው ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ ብቻ መሆኑን አሰረድተዋል።

የችግሩ ገፈት ቀማሾች ለባለሥልጣኑ ቅሬታዎችን ካቀረቡ ወዲህ፤ በተለያዩ የሕክምና ሙያ ዘርፎች አማካኝነት በተወጣጡ ባለሙያዎች ግምገማ ከተደረጋ በኋላ እርምጃዎች ተወስዷል ሲሉም አብራርተዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም፤ በከተማዋ የችግሩን መንሰራፋት ከአቤቱታ አቅራቢዎች በመረዳት በተለየ መልኩ መሰል እርምጃዎች እና የቁጥጥር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

ባለሙያዎችም የሙያ ሥነ-ምግባራቸውን እንዲያከብሩና ነዋሪውም መሰል ድርጊቶችን ሲያስተውል ጥቆማዎችን በመሰጠት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። አቶ ገልገሎ ጉዳያቸው ቅወደ ህግ የተመራ ስለመኖሩ ያሉት ነገር የለም።

ከህክምና አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ሕዝብ ከፍተኛ ቅሬታ እንደሚያነሳ ይታወቃል። በተለይም በግል የህክምና ተቋማት ውስጥ የሚጠየቀው ክፍያ፣ የአገልግሎት ጥራትና ለማሽኖችና ላቦራቶሪዎች ተደምሮ የሚጥየቀው ብር እጅግ የተጋነና፣ ሰዎች ለጤናቸው ከየትም ብለው ይከፍላሉ በሚል የሚከናወን ሙያዊ ዝርፊያ እንደሆነ በስፋት ምሬት ይሰማል።

አዲስ ሪፖርተር ይህን አስመልክቶ ከሙያ ማህበራትና ከሚታወቁ ላቦራቶሪዎች፣ እንዲሁም ከጤና ሚኒስቴር መረጃዎችን እያሰባሰበች ሲሆን በተከታታይ እንደምታቀርብ ከወዲሁ ቃል ተግባለች። ጥቆማና መረጃ ያላችሁ ወገኖች ከስር ባሉ አድራሻዎች የዝግጅት ክፍሉን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናመለክታለን።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በፀረ-ሽብርተኝነት እና በመፈራረስ መካከል ያለቸው ሶማሊያ “ሌላ አፍጋኒስታን?” የአሜሪካና አቋምና የአል-ሸባብ….

አዲስ ሪፖርተር - እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2021 ዓለምን ያስገረመው የአፍጋኒስታን...

የኢትዮጵያ፣ ህንድ እና እስራኤል ስትራቴጂካዊ አጋርነት የቀጠናው ፖለቲካዊ ትኩሳት፤ የኤርትራ መጨማደድ

አዲስ ሪፖርተር - ባለፈው ማክሰኞ በኢየሩሳሌም የተካሄደው የህንድ እና...

ጀርመንና ሕንድ ግንኙነታቸውን ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት አሳደጉ

አዲስ ሪፓርተር - የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ፍሪድሪክ ሜርዝ በሕንድ...

መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ ኬላ ላይ ተያዘ፤ መዳረሻው ሸዋ ሮቢት ነበር

አዲስ ሪፖርተር - መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ...