የአፍሪካ ህብረት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት መካከል የተደረገውን ታሪካዊ የሰላም ስምምነት አደነቀ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የአፍሪካ ህብረት በትላንትናው ዕለት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (ፋኖ-አፋህድ) መካከል ዘላቂ የሰላም ስምምነት ሲፈረም እማኝ መሆኑን፣ ስምምነቱም በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ትልቅ እርምጃ እንደሆነ አመለከተ።

በአዲስ አበባ በተካሄደው የፊርማ ሥነ ሥርዓት፣ አህጉራዊውን ተቋም የወከሉት ክቡር ሰልማ ማሊካ ሀዳዲ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር፣ እንዲሁም የአህጉራት ልማት ባለሥልጣን (IGAD) ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ሞሐመድ አብዲ ዋሬ መገኘታቸው ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ በዝርዝር አስፍሯል።

አፍሪካ ሕብረት በመግለጫው “ታሪካዊ” ያለው ስምምነት ሲከናወን ምክትል ሊቀመንበሯ ባደረጉት ንግግር፣ ሁለቱ ወገኖች ለውይይትና ለሰላማዊ መፍትሔ ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል። ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ በአህጉር ደረጃ ወሳኝ ምዕራፍ እንደሆነም አመልክተዋል።

ክቡር ሰልማ ማሊካ ሀዳዲ “እያንዳንዱ የሰላም ስምምነት በአፍሪካ የመሳሪያዎችን ድምፅ ለማስቆም ህብረቱ ወደ ያዘው ዋንኛ ግብ የሚያቀርብ ነው” ብለዋል።
የሰላም ስምምነት ለፈረሙት ሁለቱም አካላት “እዚህ ቁል ምዕራፍ ላይ በመድረሳቸሁ እንኳን ደስ ያላችሁ” ሲሉ በአፍሪካ ሕብረት ስም የደስታ መልዕት ማስተላለፋቸውን መግለጫው አስታውቋል። አክለውም “ይህ ስኬት ለአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን የሚመሩ መፍትሄዎች ያለውን ኃይል ያሳያል” ሲሉ ገልፀዋል።

የአፍሪካ ህብረት የዚህን ስምምነት አፈጻጸም፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሰላም እንድሰፍን ያለአንዳች ማወላወል ድጋፉን አጠንክሮ እንደሚቀጥልበት መግለጫው አረጋግጧል።

በሌላ በኩል የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ክቡር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ በሩዋንዳ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ክቡር ፖል ካጋሜ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ክቡር ፌሊክስ ትሺሰኬዲ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በደስታ መቀበላቸውን ህብረቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቀዋል። መሪዎቹ የደረሱበት ስምምነት በታላላቅ ሐይቆች አገራት መካከል ዘላቂ ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋት ለማምጣት ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነ ገልጸዋል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በፀረ-ሽብርተኝነት እና በመፈራረስ መካከል ያለቸው ሶማሊያ “ሌላ አፍጋኒስታን?” የአሜሪካና አቋምና የአል-ሸባብ….

አዲስ ሪፖርተር - እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2021 ዓለምን ያስገረመው የአፍጋኒስታን...

የኢትዮጵያ፣ ህንድ እና እስራኤል ስትራቴጂካዊ አጋርነት የቀጠናው ፖለቲካዊ ትኩሳት፤ የኤርትራ መጨማደድ

አዲስ ሪፖርተር - ባለፈው ማክሰኞ በኢየሩሳሌም የተካሄደው የህንድ እና...

ጀርመንና ሕንድ ግንኙነታቸውን ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት አሳደጉ

አዲስ ሪፓርተር - የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ፍሪድሪክ ሜርዝ በሕንድ...

መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ ኬላ ላይ ተያዘ፤ መዳረሻው ሸዋ ሮቢት ነበር

አዲስ ሪፖርተር - መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ...