ኢህአፓ ተጭበረበረ ወይስ አጭበረበረ ፤ ፈቃድ በማያስፈልገው የጎዳና/ የአደባባይ ሰልፍ እያኮበኮብኩ ነው!

Date:

አዲስ አበባን ማተራመስ አይቻልም” አስተዳደሩ

በሆቴል ዲ አፍሪክ የአዲስ አበባ ህዝብ በመጥራት ለማወያየት አቅዶ “ተከለከልኩ” በማለት ቅሬታውን ያሰማው የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ ኢህአፓ በቀጣይ ፈቃድ በማይጠይቀውና በማሳወቅ ብቻ ማካሄድ በሚቻለው የአደባባይ ሰብሰባዎች ላይ አተኩሮ እንደሚሰራ ለአዲስ ሪፖርተር አስታወቀ። ፓርቲው የአዲስ አበባን ሕዝብ ለማወያየት ያዘጋጀው አዳራሽ ለሁለት መቶ ሰዎች በሚል ቀብድ የተከፈለበት ሲሆን፣ አከራዩ አካል የአዲስ አበባ ሕዝብ ስለመጠራቱ አያውቅም።

የኢህአፓ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይስሃቅ እንዳሉት ፓርቲያቸው የጎዳና ላይ ወይም የአደባባይ ስብሰባን ምርጫው ያደረገው ህጉ በሚፈቅደው መሰረት አዳራሽ ለመከራየት ሞክሮ ሊሳካለት ባለመቻሉ ነው። አድራሹን ለማከራየት ውል የገባው ዞላ ዋና ስራ ስኪያጅ በበኩላቸው በድብዳቤ ውሉ እንዲቋረጥ ከተጠቀሰው ውጪ ምንም አዲስ አነገር የለም ባይ ናቸው።

“ኢሕአፓ ሕዝብ ለመሰብሰብ ጠይቆ አዳራሽ ተከለከለ” የሚለው ዜና ኢህአፓ ካሰራጨው መረጃ በመነሳት የመንግስትን አካላት በማውገዝ በተለይም በውጭ አገር የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅትና ቡድን ልሳኖች በስፋት አሰራጭተውታል።

ይህን ተከትሎ አዲስ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይሰሐቅ “ታፍነናል” ሲሉ ሁሉንም መስፈርት አሟልተው ከጨረሱ በሁዋላ አዳራሹን መከላከላቸውን አመልክተዋል።

“ለመሆኑ ፓርቲያችሁ ስንት አባላት አለው?” በሚል ለተጠየቁት ” አያገባችሁም” የሚል መልስ የሰጡት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው፣ ስብሰባው የተጠራው “አዲስ አበባ ትናገር” በሚል እንጂ የፓርቲው ስብሰባ እንዳልሆነ አመልክተዋል።

አዳራሹን ለማከራየት ቀብድ ወስዶ ሌሎች ጉዳዮችን እንዲያሟሉ ሲጠብቅ የነበረው ዞላ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘላለም ገብረህይወት፣ ፓርቲው የአዲስ አበባን ሕዝብ መጥራቱን እንደማያውቁ፣ አዳራሹ 300 ሰዎችን ብቻ እንደሚይዝ፣ የተነገራቸው ለሁለት መቶ ሰዎች የሚሆን ቦታ እንደነበር፣ ያም ሆኖ አሟልተው መምጣት የሚገባቸውን ሁሉ አሟልተው እንዲመጡ በተደጋጋሚ ቢደወልላቸውም ባለመምታታቸው በቢዝነስ ህግ መሰረት አዳራሹ ለሌሎች ደንበኞች መከራየቱን አስታውቀዋል።

አቶ ይስሃቅ እንደሚሉት ከሆነ አዳራሹን ያከራዩት አካላት ለምን ውሉን እንዳቋረጡባቸው ሲተይቋቸው “እንኑርበት፣ ተዉን” በማለት መመለሳቸውን ተናግረዋል። “ይህ ተብሏል? የመንግስት አካላት አስፈራተዋችኋል?” በሚል ቃል በቃል አቶ ይስሐቅ ያሉትን በማንሳት ለጠየቅናቸው አቶ ዘላለም ሲመልሱ ” በፍጹም” ነው ያሉት።

በህዳር 27 ቀብድ ከፍለው የአዳራሽ ውል ስምምነት ማድረጋቸውን በመጠቀስ ዞላ በጻፈው ደብዳቤ፣ በተሰጣቸው ጊዜ ውስጥ ማሟላት የሚገባቸውን ባለሟሟላታቸው ውሉ ተሰርዞ ለሌላ ተከራይ አዳራሹ መሰጠቱን ያመለክታል። ይህን አስመልክቶ አቶ ይሰሐቅ ሲናገሩ የአዲስ አበባ አስተዳደርን ይወቅሳሉ። አስተዳደሩ ለፖሊስ ደብዳቤ ከመጻፉ በፊት ስብሰባው የሚደረግበትን አዳራሽ መጠየቁን ገልጸው፣ ይህ የሆነው የስብሰባው አድራሻ ከታወቀ በሁዋላ ለማስፈራራት እንዲያመች መሆኑን አመልክተዋል። ለፖሊስ ደብዳቤ እንደተጻፈላቸውም ገልጸዋል።

ለአዲስ አበባ አስተዳደር ጥያቄ አቅርበን ” የስብሰባውን ቦታ ሳናውቅ የጸጥታ ጥበቃና አስፈላጊው ትብብር እንዲደረገ ለፖሊስ ሲታዘዘ ለየትኛው አካባቢ ይባልና ይገለጽ ሲሉ?” ጥያቄውን በጥያቄ መልሰዋል። አክለውም የጎዳና ላይ ነውጥ ዕቅድ ለማመቻቸት ጅማሮ በመሆኑ አስተዳደሩ ህኝ የሚጻረር ስራ ከተሞከረ ህግ የማስከበር ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

የዞላ ስራ አስኪያጅ የአዲስ አበባን ሕዝብ ጠርተው የት ሊከቱት ነበር? አዳራሹ የሚይዘው 300 ሰው ብቻ ነው። እነሱ የጠየቁት ለ200 ሰዎች ብቻ ነበር ሲሉ የስብሰባውን ማስታወቂያ ካዩ በሁዋላ መገረማቸውን ለአዲስ ሪፖርተር ተናግረዋል።

በስለማዊ ትግል እንደሚያምን ጠቅሶ የተደራጀው “አብሮነት” የተሰኘው የአቶ ልደቱ ማህበር በሰላማዊ ትግል ስም አገር ቤት ያሉ አንዳንድ ድርጅቶችንና ፓርቲዎችን ወደ ጎዳና በማስወጣት ነውጥ ለማነሳሳት እየሰሩ መሆናቸውን ከሃያዎቹ የአብሮነት አባላት መካከል ሁለቱ ለአዲስ ሪፖርተር መናገራቸውን ተቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

በአብሮነት ውስጥ ሆነው የነፍጥ ትግል የሚያራምዱና፣ ከሻዕቢያ ጋር በግልጽ የሚሰሩት እነ አቶ ነዓምን ዘለቀ፣ በምስራቅ በኩል ኦብነግንና የተበታተነውን የኦነግ ኃይል በማጣመር እንዲያደራጁ የተሾሙት ቡድን መሪው ፕሮርፌሰር ሕዝቅኤልና የሶማሌ ፓርላማ ተመራጭ የተካተቱበት አብሮነት “ይህ መንግስት በጦርነት አይወድቅም። በጎዳና ላይ አመጽ እንረባረበበት” በሚል የያዙት ዕቅድ አካል ይሁን አይሁን ባይታወቅም ኢህአፓ በይፋ የጎዳና ላይ ስብሰባዎችን ማካሄድ እንደሚጀመር፣ ይህንንም ሲያድረግ ከማሳወቅ ባለፈ ፈቃድ እንደማይጠይቅ ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቋል። እናት ፓርቲ ኢህአፓ የያዘውን አቋም እንደሚደግፍ ማስታወቁ አይዘነጋም።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በፀረ-ሽብርተኝነት እና በመፈራረስ መካከል ያለቸው ሶማሊያ “ሌላ አፍጋኒስታን?” የአሜሪካና አቋምና የአል-ሸባብ….

አዲስ ሪፖርተር - እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2021 ዓለምን ያስገረመው የአፍጋኒስታን...

የኢትዮጵያ፣ ህንድ እና እስራኤል ስትራቴጂካዊ አጋርነት የቀጠናው ፖለቲካዊ ትኩሳት፤ የኤርትራ መጨማደድ

አዲስ ሪፖርተር - ባለፈው ማክሰኞ በኢየሩሳሌም የተካሄደው የህንድ እና...

ጀርመንና ሕንድ ግንኙነታቸውን ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት አሳደጉ

አዲስ ሪፓርተር - የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ፍሪድሪክ ሜርዝ በሕንድ...

መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ ኬላ ላይ ተያዘ፤ መዳረሻው ሸዋ ሮቢት ነበር

አዲስ ሪፖርተር - መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ...