ትህነግ ውደ ጦርነት 6.77 ቢሊዮን ብር በግዴታ ለመሰብሰብ ሚስጥራዊ ዕቅድ አወጣ፤ በጦር ጉዳተኞች ስም 1 ቢሊዮን

Date:

ወደ ትግራይ የሚላከውን ነዳጅና ሸቀጥ ወደ ኤርትራ የሚያግዘው ትህነግ የሰለቻቸው የአገር መከላከያ ድንበር እንዲዘጋ እየጠየቁ ነው

አዲስ ሪፖርተር – የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እና የትህነግ አመራሮች፣ በክልሉ ውስጥ ያለውን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ እና የጦር ጉዳተኞችን የህክምና እርዳታ ለማግኘት በሚል ሽፋን፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ገቢ በግዴታ ለመሰብሰብ የሚያስችል ሰነድ አዘጋጅተው ወደ ስራ መግባታቸው ተገለጸ።

የተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ዕቅድ ሰነድ እንደሚያመለክተው፣በአጠቃላይ 6,770,200,000.00 (ስድስት ቢሊዮን ሰባት መቶ ሰባ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል። ይህ ገንዘብ በዋነኛነት የሚሰበሰበው በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የንግድ ተቋማት ላይ ጫና በማድረግና አዳዲስ የገቢ ምንጮችን በመጠቀም ነው።

የዕቅዱ ዓላማዎች እና የገንዘብ ክፍፍል በወጣው ሰነድ መሰረት ፤በአጠቃላይ ሊሰበሰብ ከታሰበው 6.77 ቢሊዮን ብር ውስጥ ፤1,000,000,000.00 (አንድ ቢሊዮን) ብር በትግራይ ሰራዊት የጦር ጉዳተኞች የህክምና እርዳታ ለማዋል ታቅዷል።

5,760,200,000.00 (አምስት ቢሊዮን ሰባት መቶ ስልሳ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ብር ደግሞ የክልሉን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ እና ሌሎች ክልላዊ ዕቅዶችን ለማሟላት ይመደባል።

የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻው በየደረጃው የሚገኘውን የህብረተሰብ ክፍል መሰረት ያደረገ እንዲሆን ተደርጎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ገንዘቡን ለመሰብሰብ በእቅድ ከተያዙት ዋና ዋና ተግባራት መካከል፦በምርቶችና በሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ገቢ ማግኘት።

ከከተሞች የመሬት ሊዝ ሽያጭ ገቢ ማግኘት።

ከባንኮች እና ማይክሮ ፋይናንስ ብድርና ስጦታ (ወፈያ) መቀበል።
ከኢፈርት ድርጅቶች በስጦታ መልክ ገቢ ማግኘት።

ከሆቴሎችና ከአክሲዮኖች በስጦታና በብድር መልክ ገቢ መሰብሰብ።

ከባለሀብቶችና ነጋዴዎች፣ ከግል ትምህርት ቤቶች፣ ከወርቅ ነጋዴዎች፣ በመስኖና በማኒፋክቸሪንግ ከተሰማሩ አካላት ገቢ ማግኘት ይገኙበታል።

የገቢ ምንጭ የሚጠበቀው ገቢ በ28 ከተሞች ከመሬት ሊዝ ጨረታ1,965,000,000.00 ከፋይናንስና ልማት ተቋማት (ባንኮች፣ ሆቴሎች፣ ወዘተ)1,660,000,000.00ከመሰቦ ሲሚንቶ ሽያጭ1,950,000,000.00በቢራ ላይ ከሚደረግ የዋጋ ጭማሪ1,080,000,000.00 ከውስኪ72,000,000.00ሌሎች መጠጦች (ለስላሳ፣ ውሃ፣ ወይን፣ አረቄ)43,200,000.00ጠቅላላ ድምር 6,770,200,000.00።

ይህን ግዙፍና አስገዳጅ ዕቅድ ለመምራት 21 አባላት ያሉት አንድ አቢይ ኮሚቴ እና አራት ንዑስ ኮሚቴዎች መቋቋማቸው ታውቋል።

የዋናው (አቢይ) ኮሚቴ ሰብሳቢ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ሲሆኑ፣ ከዋና ዋና አባላቱ መካከል የኢፈርት ዋና ሥራ አስፈፃሚ (CEO)፣ የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ፣ የንግድ ባንክ፣ አንበሳ ባንክ፣ ወጋገን ባንክ እና ደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ሥራ አስኪያጆች እንዲሁም የተለያዩ የመንግስትና የንግድ ተቋማት ኃላፊዎች ተካተዋል።

የማነቃቃትና የማደራጀት ንዑስ ኮሚቴው ደግሞ የገንዘብ ማሰባሰቡን ለማስፈፀም የህዝብና መንግስት ግንኙነት ኃላፊዎች፣ የመንግስትና የግል ሚዲያዎች፣ ሁሉም የሃይማኖት መሪዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ አክቲቪስቶች፣ ባለሀብቶችና ነጋዴዎችን በዘመቻው ውስጥ እንዲሳተፉ ታቅዷል።

በተጨማሪም በተገኘው መረጃ መሰረት፣ የገንዘብ ማሰባሰቢያው ሰነድ ቢዘጋጅም፣ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ውስጥ አስቸኳይ ህክምና የሚያስፈልገው የTPLF ሰራዊት የሌለ መሆኑ ተጠቅሷል። ይህም የጦር ጉዳተኞች የህክምና ሽፋን የሚለው ሰበብ ለገንዘብ ማሰባሰቢያው ዋና መሸፈኛ እንደሆነ ጥያቄዎችን አጭሯል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ ሪፖርትር የትግራይ ተባባሪ ያነጋገራቸው እንዳሉት ወደ ኤርትራ የሚጋዘው ነጋጅና ሸቀጣ ሸቀጥ ከኮንትሮባንድ አልፎ ህጋዊ መስሏል። ስለሆነም የፌደራል መንግስት ድንበሩን ሊዘጋ ይገባል ብለዋል። ከዚህ ቀደም ያነጋገርናቸው ለፍተኛ መኮንን “ትህነግን ያሞላቀቀው መንግስት ነው። አሁን መከላከያ ቢመጣ ሕዝብ በእልልታ ይቀበለዋል” ማለታቸውን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...