ግብፅና ኢራን የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ላይ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን በዓል እንዳይከበር ለፊፋ ጥያቄ አቀረቡ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ግብፅ እና ኢራን እ.ኤ.አ. በ2026 የዓለም ዋንጫ በሲያትል በሚያደርጉት የምድብ ጨዋታ ላይ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን በዓል እንዲከበር ከተወሰነው ውሳኔ ጋር በተያያዘ የዓለም የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል የሆነው ፊፋ ጣልቃ እንዲገባ መጠየቃቸው ተገለፀ።

የግብፅ እግር ኳስ ማህበር (EFA) ማክሰኞ ዕለት ለፊፋ በላከው ደብዳቤ፣ የግብፅ ብሔራዊ ቡድን በሚቀጥለው ሰኔ ወር ከኢራን ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ወቅት ከተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ጋር የተያያዙ ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች እንዲከለከሉ አሳስቧል።

የግብፅ እግር ኳስ ማህበር ደብዳቤው ላይ እነዚህ ዝግጅቶች በጨዋታው ላይ የሚሳተፉት ሀገራት ካሏቸው “ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጋር የሚጋጩ” መሆናቸውን በመግለጽ ተከራክሯል።

ሰኔ 26 ቀን የሚደረገው ይህ የምድብ ጨዋታ በአካባቢው አዘጋጆች ከሲያትል የኩራት ሳምንት መጨረሻ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች በዓል ጋር እንዲገጣጠም ተደርጎ “የኩራት ግጥሚያ” ተብሎ መሰየሙ ይታወቃል።

የግብፅ እግር ኳስ ማህበር ለፊፋ ዋና ጸሐፊ ለማትያስ ግራፍስትሮም በጻፈው ደብዳቤ፣በጨዋታው ወቅት የ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ማስተዋወቂያ የሆኑ ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች በፍጹም እንደማይቀበል ገልጿል፤ እንደነዚህ ያሉት ዝግጅቶች በደጋፊዎች መካከል ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ስሜቶችን ሊጎዱ” እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።

ማህበሩ አክሎም እነዚህ እንቅስቃሴዎች በተለይም በአረብ እና በእስላማዊ ማህበረሰቦች ውስጥ ካሉ በየሀገራቱ ካሉ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ እና ማህበራዊ እሴቶች ጋር በቀጥታ ይጋጫሉ።

ኢራን በበኩሉ የግብፅን ሀሳብ እንደምትደገፍ አስታውቃለች።በኢራን ውስጥ፣ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በሞት የሚያስቀጣ ቅጣት ሲያስከትል፣ በግብፅ ደግሞ የሞራል ህጎች የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ሰዎችን ለመክሰስ ያገለግላሉ።

የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊ የሆኑት መህዲ ታጅ፣ ቴህራን እና ካይሮ በጉዳዩ ላይ ተቃውሞዎችን እንዳቀረቡ የአካባቢው የዜና ወኪል ISNA እንደዘገበው ተናግረዋል። እርሳቸውም ይህንን አንድ የተወሰነ ቡድንን የሚደግፍ ምክንያታዊነት የጎደለው እርምጃ ሲሉ ፈርጀውታል።

ዝግጅቱ የተዘጋጀው በአካባቢው ኮሚቴ ሲሆን ከፊፋ ጋር የተገናኘ እንዳልሆነ ታውቋል።

ፊፋ በ2022ቱ የዓለም ዋንጫ በኳታር፣ የእንግሊዝና ዌልስን ጨምሮ በርካታ ቡድኖች የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን መብቶችን ለመደገፍ ያቀዱትን አንድ ፍቅር (OneLove) የእጅ ማሰሪያ እንዳይለብሱ በማስጠንቀቅ፣ ከተጠቀሙ ቢጫ ካርድ እንደሚጠብቃቸው መግለጹ ይታወሳል።

ፊፋ ከግብፅ እና ኢራን በቀረበው ይፋዊ ጥያቄ ላይ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም። የዓለም ዋንጫን በስፖርት ላይ ብቻ ለማተኮር በሚል አቋም እና የሲያትልን የማህበረሰብ እሴቶች በሚያንጸባርቀው በአካባቢው አዘጋጆች እቅድ መካከል ያለው የፊፋ ምላሽ በጉጉት ይጠበቃል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር እስከዳር አመጽ ለማቀጣጠል በተጠራው ስብሰባ “አስቻይ ሁኔታ የለም ተባለ” ጃዋር በድጋሚ አፈገፈገ

"በዋሽንግቶን ዲሲና ሎንዶን አገር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ...

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...