የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስቴር “ታሪካዊ” ጉብኝት በኢትዮጵያ፤ ነገ በፖርላማ ንግግር ያደርገጋሉ

Date:

በዲፕሎማሲያዊ ትስስራቸው 75 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ እና ህንድ ግንኙነት ዛሬ አዲስ ምዕራፍን ይዟል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን በጉዞውም ወቅት ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ ሞዲን በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም እና በወዳጅነት ፓርክ ውስጥ በይፋዊው የጉዞ መርሃ ግብር ውስጥ ያልተካተቱ ፌርማታዎችን አስጎብኝቷቸዋል።

በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ረኢ”ታሪካዊ ጉብኝት” ብለው የሰየሙት የህ ታላቅ የዲፕሎማሲያዊ ትስስር ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነቷን ለማጠናከር እና በተለወጠው ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት ውስጥ ሚናዋን እንደገና ለመወሰን በምትራመደው እርምጃ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተገልፇል።

የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ የተስተናገደው ጉብኝቱ ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ እድገት፣ በቴክኖሎጂ እና በ”south south” ትብብር ላይ ያተኮረ የልማት አጋርነት ቁርጠኝነትን በማሳየት በ BRICS እና በሰፊው “Global south” ውስጥ እያደረገች ያለውን አቋም እንደሚያጠናክርም ይጠበቃል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በነገው ዕለት በፓርላማ ንግግር እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ እንደገለጹት፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) መካከል የሚካሄደው የውይይቱ ቁልፍ አጀንዳዎች፡

  • ኢንቨስትመንትና ማኑፋክቸሪንግ፡
    ሕንድ ለኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ዋና ምንጭ በመሆኗ፣ በትብብር የሚተገበሩ የማኑፋክቸሪንግ እና የልማት ዕድሎችን ማሳደግ።
  • ግብርናና ማዕድን ልማት፡
    የኢትዮጵያን የግብርና ትራንስፎርሜሽን እና የማዕድን ዘርፍ ልማት በህንድ ተሞክሮዎችና ኢንቨስትመንት መደገፍ።
  • ዲጂታል መሠረተ ልማት እና ሳይበር ደኅንነት:
    በዲጂታል ዘመን ያሉትን የጋራ ስጋቶች ለመከላከል እና የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማጠናከር በትብብር መሥራትን ያካትታል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ጉብኝት ባለፉት 10 ዓመታት የሕንድ መሪ ምሥራቅ አፍሪካን ሲጎበኝ የመጀመሪያው ነው።

Website፡ https://addisreporter.com/

Email፡ info@addisreporter.com

Telegram፡ https://t.me/addisreporter11

X፡ https://x.com/addisreporter

Phone no ፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

Egypt’s Red Sea Signal: Opening the Door to a Historic Nile Agreement with Ethiopia

"sources like The National indicating Egypt's conditional openness to...

አብን በሁመራ፣ አዲረመጥ፣ ኮረም ኦፍላ፣ ጠለምት ራያና አላማጣ ሕዝቡ ለክልልም ምርጫም መሳተፍ አለበት አለ

አዲስ ሪፖርተር - "ህዝባችን ለክልሉ ምክርቤት ጭምር ምርጫ መካሄድ...

“ለዓመታት የፖለቲካ መብታቸው ተገፎ ለኖሩ ዜጎች የዲሞክራሲ ጭላንጭል የፈነጠቀ ታሪካዊ እርምጃ” ወልቃይት

አዲስ ሪፖርተር - የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን ኮሚቴ...

“ለአራተኛ ጊዜ ተወረናል” ከወሎ ራያ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ከሚቴ የተሰጠ መግለጫ

አዲስ ሪፖርተር - "መንግሥትም የህዝቡን የማንነት እና የራስ አስተዳደር...