ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ኢትዮጵያን እና ህንድን የደረሱበትን ስምምነቶች ይፋ አደረጉ፤

Date:

ታሪካዊ የተባለ ጉብኝት፣ ታሪካዊ በሆነ የአቀባበል ስነ ስርዓት የጀመሩት የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያና በህንድ መካከል ተደረሱባቸው ያሉትን ስምንት የስምምነት ዓይነቶች ይፋ አድርገዋል። በአቀባበሉ እርካታ እንደተሰማቸው ከፊታቸው ላይ ሲነበብባቸው የነበሩት የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በክቡር ዘብ በፈረሰኞች ታጅበው ሲታዩ ኢትዮጵያ ወደ ቀደመው ክብር መመለሷና እንግዳ አቀባበል የምታውቅ አገር እንደሆነች ያመላከተ መሆኑም ዜጎችን አስደስቷል።

በሌሎች አገራት በሚደረግ ልዩ የክብር አቀባበል ሲደነቁ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ከክብር ዘቡ ቁመና፣ አካሄድ፣ ሞገስና ኢትዮጵያን ለማጉላት የተላበሱትን መለያ የተመለከቱ ዜጎች አድናቆት ሰጥተዋል። በተለያዩ የርማህበራዊ ገጾች ላይ እንደተስተዋለው ቀደም ሲል ተራክሶ የነበረው የቤተመንግስት ክብር፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ማዕረግ ከፍ ማለቱን በሚያሳይ መልኩ ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የተደረገው አቀባበል እንደዜጋ የሚያኮራ መሆኑን ያመለከቱ ጥቂት አይደሉም። እንግዳውም ፍጹም ደስታ እንደተሰማቸው አመልክተዋል። ለክብራቸው በተደረገው የእርታ ግብዣ ላይ በአገራቸው ቋንቋ ባደረጉት ንግግር የተደረገላቸውን አቀባበል፣ የተበረከተላቸውን የክብር ሽልማት፣ እንዲሁም ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ያደረጉትን ውይይት እስከመቼውም ያማይረሳ ነው ያሉት።

ታሪካዊ የተባለውን ጉብኝት የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ህንድ እና ኢትዮጵያ በትምህርት፣ በፈጠራ፣ በጤና አጠባበቅ እና በኢኮኖሚ ማገገሚያ ላይ ያተኮሩ ስምንት ዋና ዋና ውጤቶች ላይ መስማማታቸውን በይፋዊ የትዊተር(X) ገፃቸው አስፍረዋል። ኢትዮጵያ እና ህንድ ታሪካዊ ወዳጅነታቸውን ወደ ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማሸጋገር መወሰናቸው ትክክለኛ እርምጃ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።

1️⃣ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ከፍ ማድረግ

2️⃣ ንግድን ለማሳለጥ እና የቁጥጥር ቅንጅቶችን ለማሻሻል ያለመ በጉምሩክ ጉዳዮች የትብብር እና የጋራ አስተዳደራዊ ድጋፍ ስምምነት

3️⃣ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳታ ማዕከል ለማቋቋም የመግባቢያ ሰነድ አሃዛዊ እና ተቋማዊ አቅምን ማጠናከር

4️⃣ በተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ስራዎች ስልጠና ላይ የትብብር ዝግጅትን ተግባራዊ ማድረግ እና በአለም አቀፍ የሰላም ጥረቶች ትብብርን ማጎልበት

5️⃣ በG20 የጋራ ማዕቀፍ መሰረት ለኢትዮጵያ የዕዳ መልሶ ማዋቀር የመግባቢያ ሰነድ መፈረም እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ማረጋጋት

6️⃣ በICCR ፕሮግራም ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ስኮላርሺፕ በእጥፍ ማሳደግ፣ የትምህርት እድሎችን እና የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ማስፋት።

7️⃣ በ ITEC ፕሮግራም ስር ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች እና ባለሙያዎች በ”አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ”(AI) ልዩ የአጭር ጊዜ ኮርሶችን መስጠት እና

8️⃣ ህንድ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የማህተማ ጋንዲ ሆስፒታልን አቅም ለማሳደግ በተለይም በእናቶች ጤና አጠባበቅ እና በአራስ ህጻን እንክብካቤ ላይ ያለውን ድጋፍ ለማሳደግ መሆናቸውን ገልፀዋል።

እነዚህ ስምምነቶቸ‍እ በጋራ እሴቶች ላይ የተገነባ እና ፣ ህዝብን ያማከለ እና ልማት ላይ ያተኮረ የህንድ እና ኢትዮጵያ አጋርነትን የሚያንፀባርቅ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ እና ህንድ ታሪካዊ ወዳጅነታቸውን ወደ ስትራቴጂካዊ ትብብር ምዕራፍ ለማሸጋገር መወሰናቸው ትክክለኛ እርምጃ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ውይይት ካደረገኡ በሁዋላ የመንግስት መገናኛዎች እንዳሉት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ እና ህንድ ያላቸው የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።ሁለቱ አገሮች ጥልቅ ወዳጅነት፣ ትብብር እና በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንዳላቸው አመልክተዋል።

የህንድ አቋም ከኢትዮጵያ የልማት ጉዞ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ገልጸው የአፍሪካ እና ህንድ አጋርነት አፍሪካ ባለቤት የሆነችበት፣ አፍሪካ መር እና በአፍሪካ ፍላጎቶች ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት አመልክተዋል።
ውይይቱ ኢትዮጵያ እና ህንድ በሉዓላዊነት፣ ራስን መቻል እና የተግባር ትብብር ላይ የተመሰረተውን ዘመናዊ አጋርነት የበለጠ ማጠናከርን ያለመ ነው ብለዋል።

የሁለትዮሽ ትብብሩ በእኩልነት እና የደቡብ ደቡብ አጋርነት መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም እና የህንድ የኢኮኖሚ ማዕቀፍ ብሄራዊ አቅም፣ ሁሉን አቀፍ ልማት እና ነጻነት ያከበረ አጋርነት ላይ የተመረኮዙ መሆናቸው ያላቸውን የጋራ መጣጣም እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በጠንካራ ሁኔታ እያደገ እንደሚገኝ ገልጸው በ2017 ዓ.ም የ9 ነጥብ 2 በመቶ ጥቅል ሀገራዊ እድገት (ጂዲፒ) መመዝገቡን ገልጸዋል። በ2018 ዓ.ም 10 ነጥብ 3 የጂዲፒ እድገት ይመዘገባል ተብሎ እንደሚጠበቅም አመልክተዋል።

ከኢኮኖሚ እድገቱ በተጨማሪ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን ገልጸው ህንድ የኢንቨስመንት ፍሰቱ መሪ ምንጭ ናት ብለዋል።
ከ615 በላይ የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

በተለያዩ መስኮች ያለው ግንኙነት እያደገ መምጣቱ በመተማመን ለተመሰረተው ለሁለቱ ሀገራት ትብብር ጠንካራ መሰረት እንደሚጥል ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና ህንድ ታሪካዊ ግንኙነታቸውን ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሳደግ መወሰናቸው ትክክለኛ እርምጃ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣታቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልጸው ቆይታቸው ፍሬያማ አንዲሆን ተመኝተዋል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእናት ሀገር ጥሪ ተሳትፎና ኮሎኔል መንግሥቱ

የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ...

ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ፤ ኢትዮጵያን ወደ መፃኤ ዘመን የሚያሻግር የሎጂስቲክስ አብዮት

ኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ ሰማይ ስር የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ካርታዋን እንደገና ለመሳል...

“ጥርስ የሌለው ውሻ” የሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም መፃኢ እጣፈንታ

አዲስ ሪፖርተር - ፕሬዛዳንት ትራምፕ አሜሪካን ከተባበሩት መንግስታት ደርጅት...

በዘመነ ትራምፕ ጫና ውስጥ የወደቀችው ሶማሊያ እና ለሶማሌ ላንድ ተስፋን ያለመለመው አዋጅ

አዲስ ሪፓርተር - ከሶማሌላንድ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና ከእስራኤል እውቅና...