አዲስ ሪፖርተር – በተላያዩ ወቅቶች ሕዝብ “ግራ የሚገን” በሚል የሚያነሳው ጥያቄ ወደ አንድ መስመር እያመራ ይመስላል። አንዳንድ ዜጎች ጥቆማ እንዳይሰጡ ምን አልባትም ጥቆማው በቢሮ ውስጥ ላሉ የሽፍታ መዋቅር አባላት ሊሆን ስለሚችል እንደሚሰጉ ይናገሩ ነበር። አዲስ ሪፖርተር ይህን የሕዝብ ስጋት በማንሳት በተደጋጋሚ መረጃ ለመስጠት ሞክራለች።
ሰሞኑን በሰላም ድርድር ወደ ሰላም መንገድ የመጡት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ “ቃኜ” የሚባል ከወረዳ እስከ ፌዴራል የተዘረጋ የፋኖ አደረጃጀት እንዳለ ይፋ አድርገዋል። ይህ መረብ ማንኛውንም መረጃ ወደ ጫካ በተዋረድ እያደረሰ እንዲደረግ የሚፈለገውን ሁሉ የሚያስደርግ ነው።
ብቸና የሚኖሩ የአዲስ ሪፖርተር ያነጋገራቸው “ሁሉንም ነገር የሚያካሂዱት በገሃድ ነው። መቼ መካለክያ እንደሚነቃነቅ ሳይቀር ይነገራቸዋል። አንድ ጊዜ የመከላከያን እግር ጠብቀው ብቸና ገቡ፣ መከላከያ እንደሚመጣ ሲነገራቸው መጡ እያሉ የሚፈልጉትን ይዘው ሄዱ” የሚል ዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ “አማራ ክልል ንብረቱ የሸጠ ሰው ወዲያውኑ ከባንኮች በሚሰጥ ጥቆማ ይታገታል”
በባህር ዳርና ዙሩሪያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ደግሞ ንብረት የሸጠ ሰው ወዲያው እገታ ስለሚደርስበት ንብረት መሸጥ መለወጥ ቆሟል። ከባንክ መረጃ የሚያቀብሉ ስላሉ አንድ ሰው ንብረት ሲሸጥ ማታውኑ ቤቱት ሰተት ብለው ይገባሉ። ማስረሻ ሰጤ ይፋ ያደረጉት እገታ በዚሁ መዋቅር በቅንብርና በቅንጅት የሚሰራ ከዘረፋ በላይ ሌላ ዓላማ ያለው ተግባር ነው።
ይህ የዝርፊያ መረብ ድርድሩ እንዳይሰካ ከፍተኛ እንቅፋት ፈጣሪ እንደነበር ያወሱት ማስረሻ ሰጤ በኢቢሲ በኩል ዝርዝር በሰጡት ማስረጃ የመርመራ ስራ እንዳይበላሽ ብዙውን ጉዳይ እንዳላነሱ አመልክተዋል። አክለውም “ መንግስት ያስብበት” ሲሉ አሳስበዋል። አስፈላጊውን በዳታ የተደገፈ መረጃ በመስጠት እንደሚተባበሩም አመልክተዋል።
አጋቾች፣ ዘራፊዎች የመንግስትን የሚታወቁ የገንዘብ ትቋማትና መደበኛ ስልክ እየተጠቀሙ ዝርፊያ በገሃድ እየፈጸሙና ንብረት እያፈሩ መሆኑ ስለሚታወቀ “ በመግስት ባንኮች፣ በመንግስት ስልኮች፣ በመንግስታዊ መዋቅሮች ተጠቅመው የሚዘርፉትን እንዴት መንግስት ዝም አላቸው። መንግስት ሆነ ብሎ ነው የሚፈቅድላቸው” በሚል ሲቀርብ የነበረውን የሕዝብ ምሬት “ቃኜ” የሚባል አደረጃጀት እንዳለ ይፋ በማድረግ ማሰረሻ ሰጤ ምላሽ ሰጥተዋል።
ዘመነ ካሴንና እስክንድር ነጋን በቁጥጥር ስር ካዋሉ በሁዋላ እንዲለቀቁ ያደረጉ ኃላፊ በዝምታ ታልፎ ዛሬ በድግስና በአንዳንድ ከፍተኛ ዝግጅቶች ላይ በሚታዩ የረዥም ጊዜ የክልሉ ባለስልጣናት ላይ ሕዝብ ማፍጠጥ ከጀመረ መቆየቱን የሚጠቁሙ፣ “አሁን መንግስት ስራውን ሊሰራ ይገባል” ሲሉ እየጠየቁ ነው።
በዕገታና ዘረፋ መረብ ተሳስረው የሚዘርፉና ልዩ ተልዕኮ ያላቸው ባለስልጣናትና የበታች አመራሮች በክልሉ ሰላም ከወረደ ተጠያቂ ስለሚሆኑ ድርድርና የሰላም አጀንዳን እንደሚያጨናግፉ አስቀድሞ በግርድፉ መዘገቡ አይዘነጋም።
ለውጡን ተከትሎ ባህር ዳር ቢሮ ከፍቶ የነበረውና ሰላዮቹን አሰማርቶ የዘረፋና የትርምስ መረባ ማደራጀቱን አዲስ ሪፖርተር ኢትዮሪቪውን ጠቅሳ መዘገቧ አይዘነጋም።
ለውጡን ተከትሎ በተፈጠረው የሰላም በር የገባው ሻዕቢያ ወደ አዲስ አበባ ካሰማራቸው ሰላዮቹ መካከል አንዱ የሆነውና መንግስት “በቃኝ” በማለት ወደ ኤርትራ እንዲመለሱ ካዘዛቸው መካከል አንዱ የሆነውና ኤርትራ ሳይመለስ ወደ ዱባይ ያቀናው ሰላይ ቀደም ሲል በባህር ዳር ቢሮ ከፍተው እንደነበር አመልክቶ ነበር።
“በአማራ ክልል አስተዳደር ውስጥ ነበርንበት” ያለው ይህ ሰላይ ለአዲስ ሪቪው ከሁለት ዓመት በፊት እንዳስታወቀው አዲስ አበባ ያለው የኤርትራ ኤምባሲ የስምሪቱ ማዕከል እንደነብርና ከአማራ ክልል ባለሃብቶች ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንደነበር ያመለከተው ሰላይ፣ አምባሳደሩ ቀን በቀን ማለት በሚቻልበት አግባብ ባህር ዳር ይመላለሱ እንደነበር ጠቋሟል። ዝርዝር ዘገባ ይኖረናል።
Website፡ https://addisreporter.com/
Email፡ info@addisreporter.com
Telegram፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
Phone no ፡ +251981866434 / +251116393393






