የኢሳያስ ኤርትራ ዳግም ወደ ማዕቀብና አሸባሪነት ፍረጃ! “ከሻዕቢያ ጋር አብረው የሚሰሩ ወገኖቼ እጣ ፈንታ ያሳስበኛል”

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ኢሳያስ የሚመሯት ኤርትራ ዳግም ወደ ማዕቀብና የአሸባሪነት ፍረጃ ውስጥ ልትገባ እንደምትችል ተቀማጭነታቸው በአውሮፓ የሆነ ዲፖሎማትን ጠቅሶ የኦስሎ የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ አስታወቀ። በቀጠናው ኢሳያስን እየገፉ ያሉ ምልክቶች ተበራክተዋል። “ከሻዕቢያ ጋር አብረው የሚሰሩ ወገኖቼ እጣ ፈንታ ያሳስበኛል” ሲሉ ስጋታቸውን ለአዲስ ሪፖርተር የገለጹ አሁን ላይ የሚታዩት በርካታ ምልክቶች በጥንቃቄ ሊመረመሩ እንደሚገባም መክረዋል።

የአፍሪካ ቀንድ ጂኦፓለቲካ በከፍተኛ ደረጃ እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ለአሥመራው መንግስት መጪው ጊዜ እጅግ የጨለመና አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳዩ ግልጽ መረጃዎች እየወጡ እንደሚገኙ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ መገናኛዎች እያዘገቡ ነው። እነዚሁኑ መረጃዎች በመጥቀስ ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኞች ሰክነው የፖለቲካውን አካሄድ ሊመረመሩ እንደሚገባ ይመክራሉ።

የኦስሎ ተባባሪያችን ከስፍራው እንዳለው ዲፕሎማቱ ይህን ያሉት አውሮፓ በአፍሪቃ ቀንድ ትርምስ እንዲኖር ከቶውንም ያምትፈቅድበትን መሰረታዊ ምክንያት ሲያስረዱ ነው። ” እኛ” አሉ ዲፕሎማቱ አውሮፓን ለማለት ነው፣ “እኛ እገሌ ከገሌ ሳንባል ጥቅል አውሮፓ በቀይ ባህርና በመላው የምስራቅ አፍሮቃ ትርምስ እንዲፈጠር አንፈቅድም። ትርምስ ከተፈጠረ በስደተኞች ማዕበል የምነመታውና በቀይ ባህር የንግድ መስመር መስተጓጎል መከራ ተቀባዮች ነን። ስለዚህ በየትኛውም ምድራዊ ሂሳብ የቀጠናውን ሰላም ከሚረብሹ ጉዳዮች ጋር ሕብረት የለንም”

የኤርትራን መንግስት አስመልክቶ ወቅታዊ ሪፖርቶች በሚቀርቡባቸው ከፍተኛ ስብሰባዎች ላይ መገኘታቸውን ያመለከቱት ዲፕሎማቱ፣ “አምባገነን” ያሉት የፕሬዚዳንት ኢሳያስ መንግስት ቀደም ሲል ወደ ነበረበት ማዕቀብ፣ ከዚያም ሲያልፍ አሸባሪነት ሊፈረጅ የሚችልበት አግባብ ስለመድረሱ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ይህን አስመልክቶ ምን እየሰራች እነድሆነና ይህ እንዲወሰን የሄደችበትን ርቀት አስመልክቶ የሚያውቁት ጉዳይ እንዳለ ተጠይቀው፣ “ኢትዮጵያ አርፋ ትቀመጣለች ብዬ አላስብም። ከዓለም ታላላቅ አገራት ጋር ባላት ግንኙነት ተጠቅማ የኢሳያስን መንግስት አጥብቂኝ ውስጥ ለመክተት የምትቦዝን አይመስለኝም” ሲሉ ዲፖሎማቱ አመልክተዋል።

“አሁን ግን ጉዳዩ የአውሮፓ ህልውና ጉዳይ ነው” ያሉት እኚሁ ዲፕሎማት፣ “ለአንድ አምባገነን ብሎ 130 ሚሊዮን ሕዝብ እንዲበተን የሚፈቅድ ዕድብ መሪና ፖለቲከኛ አውሮፓ ውስጥ የለም። ጉዳዩ ብሄራዊ ጥቅም ነው” ያሉት ዲፕሎማቱ ” ኢሳያስ አፉወርቂን ሽሽት የተሰደዱ የኤርትራ ዜጎች በመላው ዓለም በተለይም አውሮፓን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈሉ ነው። እዚህ ላይ ሌላ ተጨማሪ ኪሳራ አይፈቀድም” ብለዋል። አክለውም ሰሞኑን በኢሳያስ ደጋፊ ስደተኛ ኤርትራዊያን ላይ የተጀመረው ጠንከር ያለ ቁጥጥርና እገዳ ከዚሁ የመነጨ እንደሆነም አመልክተዋል።

“የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ለዓመታት በቀጠናው የነበረው ግጭትና ሴራ የመጥመቅ ፖለቲካ አሁን ላይ በኃያላን ሃገራትና በጎረቤት ሀገራት የተቀናጀ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ምክንያት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየተቃረበ ይመስላል” የሚሉት ደግሞ በዛው በኖርዌይ የሚኖሩ አስተማሪ ናቸው።

መምህሩ እንደሚሉት በተለይም ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር እንደ ስትራቴጂካዊ አጋር ሲጠቀሙባቸው የነበሩት ሃገራት ፊታቸውን ወደ አዲስ አበባ ማዞራቸው ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ የመጀመሪያው የሽንፈት ደወል ነው።

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ የዓባይ ወንዝ ጉዳይን በንግግር ለመፍታት ያላቸው ዝግጁነትና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ በቅርቡ በአዲስ አበባ ያደረጉት ጉብኝት፣ አሥመራ በቀጠናው የነበራትን ግጭትን መሰረት ያደረገ “ከፋፍለህ ግዛ” ሚና ክፉኛ እንዳዳከመው እኚሁ ለጊዜው ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት መምህር አመልክተዋል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የእናት ፓርቲ አመራር እንዳሉት “በኢሳያስ ላይ ዲፕሎማሲያዊ አጣብቂኝ ይበልጥ የከረረው የምዕራባውያን ኃይሎች በኤርትራ መንግሥት ላይ በያዙት ጠንካራ አቋም ነው። አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና የአውሮፓ ሕብረት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በኩል ያስተላለፉት ‘ከሻዕቢያ ጋር በመተባበር ዳግም ጦርነት እንዳይከፈት’ የሚለው ቀጭን ትዕዛዝ፣ የኢሳያስን ሴራ አጋልጦታል።

በፓርቲያቸው ህገ ደንብ መሰረት የኢትዮጵያ መንግስትን የሚደግፍ መረጃ መስጠት ክልክል በመሆኑ ስማቸውን የሸሸጉት እኚሁ የእናት ፓርቲ አመራር፣ ሰሞኑን እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችና ውሳኔዎች ኤርትራ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ላይ ያላትን ጣልቃ ገብነት ለማስቆም የተወሰነ ዓለም አቀፍ ውሳኔ አድርገው እንደሚወስዱት አመልክተዋል።

በጎረቤት ሱዳን ለወራት የዘለቀው ጦርነት በአሜሪካ ግፊት በሁለት ሳምንታት ውስጥ ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት ያመራል ተብሎ መጠበቁ፣ ኢሳያስ ከሱዳን አለመረጋጋት ሊያተርፉ የነበረውን ዕድል እንዳመከነባቸው ውሳኔውን ተከትሎ አስተያየት እየተሰማ ነው።

የኦስሎ ተባባሪያችን ባሰባሰበው መረጃ ከቀይ ባሕር ፖለቲካና ከመካከለኛው ምስራቅ አጋሮች አንፃርም ቢሆን፣ ለአሥመራው አገዛዝ የሚበጅ ዜና እየተሰማ አይደለም። እንደ ሳውዲ አረቢያ፣ ኳታር እና ኢራን ያሉ ሀገራት የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር የመመለስ ፍላጎት ለቀጠናው ዘላቂ ሰላም ወሳኝ መሆኑን መቀበላቸው ለኤርትራ መንግሥት ትልቅ ራስ ምታት ሆኗል።

“ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በቅርቡ በሳውዲ አረቢያ በነበራቸው ቆይታ የጅዳን ስምምነት እንዲያከብሩ የተሰጣቸው ጥብቅ ማስጠንቀቂያ፣ ቀደም ሲል የነበራቸው የባሕረ-ሰላጤው ሃገራት ድጋፍ ማብቃቱን በግልጽ ያሳያል።” ያሉም አሉ። አሁን ባለው ሁኔታ አሥመራ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገለለችና ስትራቴጂካዊ ወዳጆቿን እየከሰረች እንደሆነ በርካታ አመላካች ጉዳዮች መኖራቸው በየአቅጣጫው እየተሰማ ነው።

“የዓለም ኃያላን ሀገራት ባልተለመደ ሁኔታ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያላቸው የአቋም አንድነት የኢሳያስን አገዛዝ መጨረሻው መቃረቡን ያሳያል። እንደ አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ እስራኤልና ቱርክ ያሉ ተቃራኒ ፍላጎት ያላቸው ሃገራት ከኢትዮጵያ ጎን መቆማቸው ለኤርትራው አምባገነን መሪ ዱብእዳ ሆኖበታል” የሚሉት የእናት ፓርቲ አመራር ይህ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም አንጻር ታላቅ ድል ነው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአሜሪካ ጥላ ሥር በጋዛ ሰላም ለማስከበር ይሰማራል ተብሎ የሚጠበቀው መረጃ፣ የኢትዮጵያን ወታደራዊ ተሰሚነት ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ነው። ይህ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ የሚያሳየው አንድ እውነት ቢኖር፣ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የቀጠናው “አዋኪነት” ሚና ማክተሙንና መጪው ጊዜ ለሥርዓቱ እጅግ ጨለማና አስፈሪ ስለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ የሚናገሩት የኦስሎው መምህር “ስጋቴ ከኤርትራ አገዛዝ ጋር አብረው እየሰሩ ላሉት ወገኖች ነው” ሲሉ ኤርትራ ላይ የሚጣል ማናቸውም ፖለቲካዊ ውሳኔ ጠባሳው እነሱንም እንዳይነካ ያላቸውን ፍርሃቻ ይገልጻሉ።

ሰሞኑን ወደ ሰላማዊ መድረክ የመጡት የአህፋድ አመራር ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ፣ ሻዕቢያ የተከፋፈለውን የፋኖ አደረጃጀት ለትርምስ ተግባር እንዴት እንደሚጠቀምበት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ካፒቴኑ ይህንኑ የሻዕቢያ ውጥንና ተግባር ለአፍሪካ ህብረት፣ ለኢጋድና ለአውሮፓ ወኪሎች በዝርዝር ማሰረዳቻውን መግለጻቸው ይታወሳል።

ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ የሚመሩትን ኃይል ይዘው ወደ ሰላም ሲመጡ ” አንድ ሰው መግባቱ ፋኖ ወደ ሰላም መንገድ እንደመጣ አያሳይም” በማለት የኤርትራው የወሬ ሚኒስትር በግል ቲውተር ገጻቸው ማተማቸው፣ ይህንኑ ተከትሎ ኤርትራ ኢጋድን ወቅሳ ከህብረቱ መውጣቷ ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች መሆኑን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

ወደ ኢጋድ ከተመለሰች ጀምሮ አንድም ቀን በስብሰባም ሆነ በማናቸውም ጉዳዮች ከኢጋድ ሕዝብረት ጋር አለመስራቷን ጠቅሶ “አዝኛለሁ” ያለው ኢጋድ፣ የምስራቅ አፍሪቃ ቀንድን ሰላም ማስጠበቅ ቀዳሚ አጀንዳው በመሆኑ፣ ኤርትራን ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ማዕቀብ ጥሎ ለአፍሪካ ህብረትና ለዓለም አቀፉ ሕብረት ሊያቀብላት እንደሚችል ግምት የሚያኖሩ፣ “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር/ ትህነግ በአውሮፓና አሜሪካ ‘አርፈህተቀመጥ፣ ከሻዕቢያ ጋር የጀመርከውን ግንኙነትና የጦረነት ዝግጅት አቁም” መባሉ ከጀርባው ከፍተኛ የአካሄድ ለውጥ መሆኑን ነው። ከምንም በላይ ” ወደ ኢትዮጵያ ብትመለሱ ምንም አትሆኑም” በሚል አሜሪካ ለኢትዮጵያዊያን የሰጠችውን ጊዜያዊ ከለላ ማንሳቷና ኤርትራ ከለላ ለተነሳባቸው አስመራ ኑና ተቀመጡ” ማለቷ በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች ስለመኖራቸው አመላካች ነው።

ኢሳያስ አፉወርቂ ቀደም ባሉት ዓመታት ወይም እስከ ለውጡ ድረስ ለአልሸባብ ጦር በማስሰልጠንና መሳሪያ በማመላለስ ክስ ቀርቦበት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ማዕቀብ ተጥሎባቸው እንደነበር አይዘነጋም። በወቱ የአፍሪቃ ቀንድን ለማተራመስ ሲሰራ የነበረው ሻዕቢያ በቅርቡም ከየመን ሃውቲ ጋር ግንኙነት እንዳለው ታዋቂ የእስራኤል ሚዲያ መዘገቡን የሚገልጹ አገር ወዳዶች “ሻዕቢያ እያለ ኢትዮጵያ በምንም መልኩ ሰላም ማደር ስለማትችል፣ ሻዕቢያ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ነገ ሳይል ሊሰራ እንደሚገባና ከሻዕቢያ ጋር በግልጽ የሚሰሩትን በፓርላማ ከወዲሁ በአሸባሪነት ሊፈርጅ ይገባል” ይላሉ። ይህን አስመልክቶ አስተአየታቸውን ለማካተት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።

Website፡ https://addisreporter.com/

Email፡ info@addisreporter.com

Telegram፡ https://t.me/addisreporter11

X፡ https://x.com/addisreporter

Phone no ፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር እስከዳር አመጽ ለማቀጣጠል በተጠራው ስብሰባ “አስቻይ ሁኔታ የለም ተባለ” ጃዋር በድጋሚ አፈገፈገ

"በዋሽንግቶን ዲሲና ሎንዶን አገር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ...

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...