የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ቀባአዴድ) የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን በዝርዝር አስረዳ
አዲስ ሪፖርተር – የኤርትራ ጦር ወደ አፋር ክልል ድንበር አካባቢዎች ሰርጎ በመግባት ወታደራዊ ትንኮሳ እየፈጸመ መሆኑን ተገለጸ። ዜናው ትህነግ “ትዕግስቴ አልቋል” በማለት መግለጫ ከማሰራቸቱ ጋር የተናበበ እንደሆነ ተመልቷል። የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ቀባአዴድ) ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። ከክልሉ ከሚወጡ መረጃዎች ለመረዳት እንደተቻለው የኤርትራ ጦር ሰርጎ እየገባ ትንኮሳ የፈጸመባቸው ዋና ዋና አካባቢዎች በዝርዝር ተመልክተዋል።
በቡሬ (Bure) አፋር ድንበር አቅጣጫ የኤርትራ ጦር ከፍተኛ ወታደራዊ ንቅናቄ እያደረገበት መሆኑን ለምወቅ ተችሏል። ደናከል (Denakal/Dallol)አቅጣጫም የሰርጎ ገብነትና የትንኮሳ ሙከራዎች ታይተዋል። ጋረቦ (Garebo) እና አዋላ (Awala): እነዚህም አካባቢዎች በኤርትራ ጦር ወረራና ትንኮሳ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ክልሉ በመግለጫው ዘርዝሯል።
“የኤርትራ ወታደሮች በአካባቢው ሰላማዊ የአፋር ዜጎችን በማዋከብና የክልሉን ድንበር ለመዳፈር ሙከራ ማድረጉን ተከትሎ ክልሉ ድርጊት በአስቸኳይ ካልቆመ ክልሉ ራሱን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ፣ በተጨማሪም የፌዴራል መንግስት ጉዳዩን በቅርበት እንዲከታተል በአሰራሩ አግባብ ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው በኤርትራ መንግሥት እየደረሰብን ላለው መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብቶችና የዘር ማጥፋት ወንጀል በተመለከተ ለአፍሪካ የሰብዓዊ እና የሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን ላቀረብነው ክስ ምላሽ እየተጠባበቀ መሆኑን ጠቅሶ የቀይ ባሕር አፋር ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ዛሬ መግለጫ የሰጠው።
መግለጫውን ከተከታትሉ መገናኛዎች ለመረዳት እንደተቻለው የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በኤርትራ መንግሥት አገዛዝ ደረሰብን ያለውን መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ አስመልክቶ ድርድጅቱ በመግለጫው አብራርቷል።
ጋምቢያ(ባንጁል) የአፍሪካ የሰብዓዊ እና የሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ላቀረበው ክስ የኤርትራ መንግስት ምላሽ እንዲሰጥ ክሱን መላኩን አድንቋል።
በኤርትራ መንግስት ላይ የቀረቡትን ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ክስ ተቀብሎ በመዝገብ ቁጥር 868/25 መመዝገቡን፣ የክሱ ፍሬ ነገር እና ይዘት ተቀባይነት ያለው መሆኑን እውቅና በመስጠት የኤርትራ መንግስት እንዲመልስ ክሱን መላኩን ኮሚሽኑ ማስታወቁን ገልጿል።
የድርጅቱ ሊቀ-መንበር ኢብራሂም ሀሩን በመግለጫቸው እንደተናገሩት፤ የኤርትራው መንግሥት በደናክል አካባቢ በቀይ ባህር አፋር ህዝቦች እየፈፀመ ያለው መጠነ ሰፊ፣ ስልታዊ፣ መንግስታዊ መር እና ቀጣይነት ያለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መጥቷል።
በአሁኑ ወቅት እየደረሱ ነው ካሏቸው የመብት ጥሰቶች መካከልም ከህግ እና ከፍርድ ውጭ ግድያዎች እና ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ማካሄድ፣ ያለ ፍርድ ማሰር እና ማሰቃየት፣ በሺዎች የሚቆጠሩትን መሰወር፣ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ማከናወን መሆናቸውን ለአብነት ጠቅሰው፤ በተለይም ከ300ሺህ በላይ የቀይ ባህር አፋር ህዝብን ማፈናቀል እና ፆታዊ ጥቃትን የአገዛዙ የአፈና መሳሪያ አድርጎ መጠቀሙን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ከሀገሪቱ ፖለቲካዊ አስተዳደር ማግለል፣ የቀይ ባህር አፋር ህዝብን ማንነትና ባህል ማጥፋትና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን መጣስ ተጠቃሽ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህም ድርጅቱ የአፍሪካ የሰብዓዊ እና የህዝቦች መብቶች ኮሚሽን ከ1993 ጀምሮ በኤርትራ መንግሥት እየደረሰባቸው ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ክስ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።
እኤአ ጁን 04 ቀን 2025 በ122 ገጽ የተደራጀ ክስ ማስገባታቸውን ጠቁመው፤ ኮሚሽኑ የኤርትራ መንግስት በ60 ቀናት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥ ክሱን መላኩን እንደገለጸላቸው ጠቁመዋል።
በክሱ ከተጠቀሙት ማስረጃዎች መካከል በድርጅቱ የተከናወነ የሰብዓዊ መብት ምርመራ ግኝት፣ በተባበሩት መንግስታት እና በአፍሪካ የሰብዓዊና ሕዝባዊ መብቶች በኤርትራ ላይ የተደረጉ ምርመራዎች፣ ግኝቶችና ማስረጃዎች፣ የመብት ጥሰት የደረሰባቸው የቀይ ባሕር አፋር ተጎጂ ወገኖች እንዲሁም በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የተገኙ የሰብዓዊ መብት ምርመራዎችን መቅረቡን ተናግረዋል።
ድርጅቱ የአፋር ህዝብ ከሚደርስበት መከራ ለማዳን፣ የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ድምፅ እንዲሆኑት፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት ትኩረት እንዲሰጡንና የኢሳያስ መንግስት ላይ ህጋዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ሰብዓዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንዲሁም ተፅዕኖ እንዲያሳድሩ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






