በአፍሪካ ቀንድ ለኢትዮጵያ ፀሃይ የወጣ ይመስላል

Date:

እ.ኤ.አ ከ1991 ከሶማሊያ ተገንጥላ ራሷን ገለልተኛ ሀገር አድርጋ የቆየችው ሶማሌላንድ ትላንት በታሪካዊ የዲፕሎማሲ ስኬቷ ከእስራኤል መንግስት ነፃ እና ሉዓላዊ ሀገር ተብላ እውቅና ተሰጥቷታል። ይሄም እስራኤልን ለሶማሌላንድ እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር ያደርጋታል።

CNN ይዞት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየውም፥ ይህ እርምጃ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሀመድ አብዱላሂ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት የአምባሳደሮች ልውውጥን እና የኤምባሲዎችን መክፈትን ጨምሮ ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን እንደሚፈጥር እና “በአብርሃም ስምምነት(Abraham Accord) መርኅ” የተቀረፀ ነው።

ይህ ልማት በአፍሪካ ቀንድ አህጉራዊ እንቅስቃሴ ላይ በተለይም ለኢትዮጵያ ስትራቴጅካዊ የባህር መዳረሻ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ትርጉም አለው።

የሶማሌላንድ ሉአላዊ ሀገር መሆን ለኢትዮጵያ በምን መልኩ ይጠቅማታል?

እ.ኤ.አ በ1993 ኤርትራ ሉዓላዊ ሀገር ከሆነችበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ(Landlocked) ሀገር ሆና መቆየቷ ይታወቃል። ይህም ወደብ ባላቸው ጎሮቤት ሀገራት፥ በተለይም በጅቡቲ ላይ በንግድ እንቅስቃሴዋ ከፍተኛ ጥገኛ እንድትሆን አድርጓታል። በዚህም በአመት ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ስታወጣ እንደቆየች አትላንቲክ ካውንስል ይዞት በወጣው ፅሁፍ ገልፇል።

በጃንዋሪ 2024 የኢትዮጵያ መንግስት ከሶማሌላንድ ጋር በወቅቱ የጨረቃ ስምምነት እየተባለ ሲጣጣል የነበረውን የመግባቢያ ስምምነት(MoU) የተፈራረመ ሲሆን ይህም ስምምነት ለኢትዮጵያ የበርበራ ወደብ የንግድ መዳረሻን ጨምሮ በግምት 20 ኪሎ ሜትር ያህል የሶማሌላንድ የባህር ዳርቻ ላይ የ50 አመት የሊዝ ውል (ሊራዘም የሚችል) ሰጥቷታል።

የባሕር በር የሌላት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በጅቡቲ ወደቦች ላይ ከፍተኛ ጥገኝነት ያላት ሲሆን፣ ለዚህም በየዓመቱ ከ1.5 እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ከፍተኛ ወጪ ታወጣለች።

እንደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባሉ አገራት ኢንቨስትመንት እየታገዘ የመጣው የሶማሊላንድ የወደብ መሠረተ ልማት ማደግ ኢትዮጵያ በጅቡቲ ላይ ያላትን ጥገኝነት እንድትቀንስ እና ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ይበልጥ ቀጥተኛ ተደራሽነት እንድታገኝ ይረዳታል።

ይህ ዕውቅና የሶማሊላንድን ጂኦፖለቲካዊ ጠቀሜታ የሚያሳድግ ብቻ ሳይሆን፣ የንግድ መስመሮቿን ለማባዛትና የኢኮኖሚ ውጤቶቿን ለማሻሻል ከምትከተለው የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ጋር የሚጣጣም ነው።

ይህም ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደቦች ላይ ያላትን ከ95% በላይ ጥገኝነት በመቀነስ፣ በዓመት በቢሊዮኖች የሚገመት ከፍተኛ ክፍያን መትረፍ ከመቻሏም ባሻገር ከዚህ ቀደም ለሚደርሱባት የቢሮክራሲያዊ መሰናክሎች አማራጭ መንገዶችን እንድታዘጋጅ ያስችላታል።

እንደ አትላንቲክ ካውንስል ዘገባ ኢትዮጵያ ከምታገኘው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባሻገር በተከራየችው የባህር ዳርቻ ላይ የባህር ሃይል ሰፈር የማቋቋም መብቷን በማግኘቷ የባህር ሃይሏን መልሶ ለመገንባት እና በስትራቴጂካዊ ግዛት ቦታ በሆኑት ቀይ ባህር እና የኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ ለማሰማራት ያስችላታል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእናት ሀገር ጥሪ ተሳትፎና ኮሎኔል መንግሥቱ

የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ...

ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ፤ ኢትዮጵያን ወደ መፃኤ ዘመን የሚያሻግር የሎጂስቲክስ አብዮት

ኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ ሰማይ ስር የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ካርታዋን እንደገና ለመሳል...

“ጥርስ የሌለው ውሻ” የሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም መፃኢ እጣፈንታ

አዲስ ሪፖርተር - ፕሬዛዳንት ትራምፕ አሜሪካን ከተባበሩት መንግስታት ደርጅት...

በዘመነ ትራምፕ ጫና ውስጥ የወደቀችው ሶማሊያ እና ለሶማሌ ላንድ ተስፋን ያለመለመው አዋጅ

አዲስ ሪፓርተር - ከሶማሌላንድ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና ከእስራኤል እውቅና...