በሶማሌላንድ  የሉዓላዊነት ጥያቄ ከታናናሽ ሀገራት ጩኸት ገዝፎ የሚያስተጋባው የሃያላኑ ዝምታ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ለምስራቅ አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ የጂኦ ፖለቲካዊ አብዮት ተደርጎ የሚቆጠረው የሶማሌላንድ ሉዓላዊ ሀገርነት ጥያቄን በተመለከተ እንደ አሜሪካ ፣ ሩሲያ ፣ እንግሊዝ እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ያሉ ሃያላን ዝምታ፥ እስካሁን የተቃውሞ ድምፅ ካሰሙት ሃገራት ጩኸት በላይ ለሶማሌላንድ ህልውና ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ይዘት ይኖረዋል።

ከሶማሌላንድ ሉዓላዊነት ጋር በተያያዘ እስካሁን በየመግለጫው እና በየመገናኛ ብዙሃኑ ተቃውሟቸው ሲያሰሙ የቆዩ ሃገራት ጉዳዩን ከማዳመቅ እና ትኩረት ከመሳብ በዘለለ፥ በዓለም አቀፍ መድረክ ካላቸው የተሰሚነት ደረጃ አንፃር በጉዳዩ ላይ ተፅዕኖ የማሳደርም ሆነ ውሳኔ የማስቀየር አቅም እንደማይኖራቸው ይታወቃል።

ለምሳሌ በኢትዮጵያ የተካሄደውን ለውጥ ተከትሎ የተቀረቀረባት መቀርቀሪያ በኢትዮጵያ ተማጽኖ የተነሳላት ኤርትራ፣ ምርጫ፣ ፓርላማ፣ ካቢኔ፣ ህግ፣ ፕሬስ፣ ዴሞክራሲ፣ ወዘተ የሌለባት ወይም የነጠፈባትና ዓለም ቁብ የማይሰጣቸው መሪዎች ያሏት ኤርትራ “ተቃወመች፣ አሳሰበች” ከሚለው ጩኸት ይልቅ የነግሊዝ ዝምታ ሰበር ዜና ይሆናል። የአሜሪካ ዝምታ ወይም በገደምዳሜ መጫወት ከሰበርም ይልቃል። ሌሎቹም ተጸዕኖ ፈጣሪ አገሮች እንደዛው።

ስለዚህም የሃገራቱን የፕሮፓጋንዳ ጩኸት ወደጎን በመተው ታላላቆቹ የዓለም ሃያላን ሀገራት በጉዳዩ ፈጥነው መግለጫ ከመስጠት ይልቅ ለምን ዝምታን እንደመረጡ እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ምን አይነት አቋም እንዳላቸው መመልከት ያስፈልጋል።

አሜሪካ እስካሁን የሶማሌላንድ ሉዓላዊ ሀገርነት ጥያቄ ላይ አቋሟን በግልፅ ካላሳወቁ ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ምንም እንኳን አሜሪካ እስካሁን በጉዳዩ ላይ ያላትን ወገንተኝነት ይፋ ባታደርግም በአፍሪካ ቀንድ እና አካባቢዋ ከሚሰጣት ብሄራዊ ደኅንነት ጥቅም አንፃር ሶማሊላንድን እንደ ወሳኝ የዲፕሎማሲ አጋር ትመለከታታለች። ትላንት በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ጉባኤ ላይ አሜሪካ ለእስራኤል ድጋፍ መስጠቷም በሶማሌላንድ እውቅና ላይ በተዘዋዋሪ ያላትን ድጋፍ የበለጠ ያመላክታል።

ሌላኛዋ በጉዳዩ ላይ ዝምታን የመረጠችው ሀገር ሩስያ ናት። የሶማሌላንድ እውቅና ጥያቄ ላይ የሩሲያ ወቅታዊ ዝምታ በሰፊ ጂኦፖለቲካዊ ትግሎች የተቀረጸ ስልት ተደርጎ ይወሰዳል።

ከሰሞኑ በዶናልድ ትራምፕ እና ቩላድሚር ፑቲን መካከል  የተደረገው ንግግር የዩክሬን የሰላም ድርድር እድገትን ያሳየ እንደሆነ ከኋይት ሃውስ የወጣው መረጃ ያሳያል። ይህም ውይይት የሩስያ ዝምታ ቢያንስ ለጊዜው ሊያጠናክር ይችላል ተብሎ ይታመናል። ምክንያቱም ሞስኮ በቅርቡ ያጀመረችውን የድርድር ሂደት ማበላሸት አትፈልግም።

በአጠቃላይ በእስራኤል በኩል የአሜሪካ ቀጥተኛ ያልሆነ ድጋፍ እና የሩስያ እና የአውሮፓ ሀያላን ሀገራት ዝምታ ሶማሌላንድ ሉዓላዊ ሀገር ለመሆን በምታደርገው ያላለሰለሰ ጥረት ውስጥ አንዳንድ ሀገራት ሊፈጥሩ የፈለጉትን ጫና በቀላሉ እንድትቋቋም ያደርጋታል።

ይህም ኢትዮጵያ ወደፊት ከሶማሌላንድ ጋር በምታደርጋቸው ስምምነቶች እና እውቅናዎች በሙሉ ከምዕራብያኑ ከለላ እንድታገኝ ይረዳታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ “እንዴት ተገባራዊ ይሁን እንጂ አጀንዳው ተቀባይነት አግኝቷል” ሲሉ በፓርላማ መናገራቸውና ስለሶማሌላንድ ተጠይቀው ምንም ሳይተነፍሱ ማለፋቸው የዝምታውን ድምጽ ከጩኸቱ ያገዘፈ ሆኗል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...

የፕሮፌሰሩ እይታ “ጠንቋይ የሰዉን እንጂ የራሱን አያዉቅም” አብይ አሕመድ ነጥብ አስጥለዋል

ሀገር የምትገነባው መንግስት ያድርግ በሚሉ ጥያቄዎች ሳይሆን እኔ ይሄን...