ጌታቸው ረዳ የአልጀዚራ ቃለ ምልልሳቸው መቆረጡንና፣ የጥያቄና መልሱን ዝግጅት የሰሩት ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን አጋለጡ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ዋና ተሳዳቢ ስለነበርኩ ከተቃዋሚው ጎራ አንድ ተሳዳቢ ተቀነሰ በሚል አንድም እንኳ በድለ ያልፈጸሙባቸው ተቃዋሚዎች እንደሚዘምቱባቸው አስታውሰው ስለ አልጃዚራ ውይይታቸው መናገር የጀመሩት አቶ ጌታቸው፣ የቃለ ምልልሱ ዓላማ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ማዕከል ያደረገ መሆኑን አመልክተዋል። ይሁንና ይህን ሴራ አስቀድመው ይወቁት አይወቁት ጠያቂውም አላነሳም፣ እሳቸውም አልተናገሩም።

አቶ ጌታቸው አልጃዚራ ላይ ቀርበው የተናገሩበት ወቅት ኢትዮጵያ ከሃምሳ ሺህ በላይ ተሳታፊዎች በሚተራመሱበት የኮፕ32 ስብሰባ እንድታዘጋጅ መመረጧ ሰበር ተብሎ የዓለም ሚዲያዎች በሚዘግብቡት፣ የጄ 20 አባል አገራት ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘችበትና “የዲፕሎማሲ ክስምና” ለሚሉ ወገኖች ንግግራቸው ተንጋሎ የመትፋት ያህል እንደሆነ በታየበት ወቅት መሆኑን ነበር ቃለ ምልልሱን ልዩ ያደረገው። በውቀቱ አዲስ ሪፖርተር የአቶ ጌታቸው የአፍ ውለምታ እስከመቼ እሹሪሪ ይባላል በሚል መተቸቷ አይዘነጋም። ዛሬም ድረስ አቶ ጌታቸው ተሳስተው ቃለ ምልልሱን አደረጉ የሚል ዕምነት ለመያዝ ያስቸግራል።

አቶ ጌታቸው በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴሌቪዝን የክፍል ሁለት ቃለ ምልልሳቸው እንዳሉት፣ 1 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ከፈጀው ቃለ ምልልሳቸው አየር ላይ የዋለው የ49 ደቂቃ ቅንብር ብቻ ነው። የቀረበውም ተቆራርጦ በሚፈለገውም መኩ ብተዘጋጅቶ ነው። አቶ ጌታቸው ለአልጀዚራው አወያይ ጥናቱን የሰራለት ኢትዮጵያዊ እንደሆነም ተናግረዋል። ዋና ዓላማው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንደነበሩ እያወቁ ለምን እዛ ውስጥ ገቡ የሚለው ያልተመለሰ ጥያቄ ቢሆንም፣ ይፋ በሆነው ቪዲዮ አይካተት እንጂ በርካታ ጉዳዮችን ግልጽ አድርገው ማቅረባቸውን አመልክተዋል።

ስለ ጫካ ፕሮጀክት ጉብኝታቸው በማንሳት “ስጎበኝ ቤተመንግስት ቤተመንግስት የሚባለው ነገረ አላየሁትም” ያሉት አቶ ጌታቸው “ቤተ መንግስ የለም፣ አላየሁም ብለህ ስትመሰከር ይቆጣሉ” በማለት ዕውነትን መመስከር በተለይ እንደ እሳቸው ካለ የቀድሞ ተሳዳቢ የሚያስወግዝ እንደሆነ በመጠቆም ወቅቱንና የወቅቱን የፖለቲካ መልክ አሳይተዋል።

“ወንጀል ተፈጽሟል ብዬ አምናለሁ። ወንጀል የፈጸሙትን ዘርዝሬያለሁ” ያሉት አቶ ጌታቸው ከፊደራል ጋር በተያያዝ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት በተቀመጠው የፍትህ አግባብ እንደሚታይ ማመልከታቸውን በግልጽ ቢናገሩም ለሕዝብ ይፋ በሆነው ቃለ ምልልሳቸው እንዳልተካተተ አመልክተዋል። የቃለ ምልልሱ ዋና ዓላማው እሳቸውን ማሳጣት፣ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ዒላማ አድርጎ ማሰደብ ነበር። አቶ ጌታቸው ረዳ “ምን ነካቸውና ታጥቦ ጭቃ ሆኑ” በሚል ከፍተኛ ወቀሳ የተሰነዘረባቸውም እንዴት ይህን አጀንዳ አስቀድመው ሳይውቁ ቀሩ? የሚለው አሁን ድረስ መልስ አልተሰጠበትም።

“አዲስ መረጃ አልቀረበም” አሉ አቶ ጌታቸው ራሳችውን ዛሬ ላይ አደብ የገዛ ቀንደኛ ተሳዳቢ እንደነበሩ በማስታወስ፣ “አዲስ መረጃ አልቀረበም። የእኔን ቲዊቶች ናቸው ተተርጉመው የቀረቡት፣ በትክክልም አልተተረጎሙም” በማለት የአልጃዚራ የተቀነባበረ ቃል ምልልሳቸውን ገበና አውግተዋል። የቃለ ምልልሱን ጥናት የሰሩት ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ ስም ሳይጠቅሱ ቢናገሩም እነ “ጋዜጠኛ ጸዳለ” መሆናቸው ይታወቃል።

በከፍተኛ ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ሲደግፉ የነበሩና አሁን መስመራቸውን የቀየሩ አቶ ጌታቸውን እንዴት ከመንግስት ጋር ሊሰሩ እንደቻሉ ከሞራል ጋር አያይዘው በቃለ ምልልሱ ወቅት ራሳቸው ባዘጋጁት ፕላት ፎርም ላይ ተጋባዥ መስለው ላነሱላቸው “እንዴት ደፍረህ አብረህ ሰራህ? ሳይሆን እሱስ / ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለማለት ነው/ እንዴት አምኖህ አስጠጋህ መባል ነው ያለበት” በማለት ያለውን የዕይታ መንሸዋረር አሳይተዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ፥ የቀረችውን እንጥፍጣፊ ኃይል ተጠቅሞ እንደገና ውጊያን ስለ ሚያልመው ትሕነግ ሰፊ ጊዜ ወስደው ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ጉዳይ ገብቼ ካላቦካሁ የሚሉትን የግብፅን እና የሻዕብያን ሴራ በቅርብ በሚያውቁት ልክ እየዘከዘኩ ይፋ አድርገዋል።

የሆነውን ሁሉ ዘንግቶ “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በሚል ከሻዕቢያ ጋር እንድነት የፈጠረውን ትሕነግን አስመልክቶ በሰፊው ሀሳባቸውን የሰጡት አቶ ጌታቸው ከሰል ሲጠጋጋ ቶሎ አመድ እንደሚሆን አመልክተው “መሠባሠብ ኃይል የሚሆነው መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ስትስማማ ነው” ብለዋል። መሰረታዊ አንድ የሚያደርግ የዓላማና የመዳረሻ ስፍራ የሌላቸው አካላት የሚያደርጉት ስብስብ ያው እንደ ከሰሉ እንደሚሆን ያመለከቱት አቶ ጌታቸው፣ ሻዕቢያ እና ትሕነግ በምንም ስሌት ከስምምነት ሊደርሱ እንደማይችሉ ሊገባቸው እንደማይችል፣ እንዲሁም ሻዕቢያ አብይን ለመጣል ብቻ አጀንዳ ቀረፆ ከሚንቀሳቀስ አካል ጋር የሚያደርገው ማንኛውም ስምምነት እንደማይሳካ ተናግረዋል።

“ሻዕቢያ በ’ርካሽ ኃይል’ ሀሳቡን ማስፈፀምን ከግብፅ ተምሯል”ያሉት አቶ ጌታቸው ሻዕቢያ ትሕነግን መንግስትን ለማጥቃት እንደ ርካሽ ጉልበት እየተጠቀመው እንዳለ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
አቶ ጌታቸው አያይዘውም “ትሕነግ ትንሽ እንኳን የህዝብ አጀንዳ ቢኖረው ኖሮ ከሻዕቢያ ጋር ያለውን ግንኙነት ወድያውኑ ያቋርጥ ነበር” በማለት የአመራሩን ድንቁርና አመላክተዋል።

“የፕሪቶርያው ስምምነት በህዝብ ተተፍቶ ለነበረው ትሕነግ ራሱን የሚያድስበት እድል ሰጥቶታል” ያሉት አቶ ጌታቸው “በስምምነቱ ምክንያት እንደ አመራር ነው የዳንነው” ሲሉ የሰላሙ ስምምነት የተጫወተውን ትልቅ ሚና አስረድተዋል።

“የትግራይ ተወካዮች ወደ ድርድሩ ሲቀርቡ በወቅቱ ውሳኔ ሰጪ አካል ከነበረው ከማዕከላዊ እዝ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ጦርነቱ እንዲቆም የተሰጠው ጥብቅ መመሪያ ይዞ ነበር፤ እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 2 ቀን 2022 ስምምነቱ ሊፈረም በነበረበት ቀን ደብረጽዮን ሁኔታው ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ በማሳሰብ እንዲህ ሲል መልእክት ላከልኝ ‘ሰላም፣ አዲግራት በጠላቶች እጅ ልትወድቅ ነው የተደረሰው ስምምነት ዛሬ መፈረም ከቻለ ያ ጥሩ ይሆናል። ካልሆነ ግን ዛሬ ማታ ትግላችንን እንዴት እንደምንቀጥል እና መፈጸም እንደምንጀምር ስልታዊ ውሳኔያችንን እንወስናለን።’ “ አቶ ጌታቸው አልጃዜራ ላይ ቀርበው ከተናገሩ በሁዋላ በአፍሪካን ሪፖርት ላይ ካስረጩት ጽሁፍ የተወሰደ።

አቶ ጌታቸው ስለ ቀድሞው የትግል አጋራቸው ደብረፅዮን ባነሱበት ንግግራቸው “ደብረፅዮን በኛ መሀል ሶስተኛ ወገን አያስፈልግም ሲል ከርሞ ስልጣኑ ሲነካበት ሀሳቡን የቀየረው ሰውየው የስልጣን አጀንዳ እንጂ የህዝብ አጀንዳ ስለሌለው ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

የትሕነግ አመራር ተደጋጋሚ ውድቀት እና ሽንፈት በቀረፀው የአመራር አጀንዳ ነው የሚንቀሳቀሰው ያሉት አቶ ጌታቸው “እኔንም ጨምሮ የትግራይ ህዝብ ላይ እንደ መዥገር የተጣበቀውም ያ የትሕነግ አመራር ለወጣቱ ቦታ በመክፈት ለትግራይ ህዝብ ውለታ መዋል አለብን” ሲል ገልፇል።

“በረሃብ ቆዳው የተጣበቀውን የትግራይ ተፈናቃይ ህዝብ ጉዳይ ለትሕነግ እንጀራቸው ነው” ያሉት አቶ ጌታቸው ትሕነግ ለትግራይ ህዝብ ጠብታ እርዳታ ሊሰጥ ቀርቶ መንግስት ለሚያደርገው እርዳታ ትልቁ መሰናክል ራሱ አመራሩ መሆኑን በግልፅ አስረድተዋል።

ለተረጂው ዋና መፍትሄ ገቢ ማሰባሰብ ሳይሆን ወደ ቦታው እንዲመለስ ማድረግ መሆኑን አፅንኦት በመስጠት እነርሱ የፈለጉትን ያህል ቢቃወሙም ተፈናቃዮችን ለመመለስ አሁንም መንግስት ግፊት ማሳደር እንዳለበትም አያይዘው አሳስበዋል።

አቶ ጌታቸው በክፍል ሁለት ቃለ ምልልሳቸው ስለ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ያነሱ ሲሆን “የሱዳን ህዝብ ወደ ሰላም መመለስ ከፈለገ እንደ ኤርትራ እና ግብፅ ያሉ አጫፋሪ ሀገራት የራሳቸውን አጀንዳ እያስፈፀሙ እንዳሉ መረዳት አለበት” ሲሉ የሱዳንን መንግስት አሳስበዋል።

“ግብፅ ለአመል ስለ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያውሩ እንጂ በጣም የሚያስጨንቃቸው የሱዳን መረረጋጋት ነው” ያሉ ሲሆን ሱዳን ከተረጋጋች አባይ ወንዝን በመጠቀም እና ከአረብ ሀገራት ጋር በመስማማት ያላትን 12 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ማልማት እንደምትችል፤ ይሄም ደግሞ የግብፅ መንግስትን እንደሚያባንነው አቶ ጌታቸው ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከሱዳን ጋር በነበራቸው ቁርኝት ወቅት የሚያውቁትን ምስክርነት ሰጥተዋል።

አቶ ጌታቸው በንግግራቸው “ኢትዮጵያን አቆርቁዘህ የምትከብር ትግራይ እንደሌለች አምናለሁ” ያሉ ሲሆን በመጨረሻም “ሁሉንም ነገር በኃይል የመፍታት አዝማሚያ ያላቸው ተቋማት መበተን አለባቸው” በማለት ለኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ለትግራይ ህዝብ የሰላም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...

የፕሮፌሰሩ እይታ “ጠንቋይ የሰዉን እንጂ የራሱን አያዉቅም” አብይ አሕመድ ነጥብ አስጥለዋል

ሀገር የምትገነባው መንግስት ያድርግ በሚሉ ጥያቄዎች ሳይሆን እኔ ይሄን...