ፋኖ ሶስት ታዳጊ ሴቶችን ረሸንኩ አለ “ፋኖ ሰላይ ያላቸው ታዳጊዎች “የቀን ሰራተኞች ናቸው”

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ ውስጥ ሦስት ወጣት ሴቶች በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች ተገድለው ተገኝተዋል። ሶስቱ ሴቶች በፋኖ መገደላቸው ራሱ ፋኖ አምኗል። የሴቶቹ መገደል ከተሰማ ብሁዋላ በአካባቢው ህዝብ ዘንዳ ከፍተኛ መረበሽ፣ በወረዳው አመራሮች እና በታጣቂዎቹ መካከል የእርስ በእርስ እየተካሰሱ መሆኑ ተሰምቷል።

ኤርትራ የተቀመቱትን ዘመነ ካሴን ሊቀመንበር አድርጎ የሾመው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ማዕከላዊ ኮማንድ አባል አስረስ ማረ ዳምጤ፤ “ሦስቱ ሴቶች ለጠላት ሲሰልሉ በመገኘታቸው እርምጃ ተወስዶባቸዋል” ሲል ለቢቢሲ መናገሩን ታውቋል። ቢቢሲ በዘገባው እንዳለው የወረዳው የፀጥታ ኃይሎች ሦስቱን የሴቶች አስከሬን ያገኙ ከነዋሪዎች በደረሳቸው ጥቆማ ነው፤ የወረዳው የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ሙላት ሙንዬ እንዳሉት አስከሬኖቹ የተገኙበት ቦታ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ያለ ነው። ስፍራው በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ከሆነ እንዴት ሄደው አስከሬኖቹን ሊያነሱ እንደቻሉ ኝ አልተብራራም።

ድርጊቱ የተፈጸመው ማክሰኞ ታኅሣሥ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ጥጃ ጎጠር መገንጠያ በተባለ ስፍራ ሲሆን፣ ሟቾቹ ሙያነሽ ተሾመ፣ ትህትና አለኸኝ እና መልካም ታዴ የተባሉ ከ17 እስከ 19 ዓመት የሆናቸው ታዳጊዎች መሆናቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ማዕከላዊ ኮማንድ አባል የሆኑት አስረስ ማረ ዳምጤ ለጉዳዩ በሰጡት ምላሽ ሴቶቹ ለረጅም ጊዜ በቀን ሠራተኛነት” ሽፋን ለጥምር ጦሩ የስለላ ሥራ ሲሠሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል። እንደ አመራሩ ማብራሪያ ከሆነ ወጣቶቹ የተያዙት ወታደራዊ ሥልጠና ከሚወስዱ ምልምሎች ጋር በመመሳሰል ለምዝገባ በቀረቡበት ወቅት ሲሆን፣ በተደረገባቸው ምርመራም ለደህንነት አካላት መረጃ ሲያቀብሉ እንደነበር አምነዋል ማመናቸውን ቢቢሲ “ነገሩኝ” ብሎ ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችሏል። በዚሁ መነሻ ሴቶቹ ኝባራቸውን በጥይት ተመተው ተገድለው ተጥለዋል።

በዚህም ምክንያት በታጣቂ ቡድኑ የውስጥ ደንብ መሠረት እንደ ተዋጊ ኃይል ተቆጥረው የሞት ቅጣት እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

በተቃራኒው የወረዳው የሰላም እና ደኅንነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ደምስ አለኸኝ የታጣቂዎቹን ክስ ውድቅ በማድረግ ሟቾቹ ሰሊጥ የመሰብሰብ ሥራ ላይ የተሰማሩ ንጹሐን ዜጎች መሆናቸውን ይናገራሉ። ከመካከላቸው አንዷ የመስማት ችግር ያለባት መሆኗን የጠቀሱት ኃላፊው፣ ከመገደላቸው በፊት ወሲባዊ ጥቃት እና ድብደባ እንደተፈጸመባቸውም በሕክምና ናሙና መረጋገጡንም አመልክተዋል።

የሟች ቤተሰቦችም በበኩላቸው ወጣቶቹ በቪዲዮ ላይ የሰጡት የእምነት ቃል በከፍተኛ ድብደባ የተገኘ እንጂ እውነት እንዳልሆነና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችንም በትክክል እንደማያውቁ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት የአስከሬን ምርመራ ከተደረገ በኋላ ሟቾቹ ለቤተሰቦቻቸው ተረክበው የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው መፈጸሙ ታውቋል። ይተፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት በሰላማዊ ሰዎች ደኅንነት ላይ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን አዲስ ሪፖርተር ከአካባቢው ነዋሪዎች መረጃ ለማግኘት ባደረገው ጥረት ተረድቷል። ዝርዝር ዘገባዎችን በቀጣይ እናቀርባለን።

ለፋኖ አደረጃጀት ቅርብ የሆኑና በአደረጃጀት ውስጥ ያሉበት አሁን እንዳደረጉት በማህበራዊ ገጾቻቸው ቀደም ሲል በተመሳሳይ አንድ የአማራ ተወላጅ ከመንግስት ጋር ተገናኝተሃል በሚል እጁ ሲቆረጥ በቪዲዮ ተደግፎ መሰራጨቱ አይዘነጋም። እጁን የተቆረጠው ወጣት በተባለው ክስ እንደሌለበት የተናገረ ሲሆን ወንጀሉን የፈጸመውም በአገር መከላከያ አማካይነት በቁጥጥር ስር መዋሉ አይዘነጋም።

ሰሞኑኑን በተለያዩ ሕዝባዊ ስብሰባዎች የአማራ ክልል ሕዝብ መማረሩን ልብ በሚነካና ህሊናን በሚፈታተን መልኩ ሲገልጽ እየተሰማ ነው።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...