አዲስ ሪፖርተር – እስራኤልን ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን ከሶማሊላንድ ጠራርገው እንደሚያስወጡ የዛቱት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ አሜሪካ መንግስታቸውን ለማዳከም እና በመጨረሻም ራሳቸውን ከስልጣን ለማስወገድ የምታደርገውን ጥረት በመስጋት ላይ መሆናቸውን የሞቃዲሾ መገናኛ ብዙኃን በሰፊው ዘግበዋል።
ፕሬዝዳንቱ በተለይ የአሜሪካ መንግስት የቀድሞውን የቬንዙዌላ መሪ ኒኮላስ ማዱሮን አፍኖ ለመውሰድ ያደረገውን ሙከራ እና ያወጣውን ዋጋ በመጥቀስ፣ “አሜሪካ እንደ ቬንዙዌላ መሪ አፍና ትወስደኛለች” የሚል ስጋት እንዳላቸው በስፋት እየተዘገበ ነው።
የፕሬዝዳንት ሃሰን ስጋት የመጣው በቅርቡ በአሜሪካ እና በሶማሊያ መንግስታት መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን ተከትሎ ነው።
ፕሬዚዳንቱ በአሜሪካ ላይ ዋነኛ ጥርጣሬ ያደረባቸው ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የወደብ መዳረሻ እና የባህር ኃይል ትብብር ስምምነት በተመለከተ አሜሪካ በቂ ድጋፍ አልሰጠችም የሚል ዕምነት በመያዛቸው ነው።
አሜሪካ በሶማሊያ ለጸረ ሽብር ትግል እና የአል-ሸባብን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ድጋፍ ስታደርግ ብትቆይም፣ ከቀናት በፊት በአሜሪካ እና በሞቃዲሾ መካከል የስትራቴጂክ ቅንጅት ድጋፍ መቋረጡ ይታወሳል።
ፕሬዝዳንቱ የሀገር ውስጥ ተቃዋሚዎችን እና አሜሪካን እንደ አንድ ተባባሪ ኃይል በመመልከት፣ በራሳቸው ላይ የሚሰሩ ሴራዎች እንዳሉ በመጠራጠር ላይ ናቸው።
የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፣ ፕሬዝዳንቱ በግል ስጋታቸው ላይ፣ ከአሜሪካ የሚመጡ ተጨማሪ ጫናዎች እና ቅጣቶች እንደሚጠብቁም ይጠቁማሉ። ለአንዳንድ ከፍተኛ የሶማሊያ ባለስልጣናት የአሜሪካ የጉዞ እገዳዎች መጣል ሊያስከትል ይችላል።
አሜሪካ ለሶማሊያ የምትሰጠውን የደህንነት እና የሰብዓዊ ዕርዳታ ሊቀንስ ወይም ለተወሰኑ ፕሮግራሞች ሊገድብ ይችላል። ይህ ደግሞ ከአል-ሸባብ ጋር በሚደረገው ትግል ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል።
የአሜሪካ አምባሳደርን ወደ ኋላ መጥራት ወይም ሌሎች የዲፕሎማሲያዊ ደረጃ ቅነሳ እርምጃዎችን መውሰድ ሊከሰት ይችላል።
የፕሬዝዳንቱ ስጋት እጅግ ከፍ ያለ የፖለቲካ ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውን ያሳያል። እሳቸው እንደሚሉት፣ የቬንዙዌላው አይነት ‘የመሪ ማደን’ ሴራ ይሁን አይሁን እርግጠኛ ባንሆንም፣ ሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ቀውስ ውስጥ መግባታቸውን ያመለክታል።
የሞቃዲሾ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እና የድረ-ገጽ ጋዜጦች ይህን ጉዳይ በዋናነት እየዘገቡት ነው። ዜናው በሰፊው የሀገር ውስጥ ተቃውሞዎችን እንደሚያቀጣጥል እና ፕሬዝዳንቱ የሀገር ውስጥ ድጋፍን ለመጠየቅ እንደተጠቀሙበት አንዳንድ ተንታኞች ይገልጻሉ። የዜና ዘገባዎቹ ፕሬዝዳንቱ ስጋታቸውን የገለጹበትን ሁኔታ እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ የደኅንነት ሁኔታ ላይ ያተኮሩ ናቸው።
አስተያያት ሰጪዎች “አሜሪካ ፕሬዝዳንቱ ለማሰር ይሕንን ሁሉ ርቀት እንደተማትጓዝ ገልጸው፤ትራምፕ በአንድ የስልክ ጥሪ ናና እጅህን ለአሜሪካ ፖሊስ ስጥ ቢሉት ፍቃደኛ ከመሆን ውጪ ሌላ አማራች የላቸውም” ሲሉ በስጋታቸው ዙሪያ በሚሰራጨው ዜና ተሳልቀዋል።
በሶማሊያ ውስጥ ከሚታወቁ እና በስፋት ከሚዘገቡ መገናኛ ብዙኃን አንዱ የሆነው ጋሮዌ ኦንላይን “Garowe Online” መረጃውን ሲያሰራጭ እንዳለው ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ ተሸብረዋል።
ዋና መቀመጫው በፑንትላንድ ‘Puntland’ግዛት ጋሮዌ ቢሆንም፣ ስለ መላዋ ሶማሊያ በስፋት የሚዘግበው ጋርዌይ በፌሞቃዲሾ መንግስት እና በክልላዊ መንግስታት መካከል ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ጥልቅ ትንታኔዎችን እና ዜናዎችን የሚያቀርብ ሚዲያ ነው።
ሃሰን ሼክ ከቤተመንግስታቸው ውጭ በነጻነት መንቀሳቀስ የማይችሉ፣ ክልሎች የማይታዘዟቸው፣ በራሳቸው ጎሳ ብቻ የሚደገፉ መሪ መሆናቸው ይታወሳል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






