ለኢትዮጲያ ሲሉ ቀይ ባሕር ላይ የወደቁት ጀግኖች አደራ ተቀባይ

Date:

ኢትዮጵያ ቀይ ባሕር የትናንትና ታሪኬ ኾኖ አይቀርም የሚል አጀንዳዋን ካነሳች ውላ አደረች። የተፈጠረው ስህተት ትናትና ቢኾንም ዛሬ እና ነገ ይታረማሉ የሚሉ አንደበቶች እየበዙ መጥተዋል። ይህ ጉዳይ ተግባራዊ ይኾን ዘንድ ህያው ምስክሮች አሉ። የሺህ ዓመታት ፈተና የኾነው የዓባይ ጉዳይም ተፈትቷልና።

ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ አብራክ ክፋይ እንደነበር ታሪክ ምስክር ነው። ታሪክ ቀይ ባሕር ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ የተከፈለውን ዋጋ ላይፋቅ በደማቁ ከትቦታል። ያኔ እንቢ ለሀገሬ ያሉ እናት ሀገር ወዳድ ዜጎች ውድ ሕይወታቸውን ሳይሰስቱ እንደሰጡለትም ተመዝግቧል።

ቀይ ባሕርን ዐይናችን እያየ ከሚሄድስ ሞቴን እመርጣለሁ እያሉ ራሳቸውን ለሀገር ክብር የሰጡ መኖራቸውም እንዲሁ ተሰንዷል። የአሰብ ወደብ ከኢትዮጵያ የወጣበትን ስሁት ታሪክ የሰነዱት እና የታሪኩ ተጋሪ ታደሰ ቴሌ ሳልቫኖ አይ ምጽዋ መጽሐፍ ላይ ይህን ብለዋል።

“በዚች የኢትዮጵያ ሕዝብ የባሕር በር እና ዓለም አቀፍ ወደብ በኾነችው በምጽዋ ከተማ እና በቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ ቆሜ ሽጉጤን ለመጠጣት ዝግጁ ነኝ። በዕውነት እኔ ዛሬ በሞት ብሸነፍም በታሪክ እና በመጭው የኢትዮጵያ ትውልድ ፊት ግን አልሸነፍም” በማለት ለሀገሩ ዋጋ የከፈለውን እና በወቅቱ የባሕር ኀይል አባል የነበረን ጀግና ውሳኔ አስፍረዋል።

ይህ ውሳኔ ጀግኖች ለአሰብ ጉዳይ ጽኑ አቋማቸውን እስከ ሞት ድረስ በተግባር ለመግለጣቸው ምስክር ነው።

ከዚሁ “አይ ምጽዋ” መጽሐፍ ላይ “ኢትዮጵያ ሀገሬ የጀግኖች መፍለቂያ እና ታሪክ ያላት ሀገር ናት። ጀግናው ሕዝቧ እያለ የባሕር በሩ በሻዕቢያ ተይዞ እና የጠላቶቹ መፈንጫ ኾኖ አይቀርም” የሚል ጠንካራ ሃሳብ ሰፍሯል።

በወቅቱ የባሕር ኀይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ተሾመ ተሰማ “የፈለገ ጊዜ ይቆይ እንጅ ሻዕቢያ ምጽዋን እንደያዛት ለዘለዓለም አይኖርም” ማለታቸውንም ጽፈዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በሯ ከጇ ሲወጣ በወቅቱ የነበሩ የባሕር ኀይል አባላት እና ተቆርቋሪዎች የሕይወት ዋጋ እየከፈሉም ለቀጣዩ ትውልድ አደራን እያስቀመጡ፤ ታሪክን በደማቸው እየጻፉ ለመሄዳቸው ማሳያ ነው።

ታድያ ለሀገራቸው ሲሉ ቀይ ባሕር ላይ የወደቁት ጀግኖች አደራ ተቀባዩ ትውልድ የቱ ይኾን?

የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አደም ካሚል ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ ቀይ ባሕርን ያጣችው ዛሬም ድረስ ባሉ ጠላቶቿ ነው ብለዋል። በዋናነትም ጠንተ ጠላቷ ግብጽ ለኢትዮጵያ የባሕር በር አልባነት እጇ አለበት ይላሉ።

ትናንት ብቻ ሳይኾን ዛሬም ኢትዮጵያ የባሕር በርን ስታነሳ የሴራዋ ማገርሸት ፍትሐዊ ጥያቄን የማጥፋት ዘዴዋ እንደኾነ አንስተዋል።

ግብጻዊያን ባሉበት የዓለም ሀገራት ሁሉ ለሀገራቸው ዲፕሎማት ናቸው፤ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችንም የመጠቀም ነገራቸው ብልጠት የተሞላበት እንደኾነ ነው የገለጹት። ዓባይ ላይ ተንኮሏ የከሸፈባት ግብጽ ዛሬም እንደትናንቱ በየመድረኩ ክሷን ያለማቆሟ ምስጢር ይኸው ነው ብለዋል።

700 ሚሊዮን ተከታይ እንዳሉት ከሚነገርለት አልጀዚራ ጀርባ ሳይቀር የግብጻዊያን እጅ እንዳለበት ነው የተናገሩት። አረብኛ ቋንቋን አጥብቀው ለሀሰት ዲፕሎማሲነት ይጠቀሙበታልም ብለዋል።

ዕውነት ያላት ኢትዮጵያ እነዚህን መሣሪያዎች በመጠቀም በኩል ይቀራታል ይላሉ።

ከመሐመድ አሊፓሻ ጀምሮ የግብጽ መሪዎች ሁሉ ኢትዮጵያን ለማዳከም ያልሠሩት ተንኮል የለም ነው ያሉት። ከ4 ሺህ በላይ ሚዲያዎች በግብጽ ውስጥ ይገኛሉ የሚሉት ፕሮፌሰሩ እነዚህ ሚዲያዎች ሁሌም ኢትዮጵያን በሀሰት መወንጀል አንዱ ሥራቸው ኾኖ ቀጥሏል ብለዋል።

አሁን ላይ ኢትዮጵያን ለመወንጀል እና የኢትዮጵያን ዕውነት ለማጥፋት የተቋቋሙ በአራት ቋንቋ የሚያሠራጩ ሚዲያዎች አሉ ነው ያሉት። በአማረኛ፣ በትግረኛ፣ በኦሮምኛ እና በአረብኛ ቋንቋ የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚያራግቡ ሚዲያዎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል።

ይህ ኾኖ ሳለ እኛ ኢትዮጵያውያን ግብጾች በሚደግሱልን የሴራ ድግስ ልክ በመዘጋጀት በኩል ሥራ ይጠበቅብናል ነው ያሉት። ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለሀገሩ ዲፕሎማት መኾን አለበት ነው ያሉት። ለአብነት እንኳ የቀይ ባሕር የትናንት ማንነት ላይ ስንቶቻችን ጠንቅቀን እናውቅ ይኾን ? ይላሉ።

ጅቡቲን እና ሶማሊያን በሴራ የአረብ ሊግ አባል ያደረጉት ግብጾች ናቸው ነው ያሉት። የዚያ ውሳኔያቸው ዋና ዓላማም ኢትዮጵያን ከቀይ ባሕር ጨርሶ የማራቅ አንዱ ስትራቴጂ ነበር ብለዋል።

ብዙ ታሪክ ቀያሪ የኾነውን ሕዳሴን እውን ያደረገው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀይ ባሕርን በክብሩ ለመመለስ ያዳግተዋል ብዬ አላምንም ነው ያሉት ፕሮፌሰር አደም።
“ትውልዱም ታሪክ ለመጻፍ የታደለ መኾኑን አምኖ መዘጋጀት እና መተባበር እንዳለበት” አሳስበዋል።

Via አሚኮ

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...

የፕሮፌሰሩ እይታ “ጠንቋይ የሰዉን እንጂ የራሱን አያዉቅም” አብይ አሕመድ ነጥብ አስጥለዋል

ሀገር የምትገነባው መንግስት ያድርግ በሚሉ ጥያቄዎች ሳይሆን እኔ ይሄን...