ጃዋር መሐመድ በይፋ የትጥቅ ትግል አስተባባሪዎችን ተቀላቀለ፤ “ስለ ሻዕቢያ እንዳታነሳ ፋኖንና ትህነግን ይረዳሉ”

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ዛሬ በዋሽንግቶን ዲሲ ግብጽ በሻዕቢያ በኩል ድጋፍ የምታደርግለትን የትጥቅ ትግል የሚመሩ የተለያዩ አደረጃጀቶች የወከሏቸው ስብሰባ እንደሚቀመጡ ታውቋል። አቶ ጃዋር ይህንኑ በይፋ ስብሰብ መቀላቀላቸው ታውቋል።  በዚህ ስብሰባ እንዲካፈሉ ተጠርተው ጥያቄውን ውድቅ ያደረጉ በስብሰባው ላይ ስለ ሻዕቢያና ስለ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም እንደሚያነሱ ሲናገሩ፣ በፕሮፌሰር ሕዝቅዔል በኩል “ስለ ሻዕቢያ እንዳታነሳ ፋኖንና ትህነግን እየረዱ ነው ተባልኩ” ብለዋል። ጃዋር “ኦሮሞን ከአራት ኪሎ እንነቅላለን” ከሚሉ ኃይሎች ጋር በምን የትግል አግባብ እንደተቀላቀለ ለመጠየቅ ኢሞከርም ፈቃደኛ አልሆነም።

በስብሰባው ላይ የሚሳተፉት በተለያዩ ስያሜ ከሚጠሩ ስብስቦች ከተወከሉት መካከል አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ ነዓምን ዘለቀ፣ አቶ ልደቱ አያሌው፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ አቶ ኦባንግ፣ /አቶ ኦባንግ የቀድሞ የመብት ተሟጋች የአሁኑ ነጋዴ ኦባንግ ሜቶ አይደሉም/ ይጠቀሳሉ። ስለ ስብሰባው አጀንዳና ይዘት ዝርዝር ለአዲስ ሪፖርተር የአሜሪካ ተባባሪ መረጃ የሰጡ “የስብሰባው ባለቤት በግብጽ ውክልና ኢትዮጵያ ላይ ትርምስ የሚያመርተው ሻዕቢያ ነው” ብለዋል።

የስብሰባው አጀንዳ በዋናነት የሽግግር መንግስት ስለሚመሰረትበት አግባብ ለመነጋገርና በአውሮፓና አሜሪካ የተናበበ ሰላማዊ ሰልፍ ለማዘጋጀት ነው።

በስብሰባው ከኢትዮጵያ ማዳን፣ከኢትዮጵያ አንድነት፣ ክሪስታል ሲቲ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ ካቋቋሙት ህብረት፣ ከአብሮነትና ከመሳሰሉት ስብስቦች የተውጣጡት ተወካዮች በዛሬው ስብሰባቸው መንግስት እንዴት እንደሚፈርስ ይመክራሉ። ቀደም ሲል የሽግግር ሰነድ መዘጋጀቱን መዘገባችን አይዘነጋም።

ወደ ሽግግር ለማምራት አገሪቱ ውስጥ ሁከትና ትርምስ መፈጠር ስላለበት፣ ምርጫ እንዳይደረግ ማሰናከልና አገር ውስጥ  “ህጋዊ” ከሚባሉ ፓርቲዎች፣ ተቋማትና የህቡዕ አደረጃጀቶች ጋር በቅንጅት ረብሻ ለማስነሳት እየተሰራ እንደሆነ አዲስ ሪፖርተር መዘገቡ አይዘነጋም። በተለይም መምህራንና ተማሪዎችንና የሕክምና ባለሙያዎችን ለማነሳሳት ጃዋር መሀመድ ከስምምነት መደረሱን ግልጾ እንደነበር ባሰፈርነው ዘገባ “እኛ የምናውቀው ነገር የለም። በመምህራን ጥቅምና ኑሮ ማሻሻያ ከመንግስት ጋር አብረን እይሰራን ነው” በማለት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት ምላሽ መስጠታቸውን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

በስብሰባው ላይ ከሚገኙት መካከል አብሮነት ሰላማዊ ትግል በሚል መለያ ራሱን የሚገልጽና በአቶ ልደቱ የሚመራ ቢሆንም በውስጡ በቀጥታ ከሻዕቢያና የትህነግ አንድ ክፋይ ጋር አብረው የሚሰሩ የተካተቱበት መሆኑን የቦርድ አባል የሆኑትን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። ይህን መረጃ የሰጡን የአብሮነት ቦርድ አባል “አብሮነት የትጥቅ ትግል የሚደግፍ ስብሰብ መሆኑን አስቀድመን ተናግረናል” በማለት ምንም አዲስ ነገር እንደሌለ አመልክተዋል።

ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ክሪስታል ሲቲ በመሰረቱት ስብስብ ውስጥ ያሉበት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል፣ ኤርትራዊው አቶ ነዓምን ዘለቀ፣ ታማኝ በየነ ከሻዕቢያ እንዲሁም ከትህነግ የሚሰጡ አጀንዳዎችንና መመሪያዎችን ይዘው የሚቀርቡ መሆናቸው ታውቋል።

ዜናውን በዝርዝር ያጫወቱን የስብሰባው ተጋባዥ ከሁለት ሳምንት በፊት በሜኖሴታ የኦሮሞ ልሂቃን ተሰብስበው እንደነበር አመልክተው፣ ከስብሰባቸው ጎን ለጎን ሻዕቢያና ትህነግ የፈጠሩት ጥምረት ከብሄራዊ ጥቅማችን አንጻር ያለውን ጉዳት በማንሳት፣ ይህንኑ ጉዳይ በስብሰባው ላይ አጀንዳ እንደሚያደርጉ ለሕዝቅዔልን ማስታወቃቸውን ለአዲስ ሪፖርተር ተናግረዋል።

“እንዳታነሳው አለኝ” ይላሉ ዜናውን ያጋሩን የአብሮነት ቦርድ አባል። “ሻዕቢያ ከፋኖና ትህነግ ጋር ግንኙነት ስላለው፣ ከፍተኛ ድጋፍ ስለሚያደርግ ይህን ጉዳይ አንስተህ ክርክር እንዳትፈጥር” በማለት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ስላስጠነቀቋቸው ስብሰባውን ላለመካፈል መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የጀመረችውን ጥረት በማጣጣል ለኤርትራ መንግስት በይፋ የሚሰሩትን ኃይሎችና ግለሰቦች አሰባስቦ ለኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት በማዘጋጀት ኢትዮጵያ ውስጥ ነውጥ ለማስነሳት የኃይማኖት ተቋማትን ለመጠቀም፣ ኃይማኖት ተኮር ግድያ ለማስፋፋት በጀት ተመድቦ ወደ እንቅስቃሴ መግባቱን የአዲስ ሪፖርተር የአሜሪካ ተባባሪ ሴራውን ከሚያውቁ ያሰባስወበውን መረጃ አጣቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

በተለይም ጃዋር መሐመድ በካራሚሌና በጎሮጉት አቅጣጫ እስከ መላካ በሎ አደራጅቶት የነበረው ኃይል መረጃ ሾልኮበት ቢበተንም ርዝራዙን ለማንቀሳቀስ ኬንያ ባሉ አጋሮቹ አማክይነት እንቅስቃሴ መጀመሩን የሚያውቁ “ጃዋር በይፋ የትጥቅ ትግል አራማጆች ጋር የተቀላቀለው ይህንብኑ አደረጃጀት መልሶ ለማንቀሳቀስ ከዋናው የሻዕቢያ ወኪሎች ጋር ከስምምነት ላይ ከደረሰ በሁዋላ ነው” ብለዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት ስብሰባ አድርጎ የነበረው አብሮነት ሶስት ሰዓት የፈጀ ጭቅጭቅ ካደረጉ በኋላ ስብሰባው ያለ አንዳች ውሳኔ መበተኑን ያስታወቁት የቦርድ አባሉ፣ የተጣሉት አቶ ልደቱና ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል እንደሆኑ አምልክተዋል። የርዕዮት ሚዲያ ባለቤት የሆነው ቴዎድሮስ የአብሮነት ስራ አስፈጻሚ እንዳይሆን በመደረጉ ሁለት የቦርድ አባላት በራሳቸው ፈቃድ ራሳቸውን ስላገለሉ ተተኪ በሚመረጥበት ሁኔታ ለመመካከር ነበር ስብሰባው የተጠራው።

በዚህ ስብሰባ ላይ ፕሮፌሰሩና ሌላ አንድ አባል አቶ ልደቱን “ዲክታተር” በማለት የጀመሩት ንትርክ እስከ ስድድብ ያደረሰ፣ “አንተ ማን ነህ?” ያባባለ እንደነበር አዲስ ሪፖርተር የደረሳት በድምጽ የተደገፈ መረጃ ያመልክታል።

ስብሰባው ያለ ውሳኔ በንትርክ ከተበተነ በሁዋላ ሕዝቅዔልን “በጭቅጭቅ ጊዜ ገደልን” በማለት እኚሁ የቦርድ አባል ሲናገሩ “አብሮነት ከልደቱ ጋር እየሞተ ነው ብዬህ አልነበር፣ እንገለዋለን” በማለት መልስ ሰጥተዋል። ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል አብሮነት ወስጥ የሰላማዊ ታጋይ ሆነው በስራ አስፈጻሚነት እየሰሩ ጎን ለጎን ከብሄር ብሄረሰቦች የተወጣጣ ሌላ ቡድን ማደራጀታቸውን፣ እንዲሁም በሶማሌና ኪኛ እንዲሁም በሶማሌ ድንበር የተበተኑ የኦነግ ታጣቂዎችን በማሰባሰብ የውጊያ ግንባር እንዲጀመር ከግብጽ ሹመት ማግኘታቸውን በመረጃ አስደግፈን መዘገባችን አይዘነጋም።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...

የፕሮፌሰሩ እይታ “ጠንቋይ የሰዉን እንጂ የራሱን አያዉቅም” አብይ አሕመድ ነጥብ አስጥለዋል

ሀገር የምትገነባው መንግስት ያድርግ በሚሉ ጥያቄዎች ሳይሆን እኔ ይሄን...