ግማሽ ምዕተ ዓመት ያስቆጠረው የትሕነግ መበስበስ፤ ትግራይንና የትግራይን ህዝብ ይዞ መደርመስ!

Date:

ይህ ጽሁፍ የተላከው በሚታወቁ የቀድሞ የትግራይ መኮንን ነው። ጽሁፉ ላይ አንዳንድ የኤዲቲንግ ስራና ከተጠቀሰውም በላይ የከረሩ ዘለፋዎችን ከማስቀረቱ በላይ ሙሉ በሙሉ የጸሐፊው ነው። ጸሐፊው ስም ጠቅሰው ያነሷቸው የከረሩ ጉዳዮች ቢኖሩም ለማተም አልወደድንም።

በሚታወቁ የቀድሞ የትግራይ ተወላጅ መኮንን የቀረብ ነጻ አስተያየት

አዲስ ሪፖርተር – ቤትን የተሸከመ ምሰሶ መበስበስ እና መናድ ደረጃ ላይ ሲደርስ የቤቱን መዋቅር ይፈርሳል። የቤቱ መዋቅር ሲፈስ ምሰሶውን ተማምነው በጎጆው ውስጥ የተጠለሉ ነዋሪዎች ልይ ከፍተኛ አደጋ ማድረሱ የማይቀር ነው።

አንድ የፖለቲካ ፓርቲም ቢሆን የሚከተለው ርዕዮተ ዓለም ወይም ፖለቲካ ራሱ መዋቅሩንም ሆነ እታገልለታለው የሚለውን ህዝብ የማሻገር አቅም ሲያጣ፣ እንዲሁም መዋቅሩን የሚወክለው አመራር ያለ ምንም ተሃድሶ እና ዘመኑን ባልዋጀ ኋላ ቀር አስተሳሰብ ከተመራ፣ ፓርቲው ከመበስበሱ እና ከመሸርሸሩም ባሻገር የያዘውን ግዛት እና ህዝብ ይዞ ይገነደሳል። በትህነግ አማካይነት በትግራይ የሆነው ይህ ነው።

ከጥይት በላይ ሀሳብን የሚፈራው የትሕነግ የፖለቲካ አመራር፣ በዘመኑ የፖለቲካ እርምጃ መቃኘትን አሻፈረኝ በማለት ከዘመን ዘመን እየበሰበሰ እና እየከረፋ መኖርን ባህሉ አድርጎ፣ ትግራይ ላይ እንደ አልቅት ተለጥፎ፣ ምስኪኑን የትግራይ ህዝብን በበስባሹ ጠረን መርዞ እያሰቃየ ይገኛል።

ትሕነግ በስልጣን ዘመኑ በዙሪያው የሰበሰባቸውንና “ተጋዳላይ” የሚላቸውን ሳይቀር በሙስና እና በሌብነት በማጨማለቅ የተካነው ነው። ይህን የሚያደርገው ደግሞ ከኋላ ቀር አስተሳሰቡ ጋር የማይራመዱትን ወይም ለመቀየርና ከዘመኑ ጋር ለመራመድ የሚሞክሩትን ኮቴ ለመስበር ነው። በዚህ የማበስበስ ሴራ ስንቶች እንደተበሉ ለማስታወስ የትህነግን ዶሴ ገልበጥ ገልበጥ ማድረግ ብቻ በቂ ነው። እሱም እይክድም።

በማበስበስ ሴራ የተካነው ትህነግ አቶ መለስ ከመሞታቸው በፊት “ገምተናል፤ ከእንጥላችን በስብሰናል” በማለት በይፋ የዘፈኑለት ድርጅት እንደሆነ እዚህ ላይ ማስታወሱ ግድ ነው። ምክንያቱም የዚህ አስተያየት ጸሃፊ ይህን ስም ለትህነግ አመራሮቹ አልሰጠምና።

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ አበስብሰውና ተተኪ አልባ አድርገው አሁን ላይ ላሉት አመራሮች ያስረከቡት ትህነግ አንድም እርምጃ ወደፊት መራመድ ያቃተው፣ ሌሎችን ሲያበስብስ ንሮ ራሱ ሊድን ከማይችል የማበስበሻው ባህር ውስጥ ሰጥሞ እየተወራጨ ነው። ፓርቲው አቶ መለስ ከተሰናበቱት ጊዜ አነስቶ ጥርስ የሌለው አንበሳ እስከሆነበት እሰከዛሬ ድረስ ያለፈበትን የመበስበስ ሂደት ውጤት እንዴት እንደበላውና እንደደፋው አደፋፉን ላስተዋሉ ብዙ ማብራሪያ የሚቀርበበት አይሆንም።

ከአቶ መለስ ዜናዊ ኅልፈት በኋላ ዘይት በጨረሰ ርዕዮተ ዓለም ሲንፏቀቅ የነበረው ትሕነግ ሀገሪቱን እና ህዝቡን ሊቅሙ የሚያስችል ብሩህ አዕምሮ ላላቸው ወጣት የፖለቲካ አመራሮች የፖለቲካ ምሕዳሩን ከማስፋት ይልቅ ጠረቀመ። ይባስ ብሎ አፋኝ እና አምባገነን በሆነ አካሄድ ለየትኛውም የህዝብ ጥያቄ እና ተሃድሶ አሻፈረኝ ማለትን መረጠ። በዚህ ኋላ ቀር አመለካከቱ የህዝብን ተቀባይነት በማጣት የመበስበስ ሂደቱን ያፋጠነው ትሕነግ ብዙም ሳይቆይ አመፅ በወለደው የህዝብ የአብዮት ማዕበል ከስልጣን ተወገደ።

የስልጣን ዘመኑ ካበቃ በኋላ የነበረውን አምባገነናዊ የበላይነት ያጣው ትርሕነግ “ነፃ አወጣዋለሁ” የሚለውን የትግራይ ህዝብ ምሽግ በማድረግ ለሚሊዮኖች ደም መፍሰስ፣ ለመቶ ሺህዎች መደፈር እና መፈናቀል ምክኒያት የሆነውን በዘመናዊው የኢትዮጵያ ታሪክ አስከፊውን ጦርነት በማወጅ የበሰበሰውን ፓርቲውን ይዞ የትግራይ ህዝብ ላይ ወደቀ።

“እኔ ካልበላሁ ጭሬ ልድፋው” እንደምትለው ዶሮ መበስበስ አናቱ ላይ የወጣበት ትህነግ ለውጡን ተቀብሎ አብሮ ከምስራት ይልቅ አራት ኪሎ እያለ የረሳውን መከረኛውን የትግራይን ሕዝብ ይዞ ለመገንደስ ወደ ትግራይ አቅንቶ አዲስ የማበስበስ ዘመቻ ጀመረ። ከስህተት የመማርና ራስን የማሳደግ፣ የማረቅና የማዘመን ባህል የሌለው ትህነግ በዘረፈው ሃብት ትግራይ ውስጥ ጦር እየሰበቀ፣ ከበሮ እየደለቀ በብስባሽ ውስጥ ሰክሮ በማስከር በጀመረው ጦርነት የሆነው ሁሉ ለታሪክ የሚተው ነው። ራሱ የትግራይ ሕዝብ ጊዜው ሲደርስ የሚጎለጉለው የግፍ ጥግ ነው።

ዛሬም ቢሆን ይህን የበሰበሰ አስተሳሰብ እና የበሰበሰ አመራር ከትግራይ ህዝብ ከስር ተነቅሎ ካልተጣለ ትግራይን እና ምስኪኑን የትግራይ ህዝብን ከመከራው አያገገምምና የሚመከግተን ሁሉ አንድ እንበል። ብሎ ብሎ ከጭረሰን፣ ከዘረፈን፣ ከደፈርን፣ በጅምላ ከጨረሰን፣ እንደ ሕዝብ ለምን አልጨረስኳቸውን ብሎ ካዘነው ሻዕቢያ ጋር የሚዘፍነው ትህነግ የመበስበሱ ልክ ሞፍራል አልባ ስላደረገው ከዚህ የከፋው ሳይመጣ እንነሳ።

የትግራይ ነባር መኮንን

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በፀረ-ሽብርተኝነት እና በመፈራረስ መካከል ያለቸው ሶማሊያ “ሌላ አፍጋኒስታን?” የአሜሪካና አቋምና የአል-ሸባብ….

አዲስ ሪፖርተር - እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2021 ዓለምን ያስገረመው የአፍጋኒስታን...

የኢትዮጵያ፣ ህንድ እና እስራኤል ስትራቴጂካዊ አጋርነት የቀጠናው ፖለቲካዊ ትኩሳት፤ የኤርትራ መጨማደድ

አዲስ ሪፖርተር - ባለፈው ማክሰኞ በኢየሩሳሌም የተካሄደው የህንድ እና...

ጀርመንና ሕንድ ግንኙነታቸውን ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት አሳደጉ

አዲስ ሪፓርተር - የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ፍሪድሪክ ሜርዝ በሕንድ...

መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ ኬላ ላይ ተያዘ፤ መዳረሻው ሸዋ ሮቢት ነበር

አዲስ ሪፖርተር - መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ...