መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ ኬላ ላይ ተያዘ፤ መዳረሻው ሸዋ ሮቢት ነበር

Date:

አዲስ ሪፖርተር – መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ ኬላ ላይ ተያዘ፤ ዓላማው ሸዋ ሮቢት ላለው የፋኖ ኃይል ለማድረስ ነበር ኢትዮጵያን ለማተራመስ ከላኪዎቹ ጋር በመሆን ታጣቂ የሚያደራጀውና መሳሪያ የሚያጋግዘው የኤርትራ መንግስት የላከው የጦር መሳሪያ ተያዘ።

ይኸው መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ የተጓጓዘው በመቐለ በኩል ሲልሆን መዳረሻው ሸዋ ሮቢት እንደነበር ዜናውን ያጋሩን ክፍሎች አስታውቀዋል። እንደ መረጃው ከሆነ መሳሪያው እንዲደርስ የታሰበበት ቦታ ከመድረሱ በፊት በዓየርና በምድር በተደረገ ክትትል የተያዘው ወልደያ ኬላ ላይ ነው።

ከኬላው የተገኘው መረጃ እንደሚያመልክተው አዘዋዋሪዎቹ መሳሪያውን ከጫነው አይሱዙ ተሽከርካሪ ጋር ነው የተያዙት። ንበመስል የተደገፈርው መረጃ እንደሚያሳየው የጦር መሳሪያውን በድብቅ ለማሳለፍ በሚጠረጠሩ ቦታዎች በምሽት በመጓዝና በተለያዩ ቁሶች ውስጥ ለመደበቅ ሙከራ ተደርጓል።

“ለሻቢያ መንግስት ድልድይ ሆኖ እየሠራ ያለው ፅንፈኛው የትሀንግ ቡድን ፅንፈኛው ፋኖን በማስታጠቅ የሀገራችንን ሰላም ለማደፍረስ አቅዶ ከኤርትራ በመቐሌ በኩል በስውር የላከውን 41 ሺህ 999 የክላሽ ጥይት፣ 14 ሺህ የብሬን ጥይት እና 800 የድሽቃ ጥይት በአጠቃላይ 56 ሺህ 799 ጥይቶች በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ.አ B94744 የጭነት አይሱዙ ተሽከርካሪ ከሲሚንቶና ከብሎኬት ጋር አመሳስሎ በመጫን በአማራ ክልል ወልዲያ ከተማ አድርገው ወደ ሸዋሮቢት ለማስገባት ሲያጓጉዙ በወልዲያ የፍተሻ ጣቢያ ላይ በቁጥጥር ስር ውሏል። በሸዋ አካባቢ የአገር መከላከያ ሰራዊት ሰፊ ኦፕሬሽን በማድረግ አካባቢዎችን እያጸውዳ በመሆኑ ተተኳሽ መሳሪያ ለማቀበል የተደረገ ሙከራ መሆኑም ታውቋል።” ሲል ፖሊስ ዘግይቶ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ህዝብ በመሳደብ በሰጡት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያን በጦረነት ጠማቂነት መክሰሳቸው፣ ይህንኑ ክሳቸውንና ስድባቸውን ኢትዮጵያዊ የሚባሉ ሚዲያዎችና የተቃዋሚ ልሳኖች፣ እንዲሁም ሻዕቢያ የሚያስተዳዳርቸው የዩቲዩብ ገጾች ከትናንት ጀምሮ ሲያስተጋቡ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ትህነግ በማስተላለፉ ስራ እንጁ እንዳለበት በመገለጹ የክልሉን አስተዳደር ጸጥታ ቢሮ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ከላይ በምስሉ እነደተመለከተው የተያዘው መሳሪያ ከብሎኬት ስር ተደረድሮ ሲዛወር ነበር። በተያዙት ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ በተደረገ የመጀመሪያ ምርመራ መሳሪያው ከሻእቢያ ተልኮ በትህነግ በኩል መተላለፉ ተረጋግጧል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የዓለም የነዳጅ ቀውስ እና የኢትዮጵያ ፈተና [ታሪካዊ አርበኝነት ጥሪ] ወቅቱን ለሚመረምሩ ሁሉ

ኢትዮጵያን እንወዳለን፣ ኢትዮጵያ አገሬ ናት፣ ኢትዮጵያ እናቴ ናት፣ ሌላ...

ወሳኙ የአደዋ ድል ሚስጢር – የአፄ ምኒልክ አዋጅ

ይህ ማህበራዊ ውል መላውን ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር አስተሳስሯል።...

“አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ – ኢህአፓ አሳማነቷን በሊፒስቲክ ልትደብቅ?

በ1980ዎቹ ነበር፤ በዘመኑ ቀልድ የሚያበዛ ታዋቂ ጋዜጠኛ በአንድ የታወቀ...

ጃዋር መሐመድ የአመጽ ጥሪውን የሰረዘው ለአስቸኳይ ስራ ግብጽ ተልኮ መሆኑ ታወቀ

አዲስ ሪፖርተር - ባለፈው ማክሰኞ በኢትዮጵያ ሕዝብ አመጽ እንዲያቀጣጥል...