የሮይተርስ የሀሰት ዘገባ ሴራ – በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ የዲፕሎማሲና የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ልክፍት በማስረጃ ሲጋለጥ

Date:

ታዋቂው የመከላከያ መረጃ ተንታኝ Janes የሰጠው አስተያየት ነው፤ ሮይተርስ በዘገባው ላይ “Janes said it could not confirm the site was military based on their analysis of the imagery” በማለት የገለጸው ሀሳብ፣ የቀረበው ምስል ወታደራዊ እንቅስቃሴን እንደማያሳይ በተዘዋዋሪ ያረጋግጣል። ይህ ሆኖ ሳለ ሮይተርስ “ሚስጥራዊ የጦር ካምፕ” የሚል ስያሜ መስጠቱ ዘገባው አስቀድሞ ኢትዮጵያን ለመወንጀል ታቅዶ የተሰራ መሆኑን ያሳያል።

አዲስ ሪፖርተር – የእርስ በስር ጦርነት ውስጥ ከምትገኘው ሱዳን ጋር በሚጎራበተው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የአማጺው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሥልጠና ካምፕ መገንባቱን ከምንጮች እና ከሳተላይት ምሥሎች አረጋገጥኩ ሲል ሮይተርስ አስታውቋል። የሱዳን ፈጣን ኃይሎች ብሉ ናይል ዙሪያን መቆጣጥራቸውን ተከትሎ የሱዳን መንግስት ላሰማው ክስ ሮይተርስ ድጋፍ የሚሆንና ኢትዮጵያን የሚወነጅል መረጃ ነው ያሰራጨው፤

ይህንኑ ሮይተርስ ራሱ “ያልተረጋገጠ” በማለት ባዋጣው ዘገባ የጠቀሳቸው ሰዎችም አይታወቁም። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሥልጠና ትሰጥበታለች በተባለው በዚህ ካምፕ ውስጥ የሚገኙት አብዛኞቹ ምልምሎች ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ በወሬ መስማቱን ጠቅሶ ሮይተርስ ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 3/2018 ዓ.ም. ያወጣውን “የምርመራ” የተባለ ዘገባ አዲስ ሪፖርተር ሴራና ቅጥፈት መሆኑን አረጋጧል።

በአሁኑ ዘመን ሀሰተኛ መረጃ (Disinformation) እንደ ቀጥተኛ ወታደራዊ ጥቃት ሁሉ ሀገርን የማዳከም አቅም ያለው አደገኛ የጦር መሣሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። ታሪካዊ ጠላቶች የሀገሪቱን ሰላምና አንድነት ለመናጋት የግድ የጦር ሜዳ ውጊያ ውስጥ መግባት አይጠበቅባቸውም፤ ይልቁንም እንዲህ ያሉ የፈጠራ ዘገባዎችን በተፅዕኖ ፈጣሪ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በማሰራጨት የህዝብን ስነ-ልቦና መረበሽ እና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ የተሳሳተ አመለካከት እንዲፈጠር ማድረግ ዋነኛ ስልታቸው ነው። ይህ “ድብቅ ጦርነት” በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በማደግ ላይ እና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ባላቸው ሀገራት ላይ ሆን ተብሎ የሚሰነዘር የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ጥቃት አካል ነው። አዲስ ሪፖርተር ኢትዮጵያ የግራጫው የሳይበር ጥቃት ለማድረግ የተያዘውን ዕቅድ አስቀድማ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።

ዛሬ ሮይተርስ በድረ ገፁ Ethiopia builds secret camp to train Sudan RSF fighters በሚል ርዕስ ያወጣው የምርመራ ዘገባ የዚሁ የሃሰተኛ መረጃ ዘመቻ አካል ነው። ሮይተርስ በዘገባው የሳተላይት ምስሎችን እንደ ዋነኛ ማስረጃ ማቅረቡ፣ የበቴክኖሎጂ የታገዘ የሀሰት መረጃ ትንተናን (Technical Disinformation) ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የመጠቀም አንዱ ማሳያ ነው። የሳተላይት ምስሎች በራሳቸው ገለልተኛ ቢሆኑም፣ በምስሎቹ ላይ የሚሰጠው ትርጓሜ ግን እንደ ተንታኙ ፍላጎት ሊቀያየር ይችላል። ዘገባው በሲቪል ግንባታዎች ወይም በመደበኛ የመከላከያ መሠረተ ልማቶች ላይ “የውጭ ተዋጊዎች ካምፕ” የሚል የፈጠራ ስያሜ በመስጠት፣ ምስሎቹን ለፖለቲካዊ ጫና ማሳደሪያነት ተጠቅሞባቸዋል።

በመሆኑም ይህን የሮይተርስ ዘገባ የሀሰት መሆኑን ለማረጋገጥ ዘገባውን በአስተውሎት እስከ መጨረሻ ያነበበ ሰው በቀላሉ መረዳት ይቻላል። አዲስ ሪፓርተር ይህንን የሀሰት ዘገባ ሌላ መስረጃና እማኝ ሳያስፈልጋት እንደሚከተለው በዝርዝር አጋልጣ እርቃኑን አስቀርታዋለች። 

የሮይተርስ የምርመራ ዘገባ ሲጋለጥ

በመጀመሪያ ዘገባው እራሱ የጠቀሳቸው መረጃዎች እርስ በርሳቸው የሚጋጩ መሆናቸውን ማየት ይቻላል። ዘገባው የሳተላይት ምስሎችን እንደ ዋነኛ ማስረጃ ቢያቀርብም፣ በምስሎቹ ላይ የቀረበው ትርጓሜ ግን ተዓማኒነት የጎደለው ነው። ለዚህም ትልቁ ማስረጃ ታዋቂው የመከላከያ መረጃ ተንታኝ Janes የሰጠው አስተያየት ነው፤ ሮይተርስ በዘገባው ላይ “Janes said it could not confirm the site was military based on their analysis of the imagery” በማለት የገለጸው ሀሳብ፣ የቀረበው ምስል ወታደራዊ እንቅስቃሴን እንደማያሳይ በተዘዋዋሪ ያረጋግጣል። ይህ ሆኖ ሳለ ሮይተርስ “ሚስጥራዊ የጦር ካምፕ” የሚል ስያሜ መስጠቱ ዘገባው አስቀድሞ ኢትዮጵያን ለመወንጀል ታቅዶ የተሰራ መሆኑን ያሳያል።

በሁለተኛ ደረጃ ዘገባው የተመሰረተባቸው ምንጮች ማንነት ጥርጣሬ የሚጭር ነው። ሮይተርስ በዘገባው ውስጥ “Eight sources, including a senior Ethiopian government official…” እና “The news agency spoke to 15 sources…” እያለ ቢገልጽም፣ አብዛኛዎቹ ምንጮች በስም ያልተጠቀሱ መሆናቸው መረጃው ተዓማኒነት እንዲያጣ ያደርገዋል። እንዲህ ያሉ ለደህንነት ሲባል ስማቸው አልተጠቀሰም የሚባሉ ምንጮች፣ ብዙውን ጊዜ ለፖለቲካዊ ፍጆታ የሚፈጠሩ ወይም በአንድ ወገን የሚሰጡ የተዛቡ መረጃዎች መሆናቸው የታወቀ ነው። ይህ መረጃውን በገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል።

በሦስተኛ ደረጃ፣ ዘገባው የአሶሳ አውሮፕላን ማረፊያን ከሱዳን ጦርነት ጋር ለማገናኘት የሄደበት ርቀት እጅግ አሳሳች ነው። ሮይተርስ “The analyst and the expert said the airport had become instrumental in supplying the RSF across the border in Sudan” በማለት ያሰፈረው ሀሳብ፣ ምንም ዓይነት ተጨባጭ የበረራ መረጃ (Flight tracking) ወይም ተያያዥ ማስረጃ የሌለው ግምት ብቻ ነው። ኢትዮጵያ የራሷን ድንበርና እንደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ያሉ ስትራቴጂካዊ ተቋማትን ለመጠበቅ የአየር ኃይል አቅሟን የማጠናከር ሉዓላዊ መብት ያላት ቢሆንም፣ ይህንን ከጎረቤት ሀገር አማጺያን ጋር ለማገናኘት መሞከር የተለመደ የፕሮፓጋንዳ ስራ ነው።

በአራተኛ ደረጃ፣ በዘገባው ውስጥ የተጠቀሱት የጭነት መኪናዎች መረጃ እጅግ ደካማ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ነው። ሮይተርስ “The news agency could not independently verify what the trucks carried…” በማለት በግልጽ የተቀመጠው ሀሳብ፣ በጭነት መኪናዎቹ ውስጥ ሰራዊት ስለመኖሩ ወይም ስላልመኖሩ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ እንደሌለው ያሳያል። መኪናዎቹ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ሞዴል መመሳሰላቸው ብቻ፣ ለሌላ ሀገር ታጣቂዎች ስልጠና እየዋሉ ነው ለማለት የሚያስችል በቂ መነሻ ሊሆን አይችልም። ይህ የሚያሳየው ዘገባው በግምት ላይ የተገነባ መሆኑን ነው።

በአምስተኛ ደረጃ፣ የዘገባው አዘጋጆች ያሉበት ቦታና የዘገባው ጊዜ የግብፅን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነው። ሮይተርስ በመጨረሻው ክፍል ላይ “Additional reporting by Alexander Dziadosz, Nafisa Eltahir and Ahmed Shalaby in Cairo” በማለት የዘገባው አንድ አካል የሆኑ ጋዜጠኞች መቀመጫቸው ካይሮ መሆኑን ገልጿል። ግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያላትን ፖለቲካዊ ፍላጎት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያን በቀጠናው ውስጥ እንደ ስጋት አድርጎ የማቅረብ ጽኑ ፍላጎት እንዳላት ይታወቃል። ዘገባው በዚህ መልኩ መቀናበሩ፣ የግብፅን የዲፕሎማሲ አጀንዳ ለማስፈጸም የታለመ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።

በስድስተኛ ደረጃ፣ ዘገባው በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) መካከል ያለውን የልማት ትብብር ለክፉ ዓላማ ለማዋል ሞክሯል። ዘገባው “UAE financed the camp’s construction and provided military trainers…” የሚለውን ክስ ቢሰነዝርም፣ ሮይተርስ እራሱ “The news agency could not independently verify UAE involvement in the project or the purpose of the camp” በማለት ሀሰተኝነቱን በራሱ ቃል አረጋግጧል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግልጽ የኢኮኖሚ ትብብር እንደ “ሚስጥራዊ ወታደራዊ ጥምረት” ተደርጎ መቅረቡ፣ በኢትዮጵያ ላይ ዓለም አቀፍ ጫና ለመፍጠር የተደረገ ሙከራ ነው።

በመጨረሻም፣ ዘገባው የሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ያለውን ቀደመ የጠላትነት አመለካከትና ትንኮሳ ችላ ብሎታል። ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት በኃይል መያዟና ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎችን እያሰለጠነች መሆኑ የታወቀ ሀቅ ሆኖ ሳለ፣ ሮይተርስ ኢትዮጵያን እንደ “ጣልቃ ገብ” አድርጎ መሳሉ ፍጹም ሚዛናዊነት የጎደለው ነው። ይህ ዘገባ ኢትዮጵያ በቀጠናው ያላትን የሰላም አስከባሪነት ሚና ለማሳነስና በሀሰተኛ የሳተላይት ትንታኔ ህዝብን ለማሳሳት ሆን ተብሎ የተዘጋጀ የዲን-ኢንፎርሜሽን (Disinformation) ውጤት ነው።

የባንዳዎች የክህደት ቅሌት ሲገለጥ

በውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ የተቃዋሚ ኃይሎች፣ እንዲህ ያሉ በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የተቀነባበሩ የሀሰት ዘገባዎችን ሳይመረምሩ እንደ እውነት አድርገው መውሰዳቸው ትልቅ ባንድነት እና ብሔራዊ ክህደት ነው። ይህ ድርጊት የሀገሪቱን ገጽታ ከማበላሸቱም በላይ፣ የውጭ ኃይሎች የኢትዮጵያን የውስጥ ልዩነት ተጠቅመው ሀገራዊ አንድነትን እንዲሸረሽሩ ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል። ተቃዋሚዎች ከገዥው ፓርቲ ጋር ያላቸውን ልዩነት እና የሀገርን ሉዓላዊነትና ደህንነት ለይተው ማየት አለባቸው።

እንዲህ ያሉ ዘገባዎች በስሌት የሚቀነባበሩት፣ ቀደም ሲል የነበሩ የተሳሳቱ አመለካከቶችን እና ጥርጣሬዎችን እውነት አስመስሎ በማቅረብ የህዝብንና የአመራርን አንድነት ለመሸርሸር ነው። በተለይም የታሪካዊ ጠላቶች የሀሰት መረጃ ትንታኔን በመጠቀም፣ ኢትዮጵያን በቀጠናው ግጭት ተላላኪ አስመስለው ለማቅረብ የሚሰሩት ስራ በሀገር ወዳድ ዜጎች ዘንድ በቀላሉ ሊታወቅ ይገባል። የፖለቲካ ልዩነትን ለሀገር ጠላቶች በጎጆ መክፈቻነት ማቅረብ የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል አደገኛ አካሄድ ነው።

አሁን ባለንበት ወቅት ታላላቅ ኃይላን እና መካከለኛ ሀገራት በቀጠናችን ባለው ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ ከፍተኛ የፉክክር ሽሚያ እያደረጉ ይገኛሉ። በዚህ የጥቅም ግጭት መሃል ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር የምታደርገው ጥረት ፍሬ እንዲያፈራ የአላማ እና የአመራር አንድነት ወሳኝ ነው። ተቃዋሚ ኃይሎች ያለማስረጃ የሚለቀቁ ወሬዎችን እንደ ድጋፍ መረጃ ሲጠቀሙ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት እና የመደራደር አቅም ያዳክሙታል።

ለሀገራዊ ሉዓላዊነት ዘብ መቆም

የሀሰት መረጃዎች የታለሙት በዋነኝነት በዜጎች መካከል የመተማመን መንፈስን ለመስበር እና በሀገሪቱ የደህንነት ተቋማት ላይ ጥርጣሬ ለመዝራት ነው። ተቃዋሚ ኃይሎች እነዚህን የፈጠራ ወሬዎች ሲያስተጋቡ፣ በሰራዊቱ እና በደህንነት መዋቅሩ ውስጥ ቅሬታ እንዲፈጠር በማድረግ ለሀገር መከላከያ የሚውለውን የጋራ አቅም ይከፋፍሉታል። አንድነት በሌለበት ሁኔታ የሀገርን ዳር ድንበር ማስከበርና ከውጭ የሚመጡ ትንኮሳዎችን መመከት የማይቻል በመሆኑ፣ እንዲህ ያለው ድርጊት በቀጥታ ለጠላት እንደ መረዳዳት ይቆጠራል።

በመሆኑም፣ ማንኛውም ዜጋም ሆነ የፖለቲካ ኃይል እንዲህ ያሉ ቴክኖሎጂን የለበሱ ዘገባዎች ሲወጡ በከፍተኛ ጥንቃቄና ጥርጣሬ ሊመለከታቸው ይገባል። ምስል ስለታየ ወይም ታዋቂ የሚዲያ ተቋም ስለዘገበው ብቻ መረጃውን እንደ ወርቅ እውነት መቀበል፣ ሳያውቁ ለጠላት የፕሮፓጋንዳ ማሽን ነዳጅ መሆን ነው። የሳተላይት ምስሎችን መሠረት ያደረጉ ዘገባዎች ሳይንሳዊ ትንተናን ሽፋን አድርገው የሚመጡ የሴራ ስራዎች ሊሆኑ ስለሚችሉ፣ ከጀርባው ያለውን የጂኦ-ፖለቲካዊ ፍላጎት መመርመር ለሀገር ደህንነት ወሳኝ ነው።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ኃይሎች ከምንም ነገር በላይ ለሀገር ሉዓላዊነት ቅድሚያ መስጠት ይኖርባቸዋል። የአላማ አንድነትን ማጣት ለታሪካዊ ጠላቶች የሚሰጥ ትልቅ ሲሳይ በመሆኑ፣ በሀገር ጉዳይ ላይ በአንድ ድምጽ መቆም የህልውና ጉዳይ ነው። እውነታው ከሚነዛው ወሬ እጅግ የራቀ መሆኑን በመረዳት፣ ለሀሰተኛ መረጃዎች በር አለመክፈትና ለሀገራዊ ሉዓላዊነት ዘብ መቆም ይገባል። የሀገርን ሉዓላዊነት አሳልፎ ለፖለቲካ ትርፍ መሮጥ መጨረሻው የሀገር መፍረስ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

እንደ ማስታወሻ

ይህን መሰረት የለሽ ቅንብር በማንጠልጠል በማህበራዊ ሚዲያ የሱዳን ወገንተኛ፣ የግብጽ ተቀጣሩና የሻዕቢያ ተላላኪ ሆነው የሚወራጩ አካላት ሱዳን በታሪኳ ኢትዮጵያ ላይ አማጺ ስታደራጅ የኖረች፣ አሁንም ይህንኑ ተግባሯን አጠናክራ የቀጠለች፣ አማጺ ማደራጀትና ማስታተቅ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ድንበር በመጣስና ውጊያ በመክፈት ጉዳይ የምታደርስ፣ ከሻዕቢያ ጋር ግንባር ገጥማ ኢትዮጵያን ለመውጋት የውስጥ ልክስክሶች ሰብስባ በዝግጅት ላይ ያለች አገር ናት። ከሱዳን ልምድና የኖረ አቋም አንጻር መንግስት ያሻውን መንገድ ቢከተል፣ ገና ለገና ፓርቲን በማውገዝ ሂሳብ አገር ላይ ውንብድና መፈጸም በዘመን የማይሻር ነወር እንደሆነ ማወቅ ጠቃሚ ይሆናል። “ኢትዮጵያዊ ነን” ካልን በምንም መስፈርት ከኢትዮጵያ ይልቅ የሱዳን ጉዳይ ሊገዝፍብን አይችልም። አዲስ ሪፖርተር በምንም መስፈርት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም የማትደራደረውም በዚሁ ስሜትና ዕምነት ነው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“በመናበብ አመጽና ረብሻ ለመቀስቀስ ከፓርቲዎች ጋር ተስማምተናል” ጃዋር “በትርምስና በዓመጽ አናምንም” ፓርቲዎች

አዲስ ሪፖርተር - “እኛና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ሁለት ድርጅት...

A Critical Examination of Reuters’ Geopolitically Motivated Allegations

Addis Reporter - The recent Reuters report alleging Ethiopian training...

Exposing the Reuters Disinformation Campaign: A Strategic Attack on Ethiopia’s Sovereignty

Addis Reporter – Special Investigative Analysis In the contemporary era...