ኦሮሞ የአመጽ ጥሪን ባለመቀበሉ ፕ. ሕዝቅዔል አዲስ የኦሮሞ “አብሮነት” መሳይ ስብስብ ሊመሰርቱ ነው

Date:

አዲስ ሪፖርተር – አብሮነት በሚል ስያሜ አቶ ልደቱ አያሌው የመሰረቱት ማህበራ ውስጥ የቦርድ አባል የነበሩት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ አዲስ በኦሮሞዎች ብቻ የሚመራ ህብረት እየፈጠሩ መሆኑ ተሰማ። ፕሮፌሰሩ ባለፈው ሳምንት ከአብሮነት ዳይሬክተሮች ቦርድ ራሳቸውን ማሰናበታቸውን አስታውቀው ነበር። የአቶ ልሰዱ አብሮነት እየሞተ መሆኑ ተመክቷል። ሕዝቅዔል አዲስ አብሮነት መሰል ማህበር የሚያቋቁሙት ኦሮሚያ ላይ ሕዝብ አመጽ ባለመቀበሉ በትህነግ መመሪያ ነው።

“የሰማይ ላይ ትዕይንት” በሚል መሳሪያ አንስተው ጫካ የገቡ፣ በአገር ውስጥ ያሉ የተወሰኑ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በአሜሪካ ያሉ የተለያዩ አደረጃጀትና ስብስብ መሪዎች፣ ሚዲያ ላይ የተሰማሩ፣ እንደ አቶ ስብሃት ነጋ ያሉ የቀድሞ የትህነግ መስራችና መሪ፣ በፖለቲካው ዙሪያ አስተያየት በመስጠት የሚታወቁ፣ ራሳቸውን አንቂ ያሉ፣ የኦሮሞ ልሂቃን ወዘተ የተካተቱበት የዙም ስብስበባ ተደርጎ አብሮነት መቋቋሙ የሚታወስ ነው።

በዚሁ አቶ ልደቱ መሪ በሆኑበት “|አገር አነቀጥቅጥ” የተባለ የሰማይ ላይ ሰልፍ የተሳፈፉ የኦሮሞ ልሂቃን በሳምንቱ ሲያትል ተሰብስበው “በርዕዮተ ዓለምም ሆነ በዓላማ አንገናኝም” በሚል “አገር አንቀጥቅጥ” የተባለውን ስብስብ ተለዩ። ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል እና ጃዋር መሐመድ ወጣ ገባ እያሉ ቢቀጥሉም ሕዝቅዔል ግን አብሮነት ቦርድ ውስጥ ሆነው አብሮነት እንደሚፈርስ፣ የገቡትን ሊያፈርሱት እንደሆነ እሳቸው ወደሚያቋቁሟቸው ስብስብ ሊወስዷቸው ላሰቡ ይናገሩ እንደነበር በአዲስ ሪፖርተር መዘገቡ አይዘነጋም።

በአቶ ልደቱ አብሮነት ቦርድ አመራር ውስጥ ካሉት መካከል የደቡብ፣ የጋምቤላና የሶማሌ ተወካይ ተብለው የተካተቱትን በግል በማነጋገር “ነፍጠኞች የማይቦርቁበት ህብረት መስርተናል” በማለት ካግባቧቸው መካከል ሁለቱ ለአዲስ ሪፖርተር ምስክርነታቸውን ሲሰጡ “ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ቀደም ሲል እንዳሉት አብሮነትን የተለዩት የራሳቸውን ስብስብ ስለመሰረቱ ነው” ብለዋል።  

የአብሮነት ቦርድ አባል ከሆኑት መካከል የዘወትር የአዲስ ሪፖርተር መረጃ ሰጪ ለዋሽንግቶን ተባባሪ እንዳሉት “የአቶ ልደቱ አብሮነት በመርህ ደረጃ ፈርሷል” በማለት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል አዲስ እያቋቋሙ ስላሉት ሕብረት የሚያውቁትን አስረድተዋል። የተቋቋመበትን ምክንያት አስታውቀዋል።

እነ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል አዲስ ሕብረት እንዲያቋቁሙ መመሪያ የተሰጣቸው ተቀማጭነታቸው አሜሪካ ከሆነው የትህነግ አንጋፋ አመራሮች ናቸው። የዚህ ምክንያት ደግሞ ሁለት ነው።

“በኦሮሚያ ረብሻና ዓመጽ ሊነሳ አለመቻሉና ኦፌኮና ኦነግ በአመጽ ጥሪ ውስጥ ተሳታፊ ለመሆን ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አዲስ አደረጃጀት ያስፈልጋል” በሚል ሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች እንደሆነ ዜናውን ያስታወቁት አመልክተዋል።

“አብሮነትና ሌሎች ጥምረቶች በሰላም ስም ከጀርባ ያዘሉት ኦሮሞን የማጥቃትና ኦሮሞ እንዴት አገር ሊመራ ይፈቀድለታል። የጋላን መንግስት ከአራት ኪሎ እናስወግድና የአባቶቻችንን ርስት እናስመልስ” ከሚሉ ኃይሎች ጋር በስም የሚታወቁ የኦእሮሞ ልሂቃን እነ ጃዋርን ጨምሮ በዚህ ህብረት ውስጥ መሳተፋቸው በኦሮሚያ ውስጥ ሕዝቡን እንዳበሳጨ፣ በውጭ አገር ያሉትንም የሚታወቁ ፖለቲከኞች እንደከፋፈለ እነ ስብሃት ነጋ አንስተዋል።

“ኦነግም ሆነ ኦፌኮ ከዚህ አንጻር ሕዝብ እንዳያገላቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋሉ” በሚል በተሰጠ አቅጣጫ ምንም እንኳን በውስጥ አብረው ቢሰሩም ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል አዲስ የአብሮነት ማህበር እንዲያቋቁሙ በመወሰኑ ከአብሮነት ቦርድ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተው እንዲለቁ መደረጉን ድብዳቤያቸውን በማያያዝ የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ ዘግቧል።

የጋምቤላ፣ የደቡብና የሶማሌ ተወካዮችን በማስኮብለለ አዲስ የሚቋቋመው ኦሮሞዎች የሚመሩት አዲስ አብሮነትን መሰል ማህበር መቋቋም የአቶ ልደቱን ማህበር እንደሚያፈርሰው ከወዲሁ ተመልክቷል። አብሮነት በሶስተኛ ስብሰባው በኢትዮጵያም ሆነ በአሜሪካና አውሮፓ ታላላቅ ሰላማዊ ሰልፎች ለማካሄድ አመቺ ሁኔታ እንደሌለ በሻዕቢያ ወኪል አቶ ነዓምን ዘለቀ አማካይነት መገለጹን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። አቶ ነዓምን ይህን ያሉት የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ወይም ዲፕሎማቶች እንደ ቀድሞ የሚሰሙ ባለመሆናቸው ነው። ይልቁኑም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እንዲወገዱ ጫናው በመበርታቱና በውጭ ያለው ስብስብ የሚመራው በሻዕቢያ መሆኑ ኪስራ ማስከተሉንም የሚገልጹ አሉ።

በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች አመጽ ለማቀጣጠል ከአብሮነት ውስጥ የተወለደው “የጋራ ግብረኃይል” የተባለውና አቶ ጃዋርን ጨምሮ አምስት ስራ አስፈጻሚ ያቋቋመው ስብስብም በተመሳሳይ የመበተን ዕድል እንዳጋጠመው እየተገለጸ ነው። ስብስቡን የተቀላቀለው ጃዋር ከኦሮሞ ህዝብና ልሂቃን የተሰነዘረበትን ተቃውሞ ለማስተንፈስ፣ ስብስቡን በይፋ ባይቀላቀልም ከአቶ ነዓምን ጋር አብሮ እየሰራ መሆኑን የዲሲ ተባባሪያችን በእንቅስቃሴው ዙሪያ ያሉትን ጠቅሶ አመልክቷል።

አቶ ጃዋርና አቶ ነዓምን ከሻዕቢያ በሚሰጥ ትዕዛዝ መሰረት የግብጽን መሰረታዊ ፍላጎትና ዕቅድ የሚያስጠብቅ ዘመቻ በኢትዮጵያ ላይ በቅብብል እያሰራጩ እንደሆነ ማህበራዊ ገጾቻቸውን የሚከታተሉ “አዲሱ ጽምዶ” በማለት እየሸረደዷቸው ነው።

አቶ ጃዋር ቀደም ሲል የነበረውን የግንኙነት መስመር በመጠቀም በኦሮሚያ አመጽ እንደሚያስነሳ ቢያስታውቅም ይህ እስከታተመ ድረስ ሰሚ አግኝቶ የተሞከረው አመጽ አልተሰማም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ በማህበራዊ ሚድያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ እንደ ቀድሞ ዘመቻ የጀመረው ጃዋርን ጨምሮ ከመንግስት ጋር ሽምግልና የጀመሩ ስለመኖራቸውን እየተሰማ ነው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ከድጡ ወደ ማጡ – የሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የጦርነት ስጋት እና ተጠባቂው የቀጣናው መናወጥ

አዲስ ሪፖርተር - ዓለም አቀፉ ክራይሲስ ግሩፕ ሰሞኑን ባወጣው...

በሱዳን ጦርነት ብሄራዊ ጥቅሙን አሳልፎ እየሰጠ ያለው ደናቁርት “ኢትዮጵያዊ ሊሕቅ” እና ተጨባጩ እውነታ

እነ ጀዋር መሃመድ እና መሰሎቹ የድንቁርና ጌቶች  መሃመድ ዳጋሎ...

“ጃዋር ለምን ከጀርባ ይደበቃል? እኛ እንደ እናንተ ከግብጽ ገንዘብ አናገኝም”

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያምጽና እንዲነሳ የሚጠይቅ መግለጫ...