በሕዝብና በታጣቂው የተገፋው የትህነግ መጨረሻና የወጣቶች የድረሱልን ጥሪ፤ “መንግስ መውጪያ ያመቻችልን”

Date:

አዲስ ሪፓርተር – በትግራይ ከቀን ወደ ቀን የጦርነት ስጋት መባባስ ያሳሰባቸው የትግራይ ወጣቶች ለመንግስት ጥሪ አሰሙ። “መንግስት መውጪያ ያመቻችልን” በማለት የጦርነቱ ሰላባ መሆነ እንደማይፈልጉ አመልክተዋል። የትግራይ ሰላም ኃይሎች የፕሮፓጋንዳ ክፍል የሰላም ኃይሉ ባለበት ሁሉ በመሸሽ ወጣቶችና ታጣቂዎች አሁን እያደረጉ እንዳሉት እንዲቀላቀሉ አሳስቧል። ከዚያ በሁዋላ ወዴትና የት መቆየት እንዳለባቸው አቅጣቻ እንደሚሰጥ

በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው የትህነግ አንድ ክፋይ፣ ላለፉት ዓመታት ሲከተለው በነበረው የጥፋትና የትርምስ መንገድ ምክንያት እራሱ በለኮሰው እሳት እየተቃጠለ መሆኑን በርካታ ማሳያዎችን በመዘርዘር የሚገልጹ ተበራክተዋል። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት የትህነግ ነገር እያበቃ ነው። ሌተናል ጻድቃን ገብረትንሳኤ ሰሞኑን እንዳሉት ትህነግ የቀሩት ሁለት ምርጫዎች ብቻ ናቸው፤ ለሰላም መገዛት ወይም መለቀም። የትህነግ መሪዎች ግን በፈጠሩት ጥምረት አማካይነት በአጭር ቀን አራት ኪሎ እንደሚገቡ በሚዲያዎቻቸው አማካይነት እያስታወቁ ነው።

ትህነግ ድርጅቱ በታሪኩ አይቶት በማያውቀው ደረጃ ከፍተኛ የውስጥ መረበሽ፣ መደናገጥና መከፋፈልና ሊገለጽ በማይችል ቀውስ ውስጥ መውደቁን አምልጦ አዲስ አበባ የገባ የታጣቂ ቡድን አባል ይገልጻል። ይህ ስሙን መግለጽ የማይፍለገው የሰራዊት አባል፣ በተለይም በከፍተኛ አመራሩ ዘንድ ያለው መተማመን መጥፋት ለሥርዓቱ መፈረካከስ ዋነኛ መንስኤ መሆኑን አስታውቋል።

ከጦርነት ድካምና ከኢኮኖሚ ቀውስ ማገገም ያልቻለው የትግራይ ሕዝብ፣ እንዲሁም የጦርነቱን መከራ የቀመሰው ታጣቂው ክንፍ፣ “ጦርነት ይብቃን” የሚል ግልጽና ጠንካራ ጥሪ እያቀረቡ እንደሚገኙ ከትግራይ የሚወጡ መረጃዎች ያስረዳሉ። ይህንን ከሕዝብና ከሠራዊቱ የሚመነጨውን የተቃውሞ ማዕበል መቋቋም የተሳነው ቡድኑ፣ የውስጥ አንድነቱን ጠብቆ መቀጠል የማይችልበት ደረጃ ስለደረሰ የሚወስዳቸው እርምጃዎች በሙሉ ግራ የተጋቡ እንደሆነ ከውስጡ የወጡ እየገለጹ ነው።

የትግራይ ሰላም ኃይሎች የፕሮፓጋንዳ ክፍል ለአዲስ ሪፖርተር እንዳለው የትህነግ ኃይል እየፈለሰ ነው። ወጣቱ በአየርና በይተብስ ባገኘው ሁሉ ትግራይን እየለቀቀ ሲሆን ሕዝብ ጦርነት እንደማይፈልግ በተደጋጋሚ ስላስታወቀ ትህነግ ብቻውን እንደቀረ ሊያውቅና ያለውን ብቻኛ አማራጭ መቀበል ግዴታው መሆኑን ሊያምን እንደሚገባው ይናገራሉ። መሸሺያ እንዲመቻችላቸው የጠየቁትን አስመልክቶ በአካባቢያቸው ወዳለ የሰላም ኃይሎች እንዲሸሹ ጠቁመዋል። እዚያ ከደረሱ በኋላ ወዴት እንደሚያመሩ አቅጣጫ እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

የኮምናድ ፖአስት ካውንስል አቋቁሞ ጄነኤራል ታደሰ ወረደን ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ በላያቸው ላይ ዶክተር ደብረጽዮንን የሾመው ትህነግ በበኩሉ ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ የመዋጋት ሞራል እንዳለውና ተወሰዱ የሚሏቸውን አካባቢዎች በሙሉ በኃይል የሚያስመልሱበት ጊዜ መቃረቡን እያስታውቁ ናቸው።

በለኤላም በኩል የሻዕቢያና የፋኖ ኃይሎች በብዛት ወደ ትግራይ እየገቡ በመሆኑ የተቀናጀ ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጅት እያጠናቀቁ መሆኑን የሚገልጹት ወገኖች። ትህነግ በአጭር ጊዜ ውስጥ መንግስት እንደሚገለብጥ በኩራት እየተናገሩ ነው።

ይህን የማይቀበሉት ወገኖች ደግሞ ትህነግ የፖለቲካና የወታደራዊ መዋቅር መላላት፣ ቡድኑን ወደ ማይቀረው የመውደቂያ አፋፍ እያፋጠነው እንደሚገኝ በእርግጠኛነት እየገለጹ ነው። “የአመራሩ ግትርነትና የቆየ የጦርነት አባዜም ለውድቀቱ ተጨማሪ ማገዶ ሆኖታል። ሕዝቡ ለፕሮፓጋንዳ ጥሪዎች ጀርባውን መስጠቱና የታጣቂው ኃይል አባላትም የቡድኑን ዓላማ ተጠራጥረው መሸሻቸው፣ ድርጅቱ ያለ አጋዥና ያለ ደጋፊ ብቻውን መቅረቱን ያረጋግጣል” ሲሉ ምክኛታቸውን ይዘረዝራሉ።

“በአሁኑ ሰዓት ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲመዘን፣ ትህነግ ከራሱ አባላትና ከሕዝቡ የሚሰነዘርበትን ተቃውሞ ማስተናገድ ተስኖት፣ እንደ ቆሰለ አውሬ እራሱን በራሱ እየበላ የሚገኝበትና የህልውናው ማብቂያ ምዕራፍ ላይ የደረሰበት ወቅት ላይ ስለሆነ በዙሪያው የተሰበሰቡ ራሳቸውን እንዲያድኑ በይፋ ጥሪ ሊደረግ ይገባል” የሚሉም አሉ።

የአመራርና የዓላማ አንድነት ማጣት

በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው የትህነግ ቡድን፣ ላለፉት ዓመታት ሲከተለው በነበረው የጥፋትና የትርምስ መንገድ ምክንያት እራሱ በለኮሰው እሳት ውስጥ እየተቃጠለ ይገኛል። ድርጅቱ በታሪኩ አይቶት በማያውቀው ደረጃ ከፍተኛ የውስጥ መረበሽ፣ መደናገጥና መከፋፈል ውስጥ የወደቀ ሲሆን፣ በተለይም በከፍተኛ አመራሩ ዘንድ ያለው መተማመን መጥፋት ለሥርዓቱ መፈረካከስ ዋነኛ መንስኤ ሆኗል። ከጦርነት ድካምና ከኢኮኖሚ ቀውስ የወጣው የትግራይ ሕዝብ፣ እንዲሁም የጦርነቱን መከራ የቀመሰው ታጣቂ ክንፍ፣ “ጦርነት ይብቃን” የሚል ግልጽና ጠንካራ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ። ይህንን ከሕዝብና ከሠራዊቱ የሚመነጨውን የተቃውሞ ማዕበል መቋቋም የተሳነው ቡድኑ፣ የውስጥ አንድነቱን ጠብቆ መቀጠል የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

የቡድኑ የፕሮፓጋንዳ መዋቅርና የሕዝብ ማሰባሰብ አቅም ሙሉ በሙሉ በመፈረካከሱ፣ ለጦርነት ቅስቀሳ የሚደረጉ ስብሰባዎች በታላቅ ውድቀት እየተጠናቀቁ ይገኛሉ። ለምሳሌ ያህል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመሰብሰብ በታቀደባቸው መድረኮች ላይ ከሃያ የማይበልጡ ሰዎች ብቻ መገኘታቸው፣ ድርጅቱ በሕዝቡ ዘንድ ያለውን ቅቡልነት ማጣቱን ያረጋግጣል። የፕሮፓጋንዳ ክንፉም ቢሆን ወጥ የሆነ መልዕክት ማስተላለፍ አቅቶት፣ በአንድ በኩል ጦርነት እንፈልጋለን እያለ ሲፎክር፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሰላም ፈላጊ መስሎ ለመታየት መሞከሩ በድርጅቱ ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ግራ መጋባት ያሳያል። ይህ የመልዕክት መምታትና የሕዝብ ተሳትፎ መላላት፣ ህወሓት በፖለቲካዊ መልኩ የመጨረሻ እስትንፋሱ ላይ መሆኑን አመላካች ነው።

የስደት ማዕበልና የታጣቂው መዋቅር መፍረስ

 በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል የሚታየው የወጣቶችና የታጣቂዎች ከፍተኛ የስደት ማዕበል የሕወሓትን ወታደራዊና ፖለቲካዊ መዋቅር ክፉኛ እየናጋው ይገኛል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶችና የድርጅቱ ታጣቂ አባላት ለዓመታት ሲጋቱት የነበረውን የጦርነት ፕሮፓጋንዳ ወደ ጎን በመተው፣ አጋጣሚዎችን ሁሉ በመጠቀም ክልሉን እየለቀቁ መውጣታቸው የቡድኑን የሰው ኃይል ምንጭ እያደረቀው ነው። ይህ ፍልሰት በዋናነት ወደ አዲስ አበባና በአጎራባች የአፋር ክልል በኩል ወደ ጅቡቲ የሚደረግ ሲሆን፣ ይህም የሚያሳየው ተተኪው ትውልድ ለቡድኑ ጥፋት መሣሪያ ከመሆን ይልቅ የራሱን ሕይወት ለማዳንና የተሻለ አማራጭ ለመፈለግ መወሰኑን ነው።

ይህ የስደት ክስተት ድርጅቱን ከሰው ኃይል እጥረት ባለፈ በከፍተኛ የሞራል ስብራት ውስጥ ጥሎታል። ለጦርነት የተመለመሉና የሰለጠኑ ኃይሎች መዋቅሩን ጥለው መጥፋታቸው፣ በደረጃ በደረጃ ሲገነባ የነበረው ወታደራዊ ሰንሰለት መበጠሱን ያረጋግጣል። ታጣቂው ክፍል ለቡድኑ አመራሮች ያለው እምነት መሟጠጡና ለተጨማሪ ግጭት የሚቀርበውን ጥሪ በነቅተህ ተጠበቅ መንፈስ አለመቀበሉ፣ ሕወሓት በክልሉ ውስጥ ያለውን የኃይል ሚዛንና የማስገደድ አቅም በእጅጉ እንዲላላ አድርጎታል። ይህ የሞራል መውደቅ ደግሞ ቡድኑን ለውጭ ጥቃት ብቻ ሳይሆን ለውስጥ መፈራረስ ይበልጥ ተጋላጭ አድርጎታል።

በተያያዘም፣ የታጣቂው አመራሮች አንድ በአንድ ቡድኑን እየከዱ ወደ ሰላም ኃይሉ መቀላቀላቸው ለሕወሓት የመጨረሻው የውድቀት አዋጅ እየሆነ ነው። እነዚህ አመራሮች ለረጅም ጊዜ የቡድኑን ፖሊሲ ሲያስፈጽሙ የቆዩ ቢሆኑም፣ አሁን ላይ ግን ጥቂት የቡድኑ ፅንፈኛ ግለሰቦች ለግል ዘረፋና ለብዝበዛ ሲሉ የሚቀሰቅሱት ጦርነት ትርጉም አልባ መሆኑን ተረድተዋል። የጦር አመራሩ መከፋፈልና ወደ ሰላማዊ መንገድ መሸሽ፣ ድርጅቱ ውስጥ ያለውን የትዕዛዝ ሰንሰለት ከመበጣጠሱም በላይ፣ ቀሪዎቹ ታጣቂዎችም በነዚህ አመራሮች ፈር ቀዳጅነት ተነሳስተው መዋቅሩን እንዲለቁ እያበረታታ ይገኛል።

ይህ አጠቃላይ የመዋቅር መፍረስ አንድምታው ሲታይ፣ ሕወሓት ከመላው የኢትዮጵያና የትግራይ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ለመውረድ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱን ያመለክታል። ድርጅቱ ሕዝባዊ መሠረትና ወታደራዊ ታማኝነት ካጣ፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ በሥልጣን ላይ ሊቆይ የሚችልበት ዕድል ጠባብ ነው። ይህ የስደትና የክህደት ማዕበል የሚያረጋግጠው፣ ቡድኑ እንደ ቆሰለ ጅብ እራሱን በራሱ እየበላ መሆኑንና በአጭር ጊዜ ውስጥ በታሪክ መዝገብ ላይ ብቻ ተጠቅሶ የሚቀርበት የታሪክ አጋጣሚ መቃረቡን ነው።

የውጭ ኃይሎች ተጽዕኖና የመጨረሻው ምርጫ

በአሁኑ ሰዓት ፅንፈኛው የትህነግ ቡድን በሁለት አውዳሚ እሳቶች መካከል ተወጥሮ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህም ለህልውናው ትልቅ ስጋት ሆኖበታል። በአንድ በኩል ከላይ እንደተጠቀሰው የውስጥ መፈረካከስ፣ የህዝብ ተቃውሞና የታጣቂው ክንፍ መበታተን ክፉኛ እያሰቃየው ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ከውጭ ኃይሎች በተለይም ከሻቢያና ከግብፅ የሚሰጠው ቀጥተኛ ትዕዛዝና ግፊት ቡድኑን ወደ ከፍተኛ መወዛገብ ውስጥ ጥሎታል። እነዚህ የውጭ ኃይሎች ቡድኑን እንደ ፖለቲካዊና ወታደራዊ መጠቀሚያ መሣሪያ በማድረግ፣ ለራሳቸው ቀጣናዊ ፍላጎት ሲሉ ወደማይፈልገውና ወደማይወጣው አዲስ የጥፋት ጦርነት እየገፉት ይገኛሉ።

ይህ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትና ግፊት የቡድኑን የመጥፋት ሂደት ይበልጥ እያፋጠነው መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ሆኗል። ህወሓት በገዛ ፈቃዱ ሳይሆን በሌሎች አዝዣለሁ ባዮች ፍላጎት ላይ ተመስርቶ የሚወስዳቸው እርምጃዎች፣ በክልሉ ውስጥ ያለውን ቀሪ ደጋፊና ታጣቂ ይበልጥ እያራቁት ነው። የውጭ ኃይሎች ድጋፍና ግፊት ዘላቂ ሰላምን ሳይሆን ለተጨማሪ ደም መፋሰስና ውድመት የሚዳርግ መሆኑን የተገነዘበው የትግራይ ህዝብ፣ ድርጅቱ ለባዕዳን አጀንዳ ማስፈጸሚያነት መመረጡን በጽኑ እየተቃወመው ይገኛል። ይህም ቡድኑን በታሪክ ፊት ይበልጥ ተጠያቂና ብቸኛ እያደረገው ነው።

በአሁኑ ሰዓት የትህነግአመራሮች ፊት የተደቀነው ምርጫ እጅግ ግልጽና ጠባብ ሆኗል። አንደኛውና የተሻለው አማራጭ፣ እንደ አቦይ ስብሃት ነጋ ለፌዴራል መንግስት ሰላማዊ በሆነ መንገድ እጅ በመስጠትና በህግ ጥላ ስር በመጠለል በሕይወት የመኖር ዕድልን መጠቀም ነው። ይህ ምርጫ ለራሳቸውም ሆነ በጦርነት ለዛለው የትግራይ ህዝብ የሰላም አየርን የሚፈቅድና የክልሉን መልሶ ግንባታ የሚያፋጥን ብቸኛው ምክንያታዊ መንገድ ነው። ከዚህ ውጭ ያለው መንገድ ግን ወደ ከፋ ጥፋትና ወደማይቀረው ሞት የሚመራ መሆኑ አያጠራጥርም።

በተቃራኒው፣ አሁን በጀመሩት እብደትና በውጭ ኃይሎች ግፊት ወደ ጦርነቱ ዳግም ገፍተው ለመግባት የሚሞክሩ ከሆነ፣ ውጤቱ እንደ ቀድሞ ጓዶቻቸው በድንጋይ ስር ወይም በዋሻ ውስጥ የመጨረሻውን እስትንፋስ ተንፍሶ መሰናበት ብቻ ይሆናል። ታሪክ የዚህን ቡድን መደምደሚያ ለመጻፍ ጥቂት ጊዜያት ብቻ የቀሩት ይመስላል፤ ምክንያቱም የህዝብ ድጋፍ የሌለውና በባዕዳን ትዕዛዝ የሚንቀሳቀስ ኃይል እድሜው አጭር መሆኑን ያለፉት የታሪክ ሂደቶች በተደጋጋሚ አረጋግጠዋል። ምርጫው አሁንም በአመራሮቹ እጅ ቢሆንም፣ ጊዜው ግን በፍጥነት እያለቀባቸው ይገኛል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

The Blind Spot in the “No More War” Rhetoric: Ignoring TPLF’s Sabotage

This one-sidedness reflects a deeper issue: Jawar's analysis consistently...

ከድጡ ወደ ማጡ – የሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የጦርነት ስጋት እና ተጠባቂው የቀጣናው መናወጥ

አዲስ ሪፖርተር - ዓለም አቀፉ ክራይሲስ ግሩፕ ሰሞኑን ባወጣው...

በሱዳን ጦርነት ብሄራዊ ጥቅሙን አሳልፎ እየሰጠ ያለው ደናቁርት “ኢትዮጵያዊ ሊሕቅ” እና ተጨባጩ እውነታ

እነ ጀዋር መሃመድ እና መሰሎቹ የድንቁርና ጌቶች  መሃመድ ዳጋሎ...