የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለትራምፕ ፍላጎት የማንንበረከከው “ኢራናውያን” ስለሆንን ነው አሉ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ በቅርቡ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራን ለምን ለፍላጎታቸው ተገዥ እንዳልሆነች እንደጠየቋቸው መናገራቸውን ተከትሎ በሰጡት ምላሽ “እኛ ኢራናዊ ስለሆንን” ነው ሲሉ ምላሽ ሰጡ።

አራጋቺ እሁድ ዕለት ኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ዊትኮፍ “ኢራን ለዋሺንግተን ፍላጎቶች ለምን እንዳልተገዛች ተጠይቀው ነበር። “ምክንያቱም ኢራናውያን ስለሆንን ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

የአሜሪካ ዋነኛ ተደራዳሪ የሆኑት ልዩ መልዕክተኛው ስቲፍቭ ዊትኮፍ ከፎክስ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልስ ወቅት ትራምፕ ኢራን ይህ ሁሉ ጫና እየተደረገባት አልበገርም ለምን እንዳለች ማወቅ እንደሚፈልጉ ገልጸው ነበር። ልዩ መልዕክተኛው አሜሪካ በቀጣናው የጦር ጄት ተሸካሚ መርከቧን ብታሰማራም “እጇን ያልሰጠችው” ለምን እንደሆነ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ማወቅ ይፈልጋሉ ብለዋል።

“ዛሬ ጠዋት ፕሬዚዳንቱ ጠይቀውኛል። ተስፋ ቆርጠዋል ማለት አልፈልግም። ምክንያቱም ብዙ አማራጮች እንዳሏቸው ያውቃሉ። ነገር ግን ለምን እጃቸውን እንዳልሰጡ፤ እንዳልተስማሙ ማወቅ ይፈልጋሉ።” ዊትኮፍ እንደሚሉት የትራምፕ አስተዳደር ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንደማትታጠቅ እና ያንን ለማረጋገጥ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንድትዘረዝር ይፈልጋል።

ይህ አስተያየት የመጣው ሁለቱ አገራት ለሦስተኛ ዙር ውይይት ከመገናኘታቸው በፊት ነው። ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ በኦማን አደራዳሪነት ሁለቱ አገራት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ተገናኝተው ተወያይተዋል። አሜሪካ ጦር ጫኝ መርከቦቿን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ማንቀሳቀሷን ተከትሎ ጥቃቶቸ ሊፈጸሙ እንደሚችሉ ተገልጾ ነበር። እሁድ ዕለት በተለያዩ የአገሪቱ ዩኒቨርስቲዎቸ የሚማሩ ኢራናውያን ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተው ነበር።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

Egypt’s Red Sea Signal: Opening the Door to a Historic Nile Agreement with Ethiopia

"sources like The National indicating Egypt's conditional openness to...

አብን በሁመራ፣ አዲረመጥ፣ ኮረም ኦፍላ፣ ጠለምት ራያና አላማጣ ሕዝቡ ለክልልም ምርጫም መሳተፍ አለበት አለ

አዲስ ሪፖርተር - "ህዝባችን ለክልሉ ምክርቤት ጭምር ምርጫ መካሄድ...

“ለዓመታት የፖለቲካ መብታቸው ተገፎ ለኖሩ ዜጎች የዲሞክራሲ ጭላንጭል የፈነጠቀ ታሪካዊ እርምጃ” ወልቃይት

አዲስ ሪፖርተር - የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን ኮሚቴ...

“ለአራተኛ ጊዜ ተወረናል” ከወሎ ራያ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ከሚቴ የተሰጠ መግለጫ

አዲስ ሪፖርተር - "መንግሥትም የህዝቡን የማንነት እና የራስ አስተዳደር...