“ሕጋዊና ሕዝባዊ መንግሥት ለማፅናት ብቸኛው መንገድ ምርጫ ነው” ብልጽግና

Date:

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ – የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ከየካቲት 12 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ለተከታታይ ሦስት ቀናት በመዲናችን አዲስ አበባ ተካሂዶ በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው ሰፊ ዝግጅት እየተደረገለት የቆየውና በአሁኑ ጊዜ ወደ ዋና እንቅስቃሴው እየገባ ያለውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ዋነኛ አጀንዳው አድርጎ መክሯል፡፡

ለዚህም በቀደመው 6ኛ ጠቅላላ ምርጫ ላይ ፓርቲያችን ለሕዝብ የገባውን ቃል እና ስኬቶቹን በመንደርደሪያነት በመቃኘት የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ አጠቃላይ ዝግጅት በጥልቀት ገምግሟል፡፡ ብልፅግና ፓርቲ ከሀገራዊ ለውጡ መባቻ ጀምሮ ለሕዝብ ከገባው ቃል አንዱና ዋነኛው የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታችን ላይ ይስተዋል የነበረውን ስብራት መጠገን ነበር፡፡

ይህ አጀንዳ ከቃል እስከ ተግባር፤ ከተግባር እስከ ልምምድ የሚዘልቅ ረጅም ጉዞን የሚያጠቃልል ሲሆን፣ ጉዞውን በአስተማማኝ ውጥን ለመጀመር በቁርጠኝነትና መስዋዕትነት የታጀቡ አያሌ የተግባር ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ከገነቡ የተግባር ሥራዎች መካከል በተቃርኖ የቆዩ የፖለቲካ ኃይሎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሰላማዊ ትግል እንዲያደርጉ የማድረግ፣ የህግ ማዕቀፎችን የማሻሻል፣ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን የማጠናከር፣ የዴሞክራሲ ባህል የማጎልበትና በመደመር ዕሳቤ የመንግሥት ኃላፊነቶችን በፍትሃዊነት የማጋራት ተጨባጭና አዳዲስ የፖለቲካ ባህሎችን መፍጠር ተችሏል፡፡

ብልፅግና ፓርቲ እነዚህ አዳዲስ ባህሎች እንዲጠናከሩና ተቋማዊ መሠረታቸው እንዲጸና ለማስቻል 7ኛ ጠቅላላ ምርጫውን እንደ መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም ካለፈው ዓመት ጀምሮ አያሌ የውስጠ ፓርቲ እና የመንግሥት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

በዚህ መሠረት መንትያ ግቦች የተቀመጡ ሲሆን ÷ አንደኛውና ቀዳሚው ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሀዊ፣ አሳታፊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የማድረግ መንግሥታዊ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት ነው፤ ሁለተኛው ግብ ደግሞ ፓርቲው በጠንካራ ተፎካካሪነት በመሳተፍ አሸናፊ ሆኖ መውጣት ነው፡፡ የመንትያ ግቦቹ የእስካሁን አፈጻጸም በግምገማ የታየ ሲሆን ግቦቹ በተያዘላቸው የስኬት ሀዲድ ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡

ይህ ስኬት በየደረጃው በተሰራ ሥራ ማለትም በውስጠ ፓርቲ፣ በመንግሥታዊ ተቋማት ትብብር፣ በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅንጅት፣ በባለድርሻ አካላት አስተዋጽኦ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በሕዝብ የነቃ ተሳትፎ የመጣ ውጤት መሆኑም በተመሳሳይ ተገምግሟል፡፡ ይህም የእስካሁኑ ስኬት ቀጣይና የማይቀለበስ እንዲሆን አይነተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ነጠላ ትርክት ያነገቡ እንዲሁም ምርጫው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን እንጂ የእነሱን ጊዜያዊ ጥቅም ለመጠበቅ ቦታ የሌለው መሆኑን የተረዱ የቅርብና የሩቅ ቡድኖች ምርጫውን ለማስተጓጎል ከመሞከር አልቦዘኑም፡፡

ይህም ቢሆን ሊያጋጥሙ ከሚችሉ እክሎች አንዱ መሆኑ ከመጀመሪያው ጀምሮ የተተነበየ ነበር፤የእነዚህ ቡድኖችን ምኞት ለማክሸፍም በቂ ሥራ እየተሰራ ቆይቷል፡፡ በቀጣይነትም ምርጫው በተቀመጠለት ጊዜ እና የተያዘለትን ግብ በማሳካት እንዲጠናቀቅ ለአንዳፍታም ቢሆን ሳንዘናጋ ሥራችንን የምንሰራ ይሆናል፡፡

ሕጋዊና ሕዝባዊ መንግሥት የማጽናት ሒደት ከምርጫ ውጭ በሚደረጉ ማንኛውም እንቅስቃሴዎች በፍጹም የማይሳካ ብቻ ሳይሆን ለአንዴም የማይደናቀፍ መሆኑ ግልፅ መሆን አለበት፡፡ ለዚህም ፓርቲያችን በህሊና የመጥራት እና በተቋማት የመብቃት ሥራዎቹን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ህዝባችን እና በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትም ይህንን አጠናክረው እንዲቀጥሉም አስፈላጊ የቅንጅት ሥራዎች ይሰራሉ፡፡

እያንዳንዱ ዜጋም ጠቅላላ ምርጫው የዴሞክራሲ ሥርዓት የሚገነባበት እና ሕጋዊና ህዝባዊ መንግሥት የሚጸናበት ብቸኛውና ሁነኛ ብሔራዊ ፕሮጀክት መሆኑን በመረዳት ለዴሞክራሲያዊነቱ፣ አሳታፊነቱ፣ ፍትሀዊነቱ፣ ሰላማዊነቱ እና ለአጠቃላይ ስኬቱ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ብልፅግና ፓርቲ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

Egypt’s Red Sea Signal: Opening the Door to a Historic Nile Agreement with Ethiopia

"sources like The National indicating Egypt's conditional openness to...

አብን በሁመራ፣ አዲረመጥ፣ ኮረም ኦፍላ፣ ጠለምት ራያና አላማጣ ሕዝቡ ለክልልም ምርጫም መሳተፍ አለበት አለ

አዲስ ሪፖርተር - "ህዝባችን ለክልሉ ምክርቤት ጭምር ምርጫ መካሄድ...

“ለዓመታት የፖለቲካ መብታቸው ተገፎ ለኖሩ ዜጎች የዲሞክራሲ ጭላንጭል የፈነጠቀ ታሪካዊ እርምጃ” ወልቃይት

አዲስ ሪፖርተር - የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን ኮሚቴ...

“ለአራተኛ ጊዜ ተወረናል” ከወሎ ራያ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ከሚቴ የተሰጠ መግለጫ

አዲስ ሪፖርተር - "መንግሥትም የህዝቡን የማንነት እና የራስ አስተዳደር...