የሁመራ፣ የጸገዴ፣ የወልቃይት፣ የጠለምትና የራያ አላማጣ ምርጫ ከልሎች ከትግራይ ውጭ ሆኑ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሁመራ፣ የጸገዴ፣ የወልቃይት፣ የጠለምትና የራያ አላማጣ ምርጫ ከልሎች ከትግራይ ውጭ መሆናቸውን አስታወቀ። የወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ውሳኔውን አድንቋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ውሳኔውን እንደማይቀበለው አስታውቋል።

“በአማራና በትግራይ ክልላዊ መንግሥታት አከራካሪ የሆኑት ምርጫ ክልሎችን በተመለከተ የተሰጠንን ውሳኔ ስለማሳወቅ” በሚል ቦርዱ ይፋ ያደረገው ውስኔ ስማቸው በተዘረዘረው አካባቢዎች ላይ ይገናል የሚሉና “ማንነታችንን በኃይል ተነጥቀናል” የሚሉ ወገኖች ለላፉት ሶስት አስርት ዓመታት በላይ ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ይፋ ባደረገው መግለጫው ላይ ቦርድ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳን በተመለከተው ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም. የምርጫ ክልሎችና የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ አስታውሷል።

ይህንኑ ቦርዱ ያወጣውን የምርጫ ክልሎችና ጣቢያዎች ዝርዝር ተከትሎ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም. የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቁጥር ፈደም/አፈ/5/13138 ለቦርዱ በጻፈው ደብዳቤ በትግራይ እና በአማራ ክልላዊ መንግሥታት መካከል አከራካሪ ሆነው የቆዩት የአምስት ምርጫ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄው እስኪመራ ድረስ የሁመራ፣ የጸገዴ፣ የወልቃይት፣ የጠለምትና የራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች በትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውጪ ሆነው ለብቻቸው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ ምክር ቤቱ መወሰኑን ለቦርዱ እንዳሳወቀው አመልክቷል።

ይህ ብቻ ሳይሆን የክልል ምክር ቤት ምርጫው በአከባቢዎቹ ላይ የተነሳው የይገባኛል ውዝግብ በሕገ-መንግሥታዊ ውሳኔ ሲፈታ አመቺ ጊዜ ተመርጦ ወደፊት እንዲካሄድ መወሰኑንም እንዲሁ ምክር ቤቱ ለቦርዱ በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተላከለትን ደብዳቤ ያጣቀሰው ምርጫ ቦርድ፣ “ቦርዱ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከላይ በተጠቀሰው አግባብ ለመፈጸም የሚያስችለውን አሠራርና ሥርዓት በመጠበቅ ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑን ያስታውቃል” ሲል መጨረሻ ላይ የደረሰበትን ውሳኔ ይፋ አድርጓል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ውሳኔው አደገኛ መሆኑን ጠቅሶ እርምት እንዲደረግ በጥብቅ እንደሚያሳስብ አመልክቷል። “የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ጭቁን ህዝቦች ጋር በመሆን ሁሉንም ህዝቦች በእኩልነት የሚያገለግል ህገ መንግስትና አዲስ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት ችሏል” በማለት ወደኋላ ተመልሶ ያስታወሰው መግለጫው፣

መግለጫው አክሎም ውሳኔውን “በሕዝቦች መራራ ትግል የተመሰረተን ህገ-መንግስትና ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን በመጣስ የተፈፀመውና እየተፈፀመ ተግባር ነው” ብሎታል። መግለጫው “ጭቁን ሕዝቦች” ሲል ትግሬ ያልሆኑ የሁመራ፣ የጸገዴ፣ የወልቃይት፣ የጠለምትና የራያ አላማጣ ህዝብን እንደሚያካትትና እንደማያካትት ግልጽ አላደረገም።

ትህነግ ህገ መንግስቱን እና የፕሪቶሪያን ስምምነትን በመጣስ የትግራይን ህገ-መንግስታዊ ወሰን አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ መተላለፉን አመልክቶ “የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ከትግራይ ህዝብ ድምጽ ውጪ የተወሰነ በመሆኑ የምክር ቤቱን ውሳኔ በፅኑ በማውገዝ፣ የዚህ አደገኛ ውሳኔ ሰርኩላር እንዲታረሙና እና በድጋሚ እንዲታይ በጥብቅ እናሳስባለን” ብሏል።

ይህንኑ ተከትሎ የወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኃይሉ፣ በውሳኔው መደሰታቸውን አመልክተው፣ ውሳኔው በማንነታቸውና በወሰናቸው ላይ ጥቃት የደረሰባቸውና የፍትህ ወዳዶች ትግል መሆኑን አስታወቀዋል። አክለውም ተግብራዊነቱን እንደሚናፍቁ ለአዲስ ሪፖርተር ተናግረዋል። ላለፉት ሰባት ዓመታት ወኪል የሌለው ሕዝብ በበጀትና በተለያዩ ጉዳዮች ሲጎዳ መኖሩን አስታውሰው፣ ሕዝብ የመምረጥ መብቱ እንዲከበርለት መደረጉን ሊለመድ የሚገባ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ እንደሆነ ተናግረዋል። አክለውም ትህነግ ውሳኔውን እንደማይቀበለው እርግጠኛ መሆናቸውን ጠቅሰው መንግስት ለተግባራዊነቱ እንዲሰራበት ጠይቀዋል።

“ልክ እንደ ትግራይ ሕዝብ ሁሉ ሌልችም ፍላጎት አላቸው” ያሉት አቶ ኃይሉ ሕዝብ በነጻ የሚፈቅደውን እንዲወስን ሊፈቀድለት እንደሚገባ አስታውቀው፣ ካልዘገየ በስተቀር ውሳኔው የሚጠብቅና ፍትሃዊ እንደሆነ ለአዲስ ሪፖርተር ተናግረዋል።

ለወልቃይት ጠገዴ ዞን አስተዳደር በተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ብናደርግም ምላሽ አላገኘንም። የጠለምት ገጠር ቀበሌ መዋቅር አካላ የሆኑ “ውሳኔው ፍትሃዊና የሚተብቀ ነው። ሕዝብ የሚፈልገውን እንዲመርጥ ሊፈቀድለት ይገባል። ቀደም ባሉት ዓመታት ሕዝብ ጥያቄ ሲያቀርብ በሃይል ለመመለስ ባይሞከር ኖሮ እዚህ አይደረስም ነበር” ብለዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

Egypt’s Red Sea Signal: Opening the Door to a Historic Nile Agreement with Ethiopia

"sources like The National indicating Egypt's conditional openness to...

አብን በሁመራ፣ አዲረመጥ፣ ኮረም ኦፍላ፣ ጠለምት ራያና አላማጣ ሕዝቡ ለክልልም ምርጫም መሳተፍ አለበት አለ

አዲስ ሪፖርተር - "ህዝባችን ለክልሉ ምክርቤት ጭምር ምርጫ መካሄድ...

“ለዓመታት የፖለቲካ መብታቸው ተገፎ ለኖሩ ዜጎች የዲሞክራሲ ጭላንጭል የፈነጠቀ ታሪካዊ እርምጃ” ወልቃይት

አዲስ ሪፖርተር - የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን ኮሚቴ...

“ለአራተኛ ጊዜ ተወረናል” ከወሎ ራያ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ከሚቴ የተሰጠ መግለጫ

አዲስ ሪፖርተር - "መንግሥትም የህዝቡን የማንነት እና የራስ አስተዳደር...