አሜሪካ የጄነራል አልቡርሃን  መንግስትን በሽብርተኝነት ፈረጀች፤ ውሳኔ ወዳጅ ለሆኑት ለኤርትራና፣ለትህነግ መርዶ ሆኗል

Date:

ጃዋር መሐመድና አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአልቡርሃን ደጋፊ ሆነው ኢትዮጵያን እንደሚከሱ ይታወቃል። ይህ የአሜሪካ ውሳኔ ለእነዚህ የፓርቲ አመራሮች፣ ለኤርትራ፣ በሱዳን ወታደር ላሰማራውና የኢራንን መሳሪያ ታጠኩ ለሚለው ትህነግ እንዲሁም እነዚህን ቡድኖች በገንዘብና በዓይነት ለሚደግፉ የአሜሪካን ውሳኔ ምን ይዞ ይመጣል? የሚለው ጉዳይ እጅግ መነጋገሪያ ሆኗል።  

አዲስ ሪፓርተር- የአሜሪካ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በሱዳን ከጀነራል አልቡርሃን ጋር የሚንቀሳቀሰውን የሙስሊም ወንድማማቾች ቡድን (Muslim Brotherhood) በሽብርተኝነት መዝገብ ውስጥ በማካተት በአሸባሪነት መፈረጁ ተገለፀ። የሱዳን መንግስት ደጋፊዎችንና አብረው የሚሰሩ አገራት ኤርትራን ጨምሮ ውሳኔው መርዶ ሆኖባቸዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በቲውተር ገፃቸው በአጋሩት መረጃ ቡድኑን “ዓለም አቀፍ አሸባሪ” ሲሉ መፈረጃቸው፣ ዋሽንግተን በሱዳን እየተካሄደ ባለው የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ያላትን አቋም በግልጽ የሚያሳይ ሆኗል። ይህ ውሳኔ ከኢኮኖሚ ማዕቀብ ባለፈ፣ ለቡድኑ የሚደረግ ማንኛውንም ዓይነት ቁሳዊ ድጋፍ በሕግ የሚያስቀጣ በመሆኑ በሱዳን የውስጥ በሚካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር የፓለቲካ ተንታኞች እየገለፁ ይገኛሉ።

በዚህ የአሜሪካን ውሳኔ መሰረት ከጀነራል አልቡርሃን ጋር ማበር፣ አብሮ መስራት፣ መሳሪያ መቀባበልም ሆነ ወታደር መቀያየር ሽብርን እንደመደገፍ ስለሚቆጠር በዚህ መልኩ የሚገናኙ አገራት ጣጣ ውስጥ እንደሚገቡ የዓለም ተሞክሮ ያሳያል። ተጠያቂነቱ በእኩል ደረጃ እንደሆነም ይታወቃል። በዚህ መመዘኛ ኤርትራ ብቻ ሳትሆን ጀነራል አልቡርሃን መንግስት ደግፎ ወታደር ያሰማራው፣ በጀነራል አልቡርሃን በኩል የመሳሪያ ድጋፍ  የሚደረግለት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር/ ትህነግም ውሎ አድሮ አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚገባ ጉዳዩን የሚከታተሉ እያስታወቁ ነው።

ዋሽንግተን ይህን ውሳኔ ለመወሰን እንደ ዋነኛ ምክንያት ያቀረበችው፣ “የሱዳኑ ሙስሊም ወንድማማቾች ቡድን ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) ጋር ጥብቅ ግንኙነት አለው” በሚል ነው። አሜሪካ ቡድኑ በሱዳን ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያልተገደበ ጥቃት በመፈጸም እና ግጭቶችን በማባባስ የራሱን ጽንፈኛ ርዕዮተ ዓለም ለማስፋፋት እየሰራ ነው ስትል ትከሳለች። ይህ የኢራን እጅ በሱዳን ጉዳይ ውስጥ መኖሩን የሚጠቁመው የአሜሪካ አቋም፣ በቀጠናው ውስጥ ያለውን የኃይል ሚዛንና ፍጥጫ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል ተብሏል።

በሱዳን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ፣ በመደበኛው የሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሹ ሃይል (RSF) መካከል በሚካሄደው ጦርነት ውስጥ የሙስሊም ወንድማማቾች ታጣቂዎች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ አዲስ ሪፓርተር ከዚህ በፊት በስፋት ማስረጃ አጣቅሳ ሰፊ ሃተታ ማቅረቧ የሚታወስ ነው።

የፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች (RSF) አመራሮች “እየተዋጋን ያለነው የሙስሊም ወንድማማቾችን ነው” በሚል ለሚያቀርቡት መከራከሪያ፣ የአሜሪካው ፍረጃ እንደ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት ይቆጠራል። ይህ ደግሞ በሱዳን ጦር ውስጥ የሚገኙ የቡድኑ ደጋፊዎች ላይ ዓለም አቀፍ ጫና እንዲበረታ የሚያደርግ ነው።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) የአሜሪካን ውሳኔ በአዎንታዊነት መቀበሏ ሌላኛው ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ሆኖ ብቅ ብሏል። ኤምሬትስ የሙስሊም ወንድማማቾች ቡድንን በቀጣናው ውስጥ እንደ ስጋት ትመለከታለች። የተባበሩት ኤምሬትስ የአሜሪካ እርምጃ የቡድኑን የገቢ እንቅስቃሴ ለመግታት ይረዳል የሚል እምነት አላት። ይህ የዋሽንግተን እና የአቡዳቢ ተመሳሳይ አቋም፣ በሱዳን ጉዳይ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ የውጭ ኃይሎች በአንድ ጎራ መሰለፋቸውን የሚያመላክት ነው።

በሌላ በኩል፣ እ.ኤ.አ. በ1928 በሀሰን አል-በና የተመሰረተው የሙስሊም ወንድማማቾች ቡድን እና መሰል ቅርንጫፎቹ፣ ይህን ፍረጃ  በፅኑ እየተቃወሙ ይገኛሉ። ቡድኑ በተለያዩ የአረብ ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ማህበራዊ ድርጅቶች ያሉት ሲሆን፣ “ዓላማችን በሰላማዊ መንገድ በፖለቲካ መሳተፍ ነው” የሚል መከራከሪያ ያቀርባል። ሆኖም በሱዳን ያለው ተጨባጭ ሁኔታ እና የታጣቂዎቹ እንቅስቃሴ ይህን የሰላማዊነት መከራከሪያ ከአሜሪካ የደህንነት ተቋማት እይታ ውጭ እንዲሆን አድርጎታል።

ይህ የአሜሪካ እርምጃ በሱዳን ብቻ የተገደበ ሳይሆን፣ በሊባኖስና በዮርዳኖስ የሚገኙ የቡድኑን አጋሮችም ያካተተ መሆኑ የትራምፕ አስተዳደር ሰፋ ያለ “የማፅዳት” ስራ እየሰራ መሆኑን ያሳያል። በምዕራባውያን ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ቀኝ ዘመም አክቲቪስቶች የሙስሊም ስደተኞችን ከዚህ ቡድን ጋር በማያያዝ የሚያቀርቡት ቅስቀሳ፣ አሁን በመንግሥት ደረጃ ህጋዊ እውቅና ማግኘቱ በስደት ላይ ባሉ ሙስሊም ማህበረሰቦች ላይም ማህበራዊ ጫና ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አለ።

ለሱዳን ሰላም ሂደት ይህ ፍረጃ የሁለትዮሽ ውጤት ሊኖረው ይችላል። በአንድ በኩል፣ ጽንፈኛ የተባሉ ኃይሎችን ከድርድር ገበታው በማግለል ሂደቱን ሊያጠራው ይችላል ተብሎ ቢታሰብም፤ በሌላ በኩል ደግሞ በጦር ሜዳው ላይ ያሉ ኃይሎች “የመኖርና ያለመኖር” ትግል ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ግጭቱን ይበልጥ ሊያባብሰው ይችላል። የአሜሪካ ውሳኔ ከፖለቲካዊ ፍረጃ ባለፈ በተግባር በሱዳን ምድር ያለውን ጦርነት እንዴት እንደሚቀይረው ወደፊት የሚታይ ይሆናል።

በአጠቃላይ የሱዳኑ ሙስሊም ወንድማማቾች በሽብርተኝነት መፈረጃቸው፣ የአሜሪካን “ትቅደም” ፖሊሲ በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ በግልጽ ያሳየ ክስተት ነው። ይህ ውሳኔ በሱዳን ጦርነት ውስጥ ለሚሳተፉ አካላት ግልጽ መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን፣ በቀጣይ ሳምንታት ቡድኑ “የውጭ ሽብርተኛ ድርጅት” (FTO) ዝርዝር ውስጥ ሲገባ የሚጣሉ ማዕቀቦች የቡድኑን የገንዘብ ምንጭና የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ክፉኛ እንደሚገቱት ይጠበቃል።

ጀዋር መሃመድ እና አንዳንድ የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች የኢትዮጵያ መንግስት የሱዳን ሙስሊም ወንድማማቾች ጋር በጥምረት የሚሰራውን ጀነራል አልቡርሃንን መደገፍ አለብን በማለት እየከሰሱና በምርጫ ክርክር ላይ በይፋ አቋማቸውን እየገለጹ ባለበት ወቅት ይህ ዜና መሰማቱ ሌላው ትልቁ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።

የኢትዮጵያን መንግስትን የጀነራል አልቡርሃንን ባለመደገፉ በተላላኪነት ሲፈርጁ የነበሩ ይህን ውሳኔ ተለትሎ ምን ስሜት እንዳላቸው በግልጽ ባይታወቅም፣ የአሜሪካን ውሳኔ አስደንጋጭ እንደሚሆንባቸው አዋጁን የሰሙ ገልጸዋል። 

ከዚህም በተጨማሪ ትህነግ ከአልቡርሃን ጋር በመስራት የኢራንን ፀረ ድሮን መሳሪያ ሊያስታጥቋት እንደቻሉ ምልክቶች ይታያሉ። ብርጋዴር ጄኔራል ምግበይ ከትናንት በስቲያ ስሪቱንና አገሩን አይናገሩ እንጂ ድሮን፣ ጸር ድሮን፣ ጸረ ታንክና መሰል ስትራቴጂክ መሳሪያ መታጠቃቸውን በድምጽ ወያኔ መናገራቸው አይዘነጋም።

ተገኘ የተባለው መሳሪያ የሚጋነንና ብዙም የሚነገርለት ባይሆንም፣ ምንጩን የሚያውቁ ትህነግ በተዘዋዋሪ ከኢራን ጋር እየሰራች እንደሆነ ማሳያ እንደሆነ አመልክተዋል። በተለይም ከኤርትራ ጋር ግንባር በመፍጠር የሚደረገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ አሜሪካ በቀይ ባህር ለጀመረችው ኦፕሬሽን እንደ እንቅፋት የተወሰደና ኤርትራ ከኢራን ጋር በመሆን እየፈጠረችው ያለው ችግር እንደሆነ በአሜሪካ ዘንድ አቋም መያዙ ቀደም ሲል መዘገቡ የሚታወስ ነው።

ከላይ ያሉትን አሳቦች የዲፕሎማት ምንጮችን በመጥቀስ አስቀድመው ሲናገሩ የነበሩ እንደሚሉት በመሆኑም የኢትዮጵያ የፓለቲካ ሃይሎች የአሜሪካ ውሳኔ ምን አይነት አንድምታ ሊኖረው እንደሚችል ሊመረመሩ እንደሚገባ ጥቆማ ሰጥተዋል። በተለይም የውስጥ አካሄዱንና ሚስጢራዊ ስምምነቶችን ሳያሰሉ በገንዘብና በዓይነት ለነዚህ ተቋማት ድጋፍ የሚያደርጉ ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ መክረዋል።

ቀጠናዊ የኃይል አሰላለፍ ለውጥ

አሜሪካ የሱዳን ሙስሊም ወንድማማቾችን መፈረጇ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) በሱዳን ጉዳይ ላይ ያላትን አቋም ያጠናክራል። ኢትዮጵያ ደግሞ ከኤምሬትስ ጋር ያላት ግንኙነት ጠንካራ በመሆኑ፣ በሀገር ውስጥ ያሉ ከኢራን ወይም ከሙስሊም ወንድማማቾች ጋር ግንኙነት አላቸው የሚባሉ ኃይሎች (ትህነግን ጨምሮ) ሁለት ነበልባል እሳት መካከል የመውደቃቸው ጉዳይ አይቀሬ ነው። በአንድ በኩል የአሜሪካ ጫና፣ በሌላ በኩል ደግሞ የኤምሬትስ የደህንነት ፍላጎት እነዚህን ኃይሎች ከጨዋታ ውጭ ሊያደርጋቸው ይችላል። ይህን አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች፣ ጃዋርን ጨምሮ የተባበሩት ኢምሬትስን ዕለት ዕለት የሚዘልፉት ቡድኖች ልዩ ምክንያት እንዳላቸው አሜሪካ ገልጣዋላች ይላሉ።

አሜሪካ የሱዳን ሙስሊም ወንድማማቾችን ከኢራን ጋር ባላቸው ቁርኝት ሳቢያ በሽብርተኝነት መፈረጇ፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከጄነራል አል-ቡርሃን አስተዳደር እና ከኢራን የደህንነት መዋቅር ጋር ስትራቴጂካዊ ትብብር ላላቸው አካላት ከፍተኛ የፖለቲካና የደህንነት ስጋት ውስጥ እንደሚያስገባቸው የሚናገሩ፣ ቅድሚያ ጃዋርና የጃዋርን ሰንሰለት ያነሳሉ።

“በተለይም እንደ ጀዋር መሐመድ ያሉ ፖለቲከኞች የኢትዮጵያ መንግሥት ከሙስሊም ወንድማማቾች ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለውን የአል-ቡርሃን ስርአት መደገፍ አለበት” በሚል የሚያቀርቡት ምክረ ሀሳብ፣ አሁን ካለው የዋሽንግተን  ፖሊሲ አንጻር እነዚህን ግለሰቦችና ስብስቦች በአሜሪካ የክትትል ዝርዝር ውስጥ ሊያስገባቸው ይችላል። ዋሽንግተን ለቡድኑ የሚደረግን ማንኛውንም “ቁሳዊና ሞራላዊ ድጋፍ” በሕግ የምትቀጣ በመሆኑ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው ለዚህ ጎራ ጥበቃና የቆሙ ኃይሎች የዲፕሎማሲያዊ መገለል ብቻ ሳይሆን፣ የንብረት እገዳና የጉዞ ፍቃድ መነጠቅን ጨምሮ ከባድ ዓለም አቀፍ ማዕቀቦች ሊጣልባቸው ይችላል። ጃዋር ከአሜሪካ የተባረረበት ምክንያት በተለያዩ ምክንያቶች እንደሆነ ቢገልጽም እስካሁን በህግ በሚታወቅ የቀረበ ሪፖርት የለም። ይሁን እንጂ አሁን ባለበት ኒዘር ላንድ ብዙም እፎይታ እንደሌለው በቅርብ የሚከታተሉት ይናገራሉ።

በተጨማሪም ትህነግ ከአል-ቡርሃን መንግሥት ጋር በመተባበር የኢራንን የፀረ-ድሮን ቴክኖሎጂ ስለመታጠቁ መረጃዎች ስለሚያመለክቱ ጉዳዩን ከቀጠናዊ ትብብር ባለፈ የአሜሪካን ብሔራዊ ደህንነት በቀጥታ የሚጋፋ ስልታዊ ስጋት ያደርገዋል። ኢራን በምስራቅ አፍሪካ ያላትን ተጽዕኖ ለመገደብ የምትሰራው አሜሪካ፣ ይህን ወታደራዊ ትብብር እንደ “ሽብርተኝነትን መርዳት” (State Sponsorship of Terrorism) አድርጋ የመቁጠር እድሏ ሰፊ ነው። ይህም ትህነግን በዓለም አቀፍ ደረጃ ስጋት እንዲገጥመው ሊያደርግ ይችላል።

“በዚህ ውሳኔ መሰረት ከጀነራል አልቡርሃን ጋ በቅርበት የሚሰራው ትህነግ ከምዕራባውያን ጋር የነበረውን የቆየ ግንኙነት ወደ ጠላትነት ሊቀይረው ይችላል። የኢራን ወታደራዊ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ አማጽያን እጅ መግባቱ ዋሽንግተን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የምታደርገውን ጣልቃ ገብነት ይበልጥ ስለሚያጠነክረውና የምትከተለው “ደህንነት ተኮር” ፖሊሲ በመሆኑ ጠንካራ እርምጃ እንድትወስድ ይገፋፋታል” ሲሉ የአዲስ ሪፖርተር የዘወትር ተባባሪ የሶማሊ ላንድ ፖቲከኛ አስተያየት ሰጥተዋል።

የአሜሪካ ውሳኔ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ “የኢራን-ሱዳን-ሙስሊም ወንድማማቾች” ዘንግ ደጋፊ የሆኑ ኃይሎችን ክፉኛ የሚያዳክም የጂኦ-ፖለቲካዊ ለውጥ ነው። በሀገር ውስጥ ያሉ ተዋንያን ከአሜሪካ ጥቅም ጋር በቀጥታ የሚጋጭ የውጭ ግንኙነት መመስረታቸው፣ የትራምፕ አስተዳደር በቀጣናው የሚከተለውን “ጽንፈኝነትን የማጽዳት” ዘመቻ ወደ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይም እንዲዘልቅ በር ይከፍታል። ይህም በኢትዮጵያ መንግሥትና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል ያለውን ፍጥጫ ወደ ዓለም አቀፍ የሽብርተኝነት ትግል መድረክ በማሸጋገር፣ ከኢራንና ከሱዳን እስላማዊ ኃይሎች ጋር ንክኪ ያላቸው አካላት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፊት ተሰሚነት አጥተው እንዲገለሉና የሕልውና አደጋ እንዲጋረጥባቸው የሚያደርግ ግዙፍ አንድምታ አለው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካዊው የፖለቲካ ተንታኝ “ኢትዮጵያ የኤርትራን የባህር ዳርቻ ተቆጣጥራለች” ሲሉ መናገራቸው ሳዑዲ አረቢያ ለኢትዮጵያ “አብረን ቀይ ባህር ላይ እንስራ” ስትል አቀረበች ከተባለው ጥያቄ ጋር የሚገናኝ ሆኗል። በግጭቱ ቀጣና አካባቢ ባሉ አገራት የሚሰሩ ዲፕሎማት ለአዲስ ሪፖርተር እንዳሉት ሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ በቀይ ባህር ለማመላለስ ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ ለመስራት አሳብ አቅርባለች።

በሪል አሜሪካስ ቮይስ Real America’s Voice ቴሌቪዥን ጣቢያ የዋር ሩም ፕሮግራም ላይ ቀርበው ትንታኔ የሰጡት አሜሪካዊው የጂኦ-ፖለቲካ ተንታኝ እና ጸሃፊ ብራንደን ዌይከርት በመካከለኛው ምስራቅ የተነሳው ጦርነት አድማሱን አስፍቶ ወደ አፍሪካ ቀንድ መዛመቱን አመላክተዋል።

ብራንደን ዌይከርት በትንተናቸው የቀይ ባህርን አስመልክቶ አነጋጋሪ መረጃን ሰጥተዋል። በኢትዮጵያን፣ ኤርትራን መካከል ቀይ ባህርን አስመልክቶ ብዙ እየተባለ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ “ኢትዮጵያውያ በቀይ ባህር ዳርቻ የኦፕሬሽን ቁጥጥር ወስዳለች” ብለዋል። በሌላ አነጋገር ኢትዮጵያ ቀይ ባህር ላይ ጦሯን አስፍራ ቁጥጥር ጀምራለች ብለዋል።

እኚህ ተንታኝ አክለውም “ኢትዮጵያ የአሜሪካ ወይም የእስራኤል ጦር ኃይሎች” በማለት በቀይ ባህር ዳርቻ አደጋ ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን በመቆጣጠር ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል።

“የሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር ላይ ገና ሙሉ ጥቃት አልጀመሩም። የሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ማጓጓዣዎች ከሆርሙዝ ስትሬት ወደ ቀይ ባህር ወደቦች እየተቀየሩ ሲሆን ሁቲዎች ይህንኑ መስመር ሙሉ በሙሉ ለመዝጋት እየጠበቁ ነው” መሆኑን ተንታኙ አመልክተዋል። ይህም የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ወደ አዘርባጃንና ቤሩት ብቻ ሳይሆን ወደ አፍሪቃ ቀንድ ለማምራቱ አመልካች እንደሆነ አመልክተዋል።

የዓለም፣ በተለይም የቀይ ባህር ቀጣና በዚህ ውስጥ መኖሩ እየታወቀ ኢትዮጵያን “ተንኳሽ” በማለት የሚከሱና ለጄኔራል የጄነራል አልቡርሃን  ድጋፍ የሚሰጡትን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችንና፣ የግብጽና ኤርትራን አቋም በመያዝ በገሃድ ዘመቻ የጀመረውን ጃዋር መሐመድን አስተያየት ለማከል ያደርገነው ሙከራ አልተሳካም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ኦፐሬሽን ኢርቡ ሺኒጋ ፤ “የሰማዕታት ቃል ኪዳን” የጃዋር መሐመድ የህቡዕ ፕሮጀክት 

አዲስ ሪፖርተር - የስጋት ትንታኔ መስጠት እሰጣለሁ ባይ ነው።...

ኢትዮጵያ የUAE “ጉዳይ ፈጻሚ” (proxy)?!

የአፍሪካ ቀንድ የረዥም ጊዜ ቀጠናዊ ጥልፍልፎሽ (regional security complex)...

አስመራና መቀለ “ጽምዶ” የመንግስት ለመንግስት ግንኙነት ተብሎ በይፋ ሊታወጅ እየተመከረ ነው፤

አዲስ ሪፖርተር - በትህነግ የሰዓት አቆጣጠር የጦርነት ማስጀመሪያ ግብአቶች...

የኢሕአፓ የሃገር ክህደት ማቆሚያው የት ነው? ክህደት በቴሌቪዥን ክራባት ለብሶ አየነው

ክህደት ክራባት ለብሶ ቆሞ አየነው። ክህደት ጓሮ ለጓሮ ከሚርመጠመጥበት...