በአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና የዜግነት ሕግ (INA) በንዑስ አንቀጽ (iv) ከቁጥር (I) እስከ (VI) የተዘረዘሩት ተግባራት፣ ማንኛውም ግለሰብ ከፋኖ ወይም መሰል “Tier III” (ያልተፈረጁ) የትጥቅ ቡድኖች ጋር በሚኖረው ግንኙነት ሳቢያ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ እና ከአሜሪካ እንዲባረር የሚያደርጉ ግልጽ መስፈርቶች ናቸው። እነዚህም በቀጥታ በውጊያ መሳተፍን ብቻ ሳይሆን፤ የትጥቅ እንቅስቃሴ እንዲደረግ ማነሳሳትን፣ መቀስቀስን፣ መረጃ ማሰባሰብን፣ ለቡድኑ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችን ማድረግን (Fundraising)፣ አባላትን መመልመልን እና ማንኛውንም ዓይነት ቁሳቁሳዊ ድጋፍ (Material Support) መስጠትን ያካትታሉ። ሕጉ “ቁሳቁሳዊ ድጋፍ” የሚለውን በሰፊው ይተረጉመዋል፤ ይህም ማለት ለታጣቂዎች የሚሆን የገንዘብ መዋጮ ማድረግ፣ የመገናኛ መሣሪያዎችን መግዛት፣ ወይም በማኅበራዊ ሚዲያ የቡድኑን የጥፋት ተልዕኮ የሚያሳኩ የፕሮፓጋንዳ ስራዎችን መስራት በአሜሪካ መንግሥት ዘንድ እንደ ሽብር ድጋፍ ተቆጥሮ ለከባድ ቅጣት ይዳርጋል።
አዲስ ሪፓርተር፡- የአሜሪካ ኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ባለስልጣን (ICE) በይፋዊ የX እና ፌስቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መረጃ ሰለሞን ቦጋለ የተባለ ኢትዮጵያዊ በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በዘር ማጥፋት ቅስቀሳ ምክንያት ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ስለመባረሩ የሚገልጽ ነው። ግለሰቡ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ ራሱን ” የፋኖ አባል ” አድርጎ መግለጹ ተጠቅሷል። በዚሁ መረጃ ላይ አሜሪካ “ፋኖ”ን በምድብ 3 – “Tier III” – ሽብርተኛ ቡድንነት እንደፈረጀችው ተመላክቷል። ሰለሞን በትግራይ ተወላጆች ላይ ” የዘር ማጽዳት ” እንዲካሄድ እና ጥቃት እንዲሰነዘር በማህበራዊ ሚዲያ ሲቀሰቅስ ነበር ተብሏል። እነዚህን መረጃዎች ደብቆ ከአሜሪካ የኢሚግሬሽን ጥቅማጥቅሞችን ለመውሰድ በመሞከሩ ጥያቄው ውድቅ ተደርጎ ከሀገሪቱ ተባሯል።
አዲስ ሪፓርተር የዚህን እርምጃ አሜሪካና ኢትዮጵያ በቅርብ አጠናክረው ከቀጠሉት የፀረ-ሽብብር ዘመቻ እና ወታደራዊ አጋርነት ትብብር አንፃር ያለውን አንድምታ የሕግ እና የፀጥታና ደህንነት ባለሙያዎችን ቃለ መጠይቅ በማድረግ የሚከተለውን ሪፓርት አዘጋጅታለች

አቶ ኤፍሬም ከበደ በዋሽንግተን ዲሲ የዜግነትና የኢምግሬሽን ጉዳዮች የሕግ አማከሪ ናቸው። የኤሚግሬሽንና ጉሙሩክ ባለስልጣን የፋኖ አባል የሆነውን አቶ ሰለሞን ቦጋለን በምን የሕግ መሰረት ከአሜሪካ እንዳባረረው ለጠየቅናቸው ጥያቄ ሲመልሱ በአሜሪካ የኢሚግሬሽንና የዜግነት ሕግ (INA act) ክፍል 212(a)(3)(B)(vi)(III) መሠረት፣ አንድ ስብስብ በይፋ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የሽብርተኝነት መዝገብ ውስጥ ባይካተትም፣ ለኢሚግሬሽን ዓላማ ሲባል ግን እንደ “Tier III” ወይም “ያልተፈረጀ የሽብር ቡድን” ሊቆጠር ይችላል። ይህ ሕግ “ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ግለሰቦች ስብስብ ሆኖ በሽብር ተግባር ውስጥ የሚሳተፍ” ማንኛውንም አካል ያጠቃልላል። የሰለሞን ቦጋለ ጉዳይ መነጋገሪያ የሆነው፣ ግለሰቡ ራሱን የ”ፋኖ” አባል አድርጎ መግለጹ፣ የኢሜግሬሽንና ጉሙሩክ ባለስልጣኑ ቡድኑን(ፋኖን) በዚህ የሕግ ትርጓሜ ሥር እንዲመድበውና ግለሰቡንም ከሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት እንዳለው አካል እንድትመለከተው በማድረጉ እንደሆነ ገልፀዋል።
የሕጉ ንዑስ አንቀጽ (iv) ላይ የተጠቀሱት ከ (I) እስከ (VI) ያሉት ተግባራት “በሽብር ተግባር ውስጥ መሳተፍን” በዝርዝር ይተረጉማሉ። ከሰለሞን ቦጋለ ኬዝ ጋር በቀጥታ የሚገናኘው ንዑስ አንቀጽ (II) ሲሆን፣ ይህም “የሽብር ተግባር እንዲፈጸም ማነሳሳት ወይም መቀስቀስ” (Inciting) የሚለውን ይጨምራል። ግለሰቡ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ በትግራይ ተወላጆች ላይ “የዘር ማጽዳት” እንዲካሄድና ጥቃት እንዲሰነዘር ጥሪ ማቅረቡ፣ በአሜሪካ ሕግ ፊት እንደ ተራ የፖለቲካ ንግግር ሳይሆን፣ በቀጥታ ሽብርተኝነትን እንደ ማነሳሳት ተቆጥሮ ለሕግ ተጠያቂነት ዳርጎታል።
በሌላ በኩል፣ ግለሰቡ እነዚህን መረጃዎች ደብቆ ከአሜሪካ የኢሚግሬሽን ጥቅማጥቅሞችን (እንደ ጥገኝነት ወይም ቪዛ) ለመውሰድ መሞከሩ ሌላው የሕግ ጥሰት ነው። በአንቀጽ 212(a)(6)(C)(i) መሠረት፣ ሆን ብሎ መረጃን መደበቅ ወይም ማጭበርበር (Material Misrepresentation) ለአንድ ግለሰብ ጥያቄ ውድቅ መሆንና ከሀገር መባረር በቂ ምክንያት ነው። ሰለሞን ቦጋለ ከ”Tier III” ቡድን ጋር ያለውን ቁርኝትና የፈጸማቸውን የቅስቀሳ ተግባራት ደብቆ ለባለሥልጣናቱ በማቅረቡ፣ የአሜሪካ መንግሥት የኢሚግሬሽን ማጭበርበር ወንጀል ፈጽሟል በሚል ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ወስኗል።
የጥንቃቄ ምክር
በአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና የዜግነት ሕግ (INA) በንዑስ አንቀጽ (iv) ከቁጥር (I) እስከ (VI) የተዘረዘሩት ተግባራት፣ ማንኛውም ግለሰብ ከፋኖ ወይም መሰል “Tier III” (ያልተፈረጁ) የትጥቅ ቡድኖች ጋር በሚኖረው ግንኙነት ሳቢያ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ እና ከአሜሪካ እንዲባረር የሚያደርጉ ግልጽ መስፈርቶች ናቸው። እነዚህም በቀጥታ በውጊያ መሳተፍን ብቻ ሳይሆን፤ የትጥቅ እንቅስቃሴ እንዲደረግ ማነሳሳትን፣ መቀስቀስን፣ መረጃ ማሰባሰብን፣ ለቡድኑ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችን ማድረግን (Fundraising)፣ አባላትን መመልመልን እና ማንኛውንም ዓይነት ቁሳቁሳዊ ድጋፍ (Material Support) መስጠትን ያካትታሉ። ሕጉ “ቁሳቁሳዊ ድጋፍ” የሚለውን በሰፊው ይተረጉመዋል፤ ይህም ማለት ለታጣቂዎች የሚሆን የገንዘብ መዋጮ ማድረግ፣ የመገናኛ መሣሪያዎችን መግዛት፣ ወይም በማኅበራዊ ሚዲያ የቡድኑን የጥፋት ተልዕኮ የሚያሳኩ የፕሮፓጋንዳ ስራዎችን መስራት በአሜሪካ መንግሥት ዘንድ እንደ ሽብር ድጋፍ ተቆጥሮ ለከባድ ቅጣት ይዳርጋል።
በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ሕግ ሳቢያ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉባቸው የሚገቡ ነጥቦች አሉ። በመጀመሪያ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ (Facebook, X, TikTok) ላይ የሚደረጉ ማናቸውም የጥላቻ ንግግሮች፣ የተለየ ብሔር ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እንዲፈጸሙ የሚደረጉ ቅስቀሳዎች እና የትጥቅ ትግልን የሚያበረታቱ ጽሑፎች በአሜሪካ የደህንነት ተቋማት በቅርብ ክትትል የሚደረግባቸው መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ብዙዎች እንደ ቀልድ ወይም እንደ ፖለቲካዊ ተቃውሞ የሚለጥፏቸው መረጃዎች፣ በኋላ ላይ ለኢሚግሬሽን ጥቅማጥቅሞች (ለግሪን ካርድ ወይም ለዜግነት) እንቅፋት ከመሆናቸውም በላይ፣ እንደ ሰለሞን ቦጋለ ሁሉ ለስደት እና ለሀገር መባረር ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ። ስለሆነም፣ ከትጥቅ ቡድኖች ጋር የሚያገናኙ ማናቸውንም ዲጂታል አሻራዎችን ከመተው መቆጠብ ለግል ደህንነት ወሳኝ ነው።
በተጨማሪም፣ ማንኛውንም ዓይነት የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርጉ ድርጅቱ ወይም ተቀባዩ አካል በሕግ የተመዘገበና ከትጥቅ ትግል ጋር ንክኪ የሌለው መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል። በአሜሪካ ሕግ “አላውቅም ነበር” የሚለው ሰበብ ተቀባይነት ስለማይኖረው፣ ለሰብዓዊ እርዳታ ተብሎ የሚሰበሰብ ገንዘብ ለታጣቂዎች ትጥቅ መግዣ መዋሉ ከተረጋገጠ፣ ለጋሹ ግለሰብ በ”ቁሳቁሳዊ ድጋፍ” (Material Support) ወንጀል ሊጠየቅ ይችላል። ኢትዮጵያውያን በሀገር ወዳድነት ስሜት የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ከአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሕግ ጋር እንዳይጋጩ፣ ከማንኛውም ዓይነት የኃይል አማራጭን ከሚያራምዱ ስብስቦች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማቋረጥ እና በሰላማዊ የፖለቲካ ተሳትፎ ላይ ብቻ ማተኮር ለወደፊት ህይወታቸው አስተማማኝ ዋስትና ነው።
ይህ እርምጃ የመንግስትን የፀረ-ሽምቅ ጥረት እንዴት ይደግፋል?
ይህ አሜሪካ መንግስት እርምጃ የኢትዮጵያ መንግስት በሃገሪቱ ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ጠበንጃ አንስተው የትጥቅ ትግል የሚያደርጉትን ቡድኖች ወደ ሰለማዊ የፓለቲካ ትግል እንዲመለሱ የሚያደርገውን የፀረ ሽምቅ ውጊያ ጥረት እንዴት ሊደገፍ ይችላል ብለን የጠየቅናቸው የአፍሪካ ቀንድ የጂኦፓሊቲካ ጉዳዮች አማከሪ የሆኑት አቶ ምስክር አብይ የሰጡን ምላሽ “የሰለሞን ቦጋለ ከአሪዞና ፊኒክስ ተይዞ መባረር፣ አሜሪካ ለኢትዮጵያ መንግሥት የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥረት ያላትን የተግባር ድጋፍ የሚያሳይ ነው ብለዋል” ይህ እርምጃ በውጭ ሀገር የሚኖሩ የታጣቂ ደጋፊዎች በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያደርጉት የጥላቻና የጥቃት ቅስቀሳ ከባድ የሕግ ዋጋ እንደሚያስከፍል ትልቅ ማሳያ ነው። የአሜሪካ መንግሥት የኢሚግሬሽን ሕጉን እንደ ብሔራዊ ተፅዕኖ መሣሪያ (National Instrument of Power) በመጠቀም፣ የሽምቅ ተዋጊዎችን የሞራልና የፋይናንስ ድጋፍ ምንጭ በማድረቅ ለኢትዮጵያ መንግሥት የውስጥ ደህንነት መጠበቅ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አቶ ምስክር ገልፀዋል።
ይህ የሕግ አተረጓጎም ለፋኖ ብቻ የሚሠራ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በጦር መሣሪያ የሚንቀሳቀሱ እንደ ሕወሃት (TPLF) እና ኦነግ ሸኔ (OLA/Shene) ያሉ ቡድኖችንም በእኩልነት የሚመለከት ነው። ሕወሃት ምንም እንኳ በኢትዮጵያ ከሽብርተኝነት መዝገብ ቢሰረዝም፣ በአሜሪካ የኢሚግሬሽን ሕግ ግን ቀደም ሲል በነበረው የትጥቅ ትግል ወቅት “ቁሳቁሳዊ ድጋፍ” የሰጡ ግለሰቦች አሁንም ድረስ ጥቅማጥቅም ተከልክለው ይገኛሉ። በተመሳሳይ፣ ኦነግ ሸኔ በንጹሐን ላይ በሚፈጽመው ጥቃት ምክንያት በሕጉ መሠረት እንደ ሽብር ቡድን የሚቆጠር በመሆኑ፣ ደጋፊዎቹ በአሜሪካ የደህንነት ተቋማት ክትትል ይደረግባቸዋል። ይህም አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሕግ ውጭ የሚደረግ ማንኛውንም የትጥቅ እንቅስቃሴ እንደማትታገስ ያሳያል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393






