ከሃርሙዝ ወደ ያንቡ ቀይባህር – የሳዑዲ አዲስ አማራጭ ፣ የኢትዮጵያ ስልታዊ ሚና፣ ወርቃማ እድል እና አዲሱ አሰላለፍ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ሳውዲ አረቢያ በቀይ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው ስልታዊዋ የያንቡ ከተማ ላይ የያዘችው ግዙፍ የነዳጅ እና የኢኮኖሚ ዕቅድ፣ ከኢትዮጵያ ጋር አዲስ የወታደራዊና የደህንነት ጥብቅ የትብብር ምዕራፍ እንዲከፈት ምክንያት ሆኗል። ይህ ድንቅ አጋጣሚ ኢትዮጵያ በወጉ ልትጠቀምበት የሚገባ በመሆኑ “አገሬን” የሚሉ ዜጎች ሁሉ ተመሳሳይ አቋም ሊይዙበት እንደሚገባ ባለሙያዎች ይመክራሉ። በተቃዋሚነ ጎራ ያሉም ቢሆን የታሰበበት አካሄድ ሊመርጡ እንደሚገባ የሚመክሩ ወገኖች፣ ይህን ጉዳይ ማኮላሸት በታሪክም፣ በትውልድም የዘለዓለም እርም ሆኖ የሚመዘገብ ዝክራቸው እንደሚሆን ዝርዝር ማስረጃ አቅረበው ያስጠንቀቃሉ። እንዴት? ለምን?

ሳዑዲ አረቢያ በፋርስ ባህረ ሰላጤ (Persian Gulf) ላይ የሚገኘውን የሆርሙዝ ወሽመጥ ስጋት ለመቀነስ፣ 1,200 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የ”ምስራቅ-ምዕራብ” (East-West Pipeline) የነዳጅ ቧንቧ መስመር በሙሉ አቅሙ ስራ ላይ ለማዋል እየተንቀሳቀሰች እንደሆነ ተሰምቷል።

ይህ ግዙፍ መሠረተ ልማት በቀን እስከ 7 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ቀይ ባህር ጠረፍ ላይ ወደ ሚገኘው ያንቡ (Yanbu) ወደብ የማጓጓዝ አቅም ያለው ሲሆን፣ ዓላማውም በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ አቅርቦት እንዳይቋረጥና የገበያ መረጋጋት እንዲፈጠር ማድረግ ነው።

ያንቡ ከመዲና ከተማ በስተምዕራብ በኩል በግምት 160 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የከተመች፣ ከጅዳ ቀጥሎ በቀይ ባሕር ላይ የምትገኝ ሁለተኛዋ ትልቅ የንግድ ወደብ ናት። የዚህ መስመር ዋና ዓላማ አሁን እያወዛገበ ያለው የሆርሙዝ ወሽመጥን ሳይጠቀሙ ነዳጅን ወደ ዓለም ገበያ ማድረስ ነው። ያንቡ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ በኩል የሚፈጠርን የጸጥታ ስጋት ወይም መስተጓጎል በመቋቋም ነዳጅን በቀጥታ ወደ ቀይ ባሕር ለማመላለስ ታስቦ የተገነባ ሲሆን፣ ነዳጅን ወደ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ በቀይ ባሕር በኩል ለማጓጓዝ ዓይነተኛ አማራጭ ነው።

ይህ ግዙፍ መስመር በቀን እስከ 5 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ የማስተላለፍ አቅም አለው። ሳውዲ አረቢያ ይህንን አቅም ወደ 7 ሚሊዮን በርሜል ለማሳደግ ዕቅድ አውጥታ እየሰራች ነው።

በተመሳሳይ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችም በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ፣ በቀን 1.8 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ወደ ፉጃይራ (Fujairah) ወደብ የሚያደርሰውን የቧንቧ መስመር በስፋት ለመጠቀም ስልታዊ ዝግጅት እያደረች መሆኑ ተገልጿል። እንግዲህ እዚህ ጋር ነው ኢትዮጵያ በጉልህ የምትታየው።

የሁቲ አማፅያን ስጋት

የሳዑዲ የዘረጋችው አማራጭ መስመር የሚያርፍበት የያንቡ ወደብ፣ ከደህንነት ስጋት ነፃ አለመሆኑ ለቀጠናው ትልቅ ፈተና ሆኗል። እ.ኤ.አ. በ2019 የሁቲ አማጽያን በወደቡና በቧንቧ መስመሮቹ ላይ በፈጸሙት የድሮን ጥቃት ከፍተኛ መስተጓጎል መፈጠሩ የሚታወስ ነው። የበሆርሙዝ ወሽመጥን በመዝጋት የገጠማትን ቀውስ ለማለፍ እንደ አንድ አማራጭ የያዘችው ኢራን የምትደግፋቸው የሃውቲ አማጽያን አሁንም በየመን በኩል ወደቡን ዳግም የጥቃት ኢላማ ሊያደርጉት እንደሚችሉ የደህንነት ምንጮች እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። ይህ ስጋት የቀይ ባህር ቀጠና ከሆርሙዝ ወሽመጥ ያልተናነሰ የጸጥታ ስጋት ያለበት መሆኑንና የነዳጅ ፍሰቱ በማንኛውም ጊዜ ሊገታ እንደሚችል አመላካች ሆኖ ቀርቧል።

እቅዱ አሁን ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የያዘችውን ዓለምን የማስጨነቅ ስልት ፖለቲካዊ ፋይዳ የሚቀንስ በመሆኑ የሃውቲ አማጽያን ለኢራን አሳብ ተገዢ የመሆናቸው ጉዳይ ጥርጥር እንደሌለው የሚናገሩ፣ የሳኡዲና የተባበሩት ኢምሬትስ ዳግም መታረቅ ይህንኑ ስጋት ከማስወገድ አንጻር ጉልህ ሚና እንዳለው ይናገራሉ። ከዚህም በላይ ሳዑዲና ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ያደረጉትን ሚስጢራዊ ውይይትም ያነሳሉ።

ኢትዮጵያን ያሳተፈ ወታደራዊ ጥምረት

በቀይ ባህርና በባቢል መንደብ አካባቢ የሁቲ አማጽያን የሚያደርሱትን የባህር ላይ ትንኮሳና የጸጥታ ስጋት ለመግታት፣ ዓለም አቀፍና ቀጠናዊ የሀገራት ጥምረት የመመስረት አስፈላጊነት ከምንጊዜውም በላይ እየጎላ መጥቷል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በቀጠናው ያላት ወታደራዊና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ከግምት ውስጥ ገብቶ፣ በታቀደው የሀገራት ጥምረት ውስጥ ቁልፍ ሚና እንደሚኖራት ይጠበቃል። ኢትዮጵያ የቀይ ባህር የባህር በር ባለቤት ባትሆንም፣ ለቀጠናው ሰላምና ደህንነት ያላት ቁርጠኝነትና የባህር ኃይል ግንባታ ጥረቷ በባህር ላይ የሚፈጸሙ የሽብር ጥቃቶችን ለመከላከል በሚደረገው ዘመቻ ውስጥ እንደ ትልቅ ግብዓት እየታየ ይገኛል።

የኢትዮጵያ በዚህ ጥምረት ውስጥ መሳተፍ ለሀገሪቱ ስልታዊ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን፣ በተለይም ከጂኦፖለቲካዊ ተሰሚነትና ከብሄራዊ ደህንነት አኳያ ትልቅ ትርጉም ይሰጠዋል። በቀይ ባህር ላይ የሚፈጠር ማንኛውም የጸጥታ ቀውስ በቀጥታ የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ ላይ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራትና ከዓለም አቀፍ ኃይሎች ጋር በመተባበር የባህር መስመሩን ደህንነት የማስጠበቅ ፍላጎት አላት። ይህ ተሳትፎ ሀገሪቱ በቀጠናው ያላትን የዲፕሎማሲ አቅም ከማሳደጉም ባለፈ፣ ከሳዑዲ አረቢያና ከኤምሬቶች ጋር ያላትን ስልታዊ አጋርነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ተገምቷል።

በሌላ በኩል የቀጠናው የጸጥታ ስጋት በነዳጅ ዋጋና በአለም አቀፍ ንግድ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ የብዙ ሀገራትን ስጋት ቀስቅሷል። የሳዑዲና የኤምሬቶች አማራጭ የቧንቧ መስመሮች ዓለምን ከከፋ የነዳጅ እጥረት ቢታደጉም፣ የሁቲ አማጽያን በቀይ ባህርና በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ ያላቸውን የጥቃት አድማስ ማስፋታቸው የኢንሹራንስና የመጓጓዣ ወጪዎችን በእጅጉ ከፍ አድርጎታል። በመሆኑም የኢትዮጵያና መሰል የቀጠናው ሀገራት ወታደራዊ ድጋፍ ለንግድ መርከቦች ጥበቃና ለነዳጅ መሠረተ ልማቶች ደህንነት ዋስትና ለመስጠት እንደ ወሳኝ አማራጭ እየታየ ይገኛል።

በቀይ ባህር ዙሪያ እየተከሰተ ያለው የኃይል አሰላለፍ ለኢትዮጵያ አዲስ የታሪክና የዲፕሎማሲ ምዕራፍ የሚከፍት ነው። ሳዑዲ አረቢያ ነዳጇን ወደ ምዕራብ ለማሸሽ በምታደርገው ጥረት ውስጥ፣ የቀጠናው ሀገራት መረጋጋትና ትብብር ወሳኝ በመሆኑ የኢትዮጵያ ሚና ከታዛቢነት ወደ ንቁ ተሳታፊነት እየተቀየረ ይገኛል። በቅርብ በሚፈጠረው ጥምረት ውስጥ የኢትዮጵያ ሚና ምን ያህል ስፋት እንደሚኖረው ባይታወቅም፣ የቀይ ባህር ሰላም ግን ከሀገሪቱ የኢኮኖሚና የደህንነት ህልውና ጋር በቀጥታ የተቆራኘ መሆኑ እንደማይቀየር የዘርፉ ተንታኞች ይስማሙበታል።

ከዚያ ቀደም በሪያድ የተከናወኑትን የቀጥታና የጎንዮሽ ውይይት ሳያካትት በጥር ወር 2024፣ አዲስ አበባ የሳውዲ አረቢያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ፋያድ ቢን ሃመድ አል-ሩዋይሊ ከአቻቸው ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ጋር መክረዋል። ምክክራቸው በሽብርተኝነት እና በቀይ ባሕር ደህንነት ዙሪያ የመከላከያና የደህንነት ትብብር በማድረግ አብረው ለመስራት ምስማማታቸው የሚታወስ ነው። ይህ መረጃ የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂያዊ ግንኙነት እድገት በግልጽ የሚያመላክት ሲሆን በቅርቡ ሳዑዲ አረቢያና የኢትዮጵያ የወቅቱ የልብ ወዳጅ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ልዩነታቸውን አስወግደው በሁሉም ዘርፍ አብረው ለመስራት ዳግም ግንኙነታቸውን ማደሳቸው ዜናውን ያጎላዋል።

ከምንም በላይ የእስራኤል ወደ ቀይ ባህር መግባትና አሜሪካ የመከላከያ ኃይሏን ሙሉ በሙሉ በዚሁ በአፍሪቃ ቀንድ ባብ ኤልማንደብ ማስፈሯ፣ በይፋ ባይነገርም ኢትዮጵያ ባሕር ኃይሏ ቀይ ባህር ላይ መስፈሯ ከላይ ከተነሱት ጉዳዮች ጋር ሲገጣጠሙ፣ ኢትዮጵያ ቀይ ባሕር ላይ የመመለሷ ጉዳይ ብዙ ርቀት የሄደ ይመስላል።

ይህ የኢትዮ-ሳውዲ ትብብር በግብፅ እና በሱዳን ላይ የሚያሳድረው ጫናና እነዚሁ አገራት የሚያንቀሳቅሷቸው ኃይሎች ስጋት ቀላል አይደለም። የሳውዲ አረቢያ እና የኢትዮጵያ በስትራቴጂክ ጉዳዮ መቀራረባቸውና ወታደራዊና የደህንነት ስምምነት ላይ መድረሳቸው፣ ግብፅ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ያላትን የዲፕሎማሲ የበላይነት ሊቀንስባት ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሮባታል።ሳውዲ በግድቡ ጉዳይ ላይ “ገለልተኛ” መሆኗ ግብፅ በዓረብ ሊግ በኩል የምታገኘውን ሙሉ ድጋፍ ሊከፋፍልባት ይችላል የሚል እምነት አላት። ኤርትራም በተመሳሳይ ከሳዑዲ ቃልና ተዕዛዝ ስለማትወጣ ግንኙነቱን ፈርታለች።

በሱዳን ባለው ስር የሰደደ ግጭት ምክንያት፣ ሳውዲ እና ኢትዮጵያ በጋራ መሥራታቸው ለሱዳን ሰላም ወሳኝ ነው። ሆኖም በሱዳን ያሉ ኢትዮጵያ ላይ የተደራጁ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች ሳውዲ በኢትዮጵያ በኩል የምታደርገው ተፅዕኖ በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ላይ ሚዛን እንዲያጡ ያደርጋቸዋል። ለዚህ ይመስላል አንዳንድ ተቃዋሚዎች ጃዋር መሐመድን ጨምሮ ሕዝብ እየሰማ ለሱዳኑ ጄኔራል አልቡርሃን በግልጽ ጥብቅና ቆመው “አገራቸውን” ሲከሱ የሚሰማው። በግብጽና ኤርትራ ውክልና ኢትዮጵያን ሲወነጅሉ የሚሰማው።

በዚህ መነሻ የኢትዮጵያን ወደ ቀይ ባሕር መመለስ ከቶውንም የማትመኘው ግብጽና የግብጽ መጠቀሚያ የምትባለዋ ኤርትራ ኢትዮጵያን በውስጥ ችግር ለማጥመድ ከመቼውም በላይ እይሰሩ ነው። ለዚሁ ተግባራቸው ከፍተኛ ሃብት፣ መሳሪያና የሎጂስቲክ በማድረግ ኢትዮጵያን በውስጥ ቀውስ እንድትነከር ከታጣቂ መተጨማሪ ሕዝብ የተሳሳተ መረጃ እንዲይዝ ሰፊ የዩቲዩብ፣ የፌስ ቡክ፣ የቲውተርና መስል ሰራዊት አደራጅተው በስፋት የሳይበር ዘመቻ ከፍተዋል።

ብሄራዊ ጥቅምና ፖለቲካን እንዳይለይ ተደርጎ የተሰራው የተቃዋሚ ኃይል የትጥቅ ትግሉን ከፕሮፓጋንዳው ጋር በማቀናጀት፣ አገር ውስጥ በህጋዊ ተመዝግበው ከሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በመሆን የትርምስ አጀንዳ በህዝባዊ እምቢተኝነት ስም ዕቅድ አዘጋጅተዋል። ይህ ሁሉ አልበቃ ስላለና በሚፈለገው ደረጃ አገሪቱ ልትፈርስ ባለመቻሏ፣ ከብሄር ግጭት በተጨማሪ የኃይማኖት ብጥብጥ ለማስነሳት ግድያ፣ የተሳሳተ ትርክት፣ የብሶትና አንዱን በዳይ ሌላውን ተበዳይ የሚያስመስል ቅስቀሳ በመናበብ ጀምረዋል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር ለመመልስ ቆርጣ በመነሳቷ ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ቀይ ባህር ተመልሳ የባህር በር ባለቤት እንዳትሆን በገዛ ልጆቿ በቅንጅት ዘመቻ እየተካሄደባት ቢሆንም፣ በሚቆረቆሩላት አብዛኞች ዓላማዋን እንደምታሳካ የበርካቶች እምነት ነው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ጃልመሮ በየኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ቃል አቀባይና አማካሪ አማካይነት የእነ አቶ ልደቱን የአመጽ አስተባባሪ ቡድን ተቀላቀሉ

ዛሬ የጥምር ስብሰባ ይካሄዳል፤ በስብሰባው ሻዕቢያ ያደራጃቸው ቡድኖች ይሳተፋሉ...

ሙስጠፌ ተረኛው ባለስልጣን – በሶምሊ ክልል የጥፋት ኃይሎች ተስፋ መቁረጥ የወለደው የሃሰት ትርክ ዘመቻ ሲፈተሽ

አዲስ ሪፓርተር- በግምት ከወር በፊት በዚህ ድረገጽ ቀጣዩ የተቃዋሚው...

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

አዲስ ሪፖርተር - ኢራን በእስራኤልና በአሜሪካ የተከፈተባትን  ጦርነት ለመመከት...