በመጪው ምርጫ በርካታ ተቃዋሚዎች በፓርላማና በክልል ምክር ቤቶች ይገባሉ
አዲስ ሪፖርተር – በምርጫ መጨረሻ ሰዓት ራሳቸውን ከምርጫ ለማግለል በውጭ አገር ካሉ የተለያዩ የተቃዋሚዎች አደረጃጀትና፣ በውጭ መንግስታት ከሚደገፉ ኃይሎች ጋር ውል ያሰሩ ፓርቲዎች መካከል አቋም የቀየሩ መኖራቸው ተሰማ።በመጪው ምርጫ በርካታ ተቃዋሚዎች በፓርላማና በክልል ምክር ቤቶች ይገባሉ።

የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ ከፓርቲዎቹ ጋር ውል ካሰሩ ወገኖች ጋር በኮሚቴነት የሚሰሩትን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በመጨረሻ ሰዓት ምርጫውን ጥሎ በመውጣት ተቀባይነት እንዳይኖረው ስምምነት ካደረጉት መካከል ሃሳባቸውን የቀየሩ መኖራቸው ብስጭት ፈጥሯል።
በዋሽንግቶንና በሎንዶን ይደረጋል የተባለው “ምድር አንቀጥቅጥ” የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ ምክንያቶች እንደማይሳካ አቶ ነዓምን ዘለቀ የአመጽ አመቻች ቡድኖች ጥምረት ላይ መናገራቸውን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። የኢትዮጵያን አድን ተወካያ ዶክተር ሚካኤል “የተግለበለበ ስብስብ ነው” በማለት ውህደቱ መርህ አልባ መሆኑን ሲተቹ “ሰላማዊ ሰልፍ የሚባለው አይሳካም” ሲሉ ነበር አቶ ነዓምን ስጋታቸውን የገለጹት። አቶ ነዓምን አክለውም “ዋናው ስራ የሚሰራው አገር ቤት ባሉት ተባባሪዎቻችን አማካይነት ነው” በማለት አስታውቀው ነበር።
ተባባሪያችን እንዳለው በመጨረሻው ሰዓት ተያይዘው ከምርጫ ለመውጣት ከተስማሙ የጥምረት ኃይሎች መካከል “በምርጫው የተከፈተውን በር እንጠቀምበት” በማለት አቋም እንደቀየሩ የገለጹ አሉ። በዚህም ምክንያት የሻዕቢያ ወኪል በመሆን ተቃዋሚዎችንና ሚዲያዎችን እንደሚመሩ በዛው ስብሰውባ ላይ የትህነግ ተወካይ የመሰከሩባቸው አቶ ነዓምን በግል ድርድር መጀመራቸው ተመልክቷል። ለጊዜው ዝርዝር ባይቀርብም የድምጽ መረጃ ያላቸው እንዳሉም ተመልክቷል።
“ምርጫው ተአማኒ አይደል፣ ብልጽግና ከራሱ ጋር ተወዳድሮ ነው ራሱን ያሸነፈው” በሚል በዓለ ዓቀፍ ደረጃ ቅቡል እንዳይሆን በጀት ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን በተደጋጋሚ የአመጽ አነሳሾችን ቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ በመጥቀስ መዘገባችን አይዘነጋም።
በዚሁ መሰረት በተለያዩ ጊዚያት ተቋቁመው የነበሩ አመጽ አነሳሽ ቡድኖች ራሳቸውን አንድ ለማድረግ በጠሩት ስብሰባ በተዘጋጀ የመግባቢያ ሰነድ ባይሳማሙም ሰብሳቢዎቹ በአገር ቤት ተባባሪና አደራጅ ኃይል መኖሩን አመልክተዋ ዋናው ስራ የሚሰራው በእነዚሁ ክፍሎች አማካይነት እንደሆነ አስታውቀው ነበር። ይህን አስታውሰው ለተባባሪያችን መረጃ ያካፈሉት ወገኖች ” አራት ፓርቲዎች ከምርጫው ብንወጣም የሚፈጠር ነገር የለም። ምርጫውን ውድቅ ሊያደርጉ የሚችሉ አገራት ከመንግስት ጋር ናቸው። ሌሎች በርካታ ፓርቲዎችም አብረው ስለሚሰሩ እኛ መውታታችን ዋጋ የለውም። ይልቁኑም ብልጽግና በተወሰነ ደረጃ በሚለቀው ቦታ ለማሸነፍ መስራቱ ይሻላል” ማለታቸው ተናግረዋል።
ይህ የፓርቲዎቹ አቋም አቶ ነዓምንና እሳቸውን የሚመሯቸው የውጭ ኃይሎችን ክፉኛ ያበሳጨ ሲሆን፣ ከቀድሞው በበለጠ ጠንካራ ፕሮፓጋንዳ እንዲዘጋጅ፣ በፓርቲዎቹ ላይም ጫና ለማሳደር ማስጠንቀቂያዎችን ጭምር ያቀፈ ፕሮግራም እንዲካተትና አዲስ አበባ ያሉትንና አሳባቸውን የቀየሩትን የፓርቲ አመራሮች አቋማቸውን ካላስተካከሉ በተዋረድ በተደራጁ የማህበራዊ ሚዲያ አማካይነት የማሳጣት ስራ ለመስራት ዕቅድ መያዙ ተሰምቷል።
ይህን አስመልክቶ አቋማቸውን እንደቀየሩ ለዝግጅት ክፍላችን በስም የተጠቀሱትን የአንድ ፓርቲ አመራር አነጋግረን “ወሬ ነው። የተደረገ ስምምነት የለም። እንደተባለው ግን በማስፈራራት የሚኬድ ከሆነ እርቃኑን የሚቀራው ማን እንደሆነ ይታወቃል” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
በዘንድሮው ምርጫ በአዲስ አበባ ምክር ቤት አነሰ ከተባለ ከሃያ በላይ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እንደሚገቡ ሲጠበቅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደግሞ ከሃያ በመቶ የሚልቁ እንደሚመረጡ ከወዲሁ እዩእተነገረ ነው።
ይህንኑ እድል በመጠቀም እየተቃወሙ በፓርላማ እንዴት አብሮ መስራት እንደሚቻል ማሳየትና ዴሞክራሲን መለማመድ የተሻለ እንደሆነ በመጠቆም በርካታ ፓርቲ ካቀረቡት መካከል አብዛኞቹ የምርጫውን ቀን እየጠበቁ ነው።
ፎቶ ቢቢሲ (ከግራ ወደ ቀኝ) የአብን ሊቀ መንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ የኢዜማ ሊቀ መንበር ኢዮብ መሳፍንት፣ የአብን ምክትል ሊቀ መንበር መልካሙ ፀጋዬ እና የኢዜማ ምክትል ሊቀ መንበር ንጋቱ ወልዴ
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393






