የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓት ደህንነት ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና ጥበቃ የወቅቱ ጥያቄ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በኢትዮጵያ በፍጥነት እየገሰገሰ የመጣውን የዲጂታል ፋይናንስ ምህዳር ተከትሎ የሚስተዋሉ ስጋቶችን በጋራ ለመከላከልና ዘላቂ መፍትሄዎችን ለማመላከት ያለመ ከፍተኛ የፓናል ውይይት ተካሄደ።

ውይይቱ “ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ፋይናንስ ለሀገራዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን፣ የዘርፉን ቁልፍ ባለድርሻ አካላትና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን በአንድ መድረክ አገናኝቷል።

ይህንን ስትራቴጂያዊ የፓናል ውይይት በበላይነት የመሩት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ በንግግራቸው፤ የዲጂታል ፋይናንስ ምህዳሩን ከስጋት ነፃ ማድረግ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና ለዜጎች ደህንነት ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። አቶ ዳንኤል አክለውም፣ የዲጂታል ፋይናንስን የሳይበር ደህንነት ማረጋገጥ የአንድ ተቋም ድርሻ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ውጤት መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

በፓናሊስትነት የተሳተፉት የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ በበኩላቸው፤ ባንኩ የፋይናንስ ተቋማትን ደህንነት ለማረጋገጥ የቁጥጥር ስርዓቱን ከዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ጋር እያጣጣመ መሆኑን ገልጸዋል።

ተቋማት ጠንካራ የቴክኖሎጂ አቅም እና የሰለጠነ የሰው ኃይል እንዲገነቡ የሚያስገድዱ የፖሊሲ ማሻሻያዎች እየተተገበሩ መሆኑንም አብራርተዋል።

በተመሳሳይ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሊሳ አብዲሳ፤ በህግ አስከባሪዎችና በአገልግሎት ሰጪዎች መካከል ያለውን የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥ ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም ወንጀለኞችን በአፋጣኝ ለይቶ ለህግ ለማቅረብና የተደራጁ የዲጂታል ጥቃቶችን ለመቀልበስ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ከኢትዮ ቴሌኮም በኩል የፓናል ውይይቱ ተሳታፊ የነበሩት የቺፍ ሞባይል መኒ ቢዝነስ ኦፊሰር አቶ ብሩክ አድኃና፤ የዲጂታል ማጭበርበርን ለመከላከል እየተወሰዱ ያሉ የባዮሜትሪክ ማረጋገጫ እርምጃዎችን አንስተዋል።

ተቋማቸው ችግሩን ለመቅረፍ የሳይበር ደህንነት መዋቅሮችን በመፍጠርና የዲጂታል ማንነት ማረጋገጫ ስርዓቶችን በማዘመን በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሥዩም ዳምጠው በበኩላቸው፤ የማንነት እና የዲጂታል ፋይናንስ ማጭበርበርን ለመከላከል ተቋማት የቴክኖሎጂ አቅማቸውንና የደህንነት ማዕቀፎቻቸውን በየጊዜው ማዘመን እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ባንኩ የደንበኞችን መረጃና የዲጂታል ሀብት ከአጭበርባሪዎች ለመጠበቅ የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ የክትትል እርምጃዎችን በቁርጠኝነት እየተገበረ መሆኑንም አብራርተዋል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በፓናሊስቶቹ ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን፣ ይህም በመድረኩ ላይ ለነበረው ሃሳብ መለዋወጥ ተጨማሪ ጠቃሚ ግብዓት ሆኗል።

የውይይቱን ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር ዲማ ነገዎ (ዶ/ር)፤ የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ያለውን ፋይዳ በመጥቀስ፣ ስርዓቱ ግን በሰላምና በደህንነት ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ክቡር ሰብሳቢው እንደገለጹት፤ የሳይበር ወንጀል ስልቶች በየቀኑ የሚቀያየሩ በመሆናቸው ሀገራዊ የህግ ማዕቀፎች እነዚህን ወንጀሎች ለመቆጣጠር በሚያስችል መልኩ በየጊዜው መዘመን አለባቸው።

በመጨረሻም ጉዳዩ በሚመለከታቸው ተቋማት መካከል ያለው ቅንጅት በቴክኖሎጂ የተደገፈና ወደ ተግባር የተቀየረ መሆን እንዳለበት ገልጸው፤ ቋሚ ኮሚቴው ይህንን የቅንጅት ስራ በቅርበት እንደሚከታተልና ድጋፍ እንደሚሰጥ የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የዲሲና ሎንዶን ሰላማዊ ሰልፍ ይሳካል?

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ ምርጫ እንዳይካሄድ ለመበጥበጥ የተቋቋመው ጥምር...

“ዓለም አቀፍ ጫና ሲደርስ ችግሩን መሻገር የሚቻለው ከምክንያት በላይ ኾኖ በመገኘት ነው” የኢኮኖሚ ምሁር

አዲስ ሪፖርተር - በመካከለኛው ምሥራቅ የተፈጠረው ጦርነት በሀገራት ኢኮኖሚ...

በመጨረሻ ሰዓት ራሳቸውን ከምርጫ ለማግለል ውጭ ካሉ ኃይሎች ጋር ውል ከገቡት መካከል አቋም የቀየሩ መኖራቸው ተሰማ

በመጪው ምርጫ በርካታ ተቃዋሚዎች በፓርላማና በክልል ምክር ቤቶች...