ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የዲሲና ሎንዶን ሰላማዊ ሰልፍ ይሳካል?

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በኢትዮጵያ ምርጫ እንዳይካሄድ ለመበጥበጥ የተቋቋመው ጥምር የቴክኒክ ኮሚቴ፣ ከዛሬ ቅዳሜ ጀምሮ በዩቲዩብ ቃለ መጠይቅ እንዲያደርጉ ከተደለደሉት ውስጥ የኢትዮጵያን አድን ተወካይ የነበሩትን ዶክተር ሚኒሊክን አገለለ። ባለፈው ረቡዕ በተካሄደው ስብሰባ ላይ “በመግለብለብ መራመድ አያስፈልግም” ሲሉ ስብሰባው መርህ ላይ እንዲመሰረት ጠይቀው ነበር። የፋኖ ሶስተኛ ደረጃ አሸባሪ መባል አስፈርቷል።

በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ከዛሬ ቅዳሜ ጀምሮ እስከ አርብ ድረስ ቃለ-መጠይቅ የሚሰጡ ሰዎች የምደባ ዝርዝር ተዘጋጅቶ በተሰራጨው ደብዳቤ ላይ የዶክተር ሚኒሊክ ስም አልተካተተም። ዶክተሩ አቶ ነዓምን እና አቶ ልደቱ ያደራጁት የአመጽ አመቻችና አስተባባሪ ቴክኒክ ኮሚቴ ጥምረት ለመፍጠር ረቡዕ በተደረገው የባለፈው እሁድ ስበብሰባ ቀጣይ ውይይት ላይ “የዲጂታል ስብሰባው የተሻለ ነው። የሰላማዊ ሰልፉ ጉዳይ ግን አያዋጣም፤ ሰው አይወጣልንም” ብለውም ነበር።

የፋኖ በሶስተኛ ደረጃ አሸባሪነት መፈረጅ በፈጠረው ስጋት፣ ወልቃይትንና ራያን አሳልፈው ለመስጠት ተስማምተዋል በተባሉት ከፊል የፋኖ አደረጃጀት ሳቢያ በተፈጠረው መከፋፈል፣ አሁን እየተካሄደ ያለውን የአምጽ ጥሪ እያቀነባበረ ያለው ሻዕቢያ በመሆኑ፣ እና በአገር ቤት በሰላማዊ ዜጎች ላይ በጅምላ የሚደርሰው በደል የፈጠረው ብስጭት አንድ ላይ ተዳምሮ ስለፉን ተቀባይነት እንዲያጣ እንዳደረገው የስብሰባው ተሳታፊዎች አመልክተዋል።

በውይይቱ መጀመሪያ ላይ የሻዕቢያ ወኪል እንደሆኑ በባልደረባቸው የተመሰከረባቸው አቶ ነዓምን፣ ስብሰቡ በአመጽ ምርጫውን ለማኮላሸትና ቅቡል እንዳይሆን ለማድረግ ከመስራት ውጪ ሌላ ዓላማ እንደሌለው አቅጣጫ ሲሰጡ የተቃውሙት ዶክተር ሚካኤል፣ አካሄዱ ግብስብስ መሆኑ ከኢትዮጵያን አድን አቋም የተያዘበት ነው ብለዋል። የቮይስ ኦፍ ኢትዮጵያ ምንጮች እንዳሉት ዶክተር ሚኒሊክ ይህን በማለታቸው ሳቢያ ነው ከቅስቀሳው ምድብ ውጪ የሆኑት።

“መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች አሉ” ያሉት ዶከተር ሚካኤል፣ አንከር ላይ በተለቀቀው የሰልፍ ጥሪ ማስታወቂያ በባለቤትነት የተጠቀሰው “የሰላማዊ ሰልፍና ትዕይንት አስተባባሪ” የሚለው አገላለጽ ትክክል እንዳልሆነም በረቡዕ ስብሰባ ላይ አስታውቀው ነበር። በስብሰባ የተሰየመ ስም ሳይሰጥና በጋራ የተያዘ አቋም ሳይኖር፣ ማስታወቂያ መሰራቱ በራሱ ክህብረቱ ይልቅ መበተኑ እንደሚቀድም ማሳያ እንደሆነም ተናገው ነበር። አክለውም “ነገሩ ሸፍጥ ይመስላል” በማለት የአሰራና የድርክት መርህ መከተል ሊቀድም እንደሚገባው አሳስበው ነበር።

የስብሰባው አቅጣጫ መሪና ተቆጣጣሪ የሆኑት የሻዕቢያ ወኪል አቶ ነዓምን ዘለቀ በበኩላቸው “እመነኝ” ሲሉ ሸፍጥ እንደሌለ ምለው ስብሰባው አቶ ጅሬኛን ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ አቶ ያሬድን ከአቶ ነዓምን ድርጅት፣ አቶ ኢንጂነር ሙሉጌታን መርጦ ተበትኖ ነበር።

ስብሰባው በዚህ መልኩ ከተበተነ በኋላ ለቅዳሜው የኢንተርኔት ሰልፍ ቅሰቀሳ እንዲያደርጉ በተዘጋጀው የተናጋሪና ሚዲያ ዝርዝር ውስጥ ዶክተር ሚኒሊክ አለካተታቸው ታውቋል።

በድልድሉ መሰረት አብረው የተቀናጁት ሰዎች በተመደቡበት ሚዲያ የሚናገሩትም ተዘጋጅቶላቸዋል። በመጀመሪያ በየራሳቸው ቋንቋ “እኔ እገሌ ነኝ” በማለት ህዝቡ እንዲያምጽ ጥሪ በማቅረብ ራሳቸውን ቀርጸው ለእነ አቶ ነዓምን ይልኩና ሳምንቱን ሙሉ ማስታወቂያ ይሰራባቸዋል።

በአምስት ዋና ጉዳዮች ማለትም፣ ምርጫ አያስፈልግም፣ ጦርነት ይቁም፣ሰላም ይስፈን፣ ያለውን መንግስት አገዛዝ በማለት መጥራት፣ እንዲሁም የሽግግር መንግስት ይቋቋም የሚሉ አሳቦችን ብቻ እንዲያሰራጩ መመሪያ መተላለፉን፣ በስልክም የግል ግንኙነት እየተደረገ ይሄው አካሄደ ወጥ እንዲሂን መመሪያ እየተሰጠ መሆኑ ታውቋል።

ሚዲያዎቹ ከሻዕቢያ በቀጥታ የሚከፈላቸውን ጨምሮ ተናጋሪዎቹን ከዚህ ውጪ ጥያቄ እንደምያቀርቡላቸው ተነግሯቸዋል። በዚሁ ምደባ መሰረት

  1. EMS- ነዓምንና አብዩ
  2. ⁠አንከር- ገዱና ጀዋር(አባይ)
  3. ⁠ርዕዮት- ሕዝቅኤልና ያሬድ
  4. ⁠ዛራ- ጅሩና አባይ
  5. ⁠ነፃ ፕሬስ- ገለታውና ያሬድ
  6. ⁠ኢትዮ-ኒውስ(በቃሉ)- ነዓምንና ገለታው
  7. ⁠አዲስ ድምጽ— ልደቱና እስማኤል
  8. ⁠ሆርን- ያሬድና ሕዝቅኤል
  9. ⁠የሀሳብ-ገበታ— ሙሉጌታና ገለታው
  10. ⁠ሆራይዘን- ሙሉጌታና አባይ
  11. ⁠ኩሽ— ልደቱና ጅሩ
  12. ⁠ነጋሪ— ነዓምንና አቢዩ
  13. ⁠⁠መቲ— እስማኤልና ኦባንግ
  14. ⁠ABC(ትንግርቱ)— ነዓምንና ያሬድ
  15. ⁠ኢትዮ-ፎረም- ገዱ፣ አባይ፣ልደቱና ጀዋር(ጅሩ)
  16. ⁠ቴዲ-አዋሳ(ቲክ-ቶክ)— ጀዋር(ሕዝቅኤል)፣ ገዱ፣አባይና ልደቱ። ሆነው ተመድበዋል። ጃዋር መሐመድ ካልተገኘ በሚል ተተኪ ተመቻችቷል።

የምደባው ቅጽ “ምቾት የማይሰጥ ምደባ ካለ ሚዲያዎቹን መለዋዎጥም ይቻላል። ተጣማሪ ሰዎች ከሚዲያዎቹ ጋር ተነጋግራችሁ እራሳችሁ ቀጠሮ ብትይዙና ቃለ-መጠይቅ ብትሰጡ። ምንአልባት ከሚዲያዎቹ ጋር ትውውቅ ከሌላችሁ ለእኔ ወይም ለነዓምን ብትነግሩን ልናነጋግራቸው እንችላለን።” ሲል አቶ ልደቱ በደብዳቤው መጨረሻ ላይ መልዕክት አስፍሯል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ዓለም አቀፍ ጫና ሲደርስ ችግሩን መሻገር የሚቻለው ከምክንያት በላይ ኾኖ በመገኘት ነው” የኢኮኖሚ ምሁር

አዲስ ሪፖርተር - በመካከለኛው ምሥራቅ የተፈጠረው ጦርነት በሀገራት ኢኮኖሚ...

የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓት ደህንነት ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና ጥበቃ የወቅቱ ጥያቄ

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ በፍጥነት እየገሰገሰ የመጣውን የዲጂታል ፋይናንስ...

በመጨረሻ ሰዓት ራሳቸውን ከምርጫ ለማግለል ውጭ ካሉ ኃይሎች ጋር ውል ከገቡት መካከል አቋም የቀየሩ መኖራቸው ተሰማ

በመጪው ምርጫ በርካታ ተቃዋሚዎች በፓርላማና በክልል ምክር ቤቶች...