አዲስ ሪፖርተር – በኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ አነጋጋሪ ሰው ናቸው። በሁለት ጽንፍ ተፈርጀው ይተቻሉ። በአንድ በኩል “ለኦሮሞ ሕዝብ ማንነትና ታሪክ የታገሉ ምሁር” የሚሏቸው አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ “የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈታተኑ፣የባዕድ አገር የኤርትራ መሪ ኢሳያስ ፍላጎት አስፈጻሚ” በሚል ስማቸው ይነሳል። “ፖለቲካዊ ቅጥረኝነት” ለሚለው ብሂል ጥሩ ምሳሌ የሚባሉት ፕሮፌሰር መሐመድ ሀሰን ናቸው።
“የዲሲ ጉልቤ” ይሏቸዋል። በጋጠወጥነት ይታወቃሉ። ኡጋንዳ ብቻቸውን፣ አዲስ አበባ ደግሞ ከታማኝ በየነ ጋር እጅግ “ነወር” በተባለ ውስልትና ተይዘዋል። ሲናገሩ አይጠነቀቁም። የንግግር ወለምታ ዋና መለያቸው ነው። በአስመራ በኩል የዘሬ ያንዘርዝረኝ ዓይነት እንደሆኑ ይሰማል። አሁን አሁን አሜሪካ ሆነው ሻዕቢያ በውክልናና በራሱ ፋልጎት የተነሳ የሚያራምደውን የሚዲያና የትርምስ ቴክኒክ ኮሚቴ ይመራሉ። አኚህ ሰው የቀድሞው የግንቦት ሰባት ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ነዓምን ናቸው።
ሁለቱም የፕሬዚዳንት ኢሳያስን አገዛዝ የሚያመልኩ፣ የሚታዘዙና የሚያገለግሉ እንደሆነ በርካታ መረጃዎች አሉ። አሁን ላይ አቶ ነዓምን ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከፕሮፌሰሩ ጀርባ ያሉ ጉፍዳዮችን በማንሳት አብረዋቸው ለሚሰሩ እየገለጹ ነው። በተለይም በፕሮፌሰሩ ስድብ ለተማረሩ ሚዲያዎች በርካታ መረጃ እየሰጡ ነው።
መሀመድ ሃሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስን መጽሃፍ ያደራጁ፣ ያረሙ፣ መጽሐፉ አንባቢ እንዲኖረውና ታማኝ እንዲመስል ሙያዊ ቅመሞች ያከሉ ናቸው። ሰሞኑን “ይዋሻል፤ እሱ የሚለውና መሬት ላይ ያለው አይገናኝም” በሚል መገምገማቸውን ከአቶ ነዓምን አፍ የሰሙ አጫውተውናል። በሶማሌ ክልል የተጀመረው የፕሮፓጋንዳ ጦርነትም ከዚሁ ግምገማ በኋላ የተፈበረከ እንደሆነም የሚናገሩ አሉ።

ምሥራቅ ሐረርጌ የተወለዱት ፕሮፌሰር መሐመድ ሀሰን ሲፈልጉ ራሳቸውን ሶማሌ በማድረግ እንደሚያቀርቡ፣ ይህንኑም በይፋ እንደሚናገሩ የሚገልጹ “በምሁር ደረጃ የሃሳብ ግልሙትና የሚያጠቃው፣ ነወር ጌጡ” በማለት ይተቿቸዋል። በተለይም የሶማሌ ተወላጆች “ውሸታም” በማለት ይከሷቸዋል።
ፕሮፌሰሩ የኦሮሞ ጥናት ማኅበር (OSA) መሥራችና የቀድሞ ፕሬዚዳንት ናቸው። በጥናታቸውም ሆነ በተለያዩ ጽሁፎቻቸው “ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት የተመሰረተች ግዛት ናት” የሚለውን ትርክት በማራመድ ይታወቃሉ። እኚህ ምሁር ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር ግጣማቸው የተዋደደው በዚሁ እሳቤያቸው እንደሆነ ስለግንኙነታቸው የሚያውቁ ይናገራሉ።
የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን የትግል ጉዞ የሚተርከውን መጽሐፍ በማረም፣ በማስተካከል፣ መግቢያና መቋጫውን በማዘጋጀት ረገድ ትልቅ ሚና ያላቸው ፕሮፌሰር መሐመድ ሀሰን። ፕሬዚዳንት ኢሳያስን “በሕይወት ካሉ የአፍሪካ መሪዎች መካከል እጅግ አስፈላጊው መሪ” በማለት የሚገልጿቸው ደፋር ናቸው። “ምሁር ሳይሆኑ ፖለቲካዊ ቅጥረኛ” በማለት በበርካታ ኤርትራዊያን ሳይቀር ተነቅፈዋል።
በአሁኑ ወቅት “የታላቁ የአፍሪካ ቀንድ አንድነት (Great Horn of Africa Union)” በሚል ትርክት፣ ኤርትራን የቀጠናው ማዕከል አድርጎ የመሳል ስራ እየሠሩ የሚገኙት እኚሁ ፕሮፌሰር፣ ኢትዮጵያ አሁን በያዘችው መንገድ ከቀጠለች ይህ እሳቤ እውን ሊሆን ስለማይችል፣ ኢትዮጵያን ከውስጥ ማፍረስ በሚለው የኢሳያስ አጀንዳ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ተደርገዋል።
ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት /ኦነሰ ብሎ የሚጠራውን ኃይል “ትርፍራፊ” ከሚባለው የኦጋዴን ነጻ አውጪ ኃይል ጋር የማቀናጀት ኃላፊነትን ከፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ ጋር በመሆን መረከባቸውን ቀደም ባሉት ጊዜያት መዘገባችን ይታወሳል።
ሁለቱም ፕሮፌሰሮች ለዚሁ ፕሮጀክታቸው መሳካት ግብጽ፣ቱርክ፣ ኬንያና ሶማሊያ በተደጋጋሚ በመመላለስ ድርጅቶቹ ግንባር ፈጥረው በምስራቅ በኩል ጦርነት እንዲከፍቱ የማቀናጀት ስራ ሲሰሩ ቢቆዩም ምንም ውጤት ሊያስመዘግቡ እንዳልቻሉ በመጥቀስ “የሚያቀርቡት ሪፖርትና መሬት ላይ ያለው እውነታ የተለያየ ነው” በሚል መገምገማቸው ተሰምቷል።
በአሜሪካ የሻዕቢያ ወኪል ሆነው እየሰሩ ያሉት አቶ ነዓምን “አለቆች እየላኩብን እንጂ ይህንን ሰው አንፈልገውም” በማለት ሲናገሩ እንደተሰማው “በሶማሌ ክልል የሚጠበቀውና መሬት ላይ ያለው እውነታ የተለያየ ነው። እሱ የሚያቀርበው ሪፖርት ውሸት ነው” ብለዋል።
አቶ ነዓምን ለስራ ባልደረቦቻቸው “በሶማሌ ክልል ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ አልተቻለም። ፕሮፌሰር መሐመድ የሚመሩት እንቅስቃሴ ከእውሸት ሪፖርት የዘለለ ውጤት አላመጣም። ይህም ሳያንስ በሚቀርቡበት ሚዲያ ሁሉ ኢትዮጵያን አስመልክተው የሚሰጡት አስተያየት ስራችንን እያበላሸ ነው። እንዳንከለክለው የሚልኩት እነሱ [ሻዕቢያዎች] ናቸው” በማለት ለሚዲያ ባለቤቶች መናገራቸውን በቅርብ መረጃ የሚያገኙ ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቀዋል።
አቶ ነዓምን “በማንኛውም መንገድ ምርጫውን ማኮላሸትና ተአማኝ እንዳይሆን ማድረግ ዋናው ፕሮጀክታችን ነው” በሚል ከሻዕቢያ የተሰጣቸውን ወቅታዊ አጀንዳ በበላይነት የሚመሩ እንደሆነ ይታወቃል። አቶ ነዓምን ፕሮፌሰሩ ቀጣፊ መሆናቸውን ለሚዲያዎቹ መናገር የፈለጉበት ቁልፍ ምክንያት እንዳልገባቸው መረጃውን የሰሙ አስታወቀዋል።
“ተስፋ እንጂ የሚጨበጥ ነገር ማሳየት ያልቻሉ ናቸው” በማለት አቶ ነዓምን ሻዕቢያና የሻዕቢያ አለቆች ከፍተኛ ገንዘብ ቢመድቡም ውጤት ሊመጣ አለመቻሉን አመልክተዋል። መረጃውን ያጋሩ ወገኖች እንደሚሉት አቶ ነዓምን ፕሮፌሰሩን ማዘዝም ሆነ ማናገር የማይችሉ መሆናቸውን እያወቁ፣ ከኢሳያስ ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳላቸው እየተረዱ ይህን ጉዳይ በድፍረት መናገራቸው አስገርሟቸዋል። በቀጣይ ምን ሊገጥማቸው እንደሚችል ለማየት እንደጓጉም አመልክተዋል። እሳቸውን እንዲያስተናግዱ የሚታዘዙ ሚዲያዎች በሰውየው ስድብ መማረራቸውንም አመልክተዋል።
ፕሮፌሰር መሐመድ ሃሰን እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ የተገናኙበት የጋራ ነጥብ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የምትቀጥልበት አግባብ ላይ ያላቸው አፍራሽ እይታ እንደሆነ በተለያዩ ወቅቶች መዘገቡ ይታወቃል።
ፕሮፌሰር መሐመድ ሃሰን በውጭ አገር የሚገኙ የሚዲያ አውታሮች በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የሚያደርጉትን ተፅዕኖ በማስተባበር እና የፖለቲካ ትንታኔዎችን በመስጠት፣ የፕሬዚዳንት ኢሳያስን ቀጠናዊ ፍላጎት ከዲፕሎማሲያዊ ጫና ጋር እንዲጣጣም የማድረግ ሚና የተሰጣቸውም ለዚሁ ተግባር እንደሆነ ምስክሮች ይናገራሉ። በዚሁ መነሻ አቶ ነዓምን ያወጡት መረጃ ጆሯቸው ከደረሰ እሳቸውም ሊገመገሙ ይችላሉ።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስን “የስትራቴጂ ባለሙያ” ፕሮፌሰሩን ደግሞ “የሃሳብ ቀማሪ” ጥምረት እንደሚመስል የሚናገሩ፣ ኢሳያስ ጉልበትና ሎጂስቲክ ወይም ግብአት ሲያቀርቡ፣ ፕሮፌሰሩ ኢሳያስ ለሚያቀርቧቸው ማናቸውም ግብአቶች ማዕረጋቸውን በመጠቀም ህጋዊነት የማላበስ ስራ እንደሚሰሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ይገልጻሉ።
ፕሮፌሰር መሐመድ ሀሰን በአውሮፓና በአሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን በማንቀሳቀስና የኤርትራን መንግሥት አቋም ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከማሳወቅ አንጻር “ስውሩ የኢሳያስ አምባሳደር” የሚል ማዕረግ ያገኙ ታማኝ አገልጋይ ናቸው።
በውጭ አገር የሚገኙ የሚዲያ አውታሮች በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የሚያደርጉትን ተፅዕኖ በማስተባበር እና የፖለቲካ ትንታኔዎችን በመስጠት፣ የፕሬዚዳንት ኢሳያስን ቀጠናዊ ፍላጎት ከዲፕሎማሲያዊ ጫና ጋር እንዲጣጣም የማድረጉን ኃላፊነት የወሰዱት እኚህ ፕሮፌሰር፣ ግዳጃቸውን መወጣት የጀመሩት በ1990 ዎቹ ጀምሮ ሲሆን አሁን ድረስ ኢትዮጵያ ላይ መርዝ በመርጨት የኢሳያስ አንደበትና ቀለሃ ሆነው እየሰሩ ነው። ይህንኑ ጥይታቸውን የሚተኩሱት “ኢትዮጵያዊ ነን” በሚሉት እንደ እነ መሳይ መኮንኑ አንከር፣ ኢ.ኤም.ኤስ። ዘውዱ ሾው በመሳስለሁ ስማቸው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር አብሮ ከሚነሳ ሚዲያዎች አማካይነት ነው።
በኢህአዴግ ዘመን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በወቅቱ በነበረውን የኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና ለማሳደር የተለያዩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎችን ኤርትራ ያጠራቅሙ ነበር። ፕሮፌሰር መሐመድ ሀሰን ደግሞ አስመራ የከተሙት ተቃዋሚ ኃይሎች ተቀላቅለው ኃይል እንዲፈጥሩ ይሰሩ ነበር። ኦነግና ኦብነግን የማዋሃድ፣ የማቀናጀት ስራቸውን የጀመሩት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እንደነበር አስመራ የነበሩ ምስክሮች ያፋ የሚያደርጉት አሃቅ ነው።
ኢትዮጵያን የማዳን ትርክት
ፕሬዚዳንት ኢሳያስና ፕሮፌሰር መሐመድ ለሚያደርጉት ማናቸውም እንቅስቃሴ የሚሰጡት ምክንያት “ኢትዮጵያን ከከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካ ማዳን” የሚል ትርክት ነው። “ኢሳያስ ኢትዮጵያ የብሄር ፖለቲካ አይስፈልጋትም ሲሉ ትህነግን ይመክሩና ያስጠነቅቁ ነበር” ሲሉ አስመራ ደርሰው “ዝግኒ” ወይም ምስር ወጥ በልተው የተመለሱ ደጋግመው የሚናገሩት እንዲሁ ለዜና ማዳመቂያ ሳይሆን “ኢትዮጵያን ማዳን” የሚለውን ትርክት ለመሞሸር እንደሆነ ማስረጃ እያጣቀሱ የሚናገሩ ጥቂት አይደሉም።
ፕሮፌሰር መሐመድ ሀሰን በአውሮፓና በአሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን በማንቀሳቀስ ኢሳያስን የመለዐክ ክንፍ አልብሰው ለማቅረብ በሚከፈላቸው ሚዲያዎች ሌት ተቀን የሚያወሩት በዚሁ ትርክት የመፍጠር ስልት እንደሆነ ማስተዋል ልብ የሚለው እዚህ ላይ ነው።
የጀርመን ድምጽንና ቪኦኤን ጨምሮ በውጭ አገር የሚገኙ የሚዲያ አውታሮች በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የሚያደርጉትን ተፅዕኖ በማስተባበር እና የፖለቲካ ትንታኔዎችን በመስጠት፣ የፕሬዚዳንት ኢሳያስን ቀጠናዊ ፍላጎት ከዲፕሎማሲያዊ ጫና ጋር እንዲጣጣም የማደረግ ስራ የሚሰሩት ፕሮፌሰር መሐመድ፣ “ኢትዮጵያን ማዳን” የሚለውን በመርዝ የተለወሰ ኢትዮጵያን የሚፈረካክስ ትርክት ያዋለዱት በዚህ አካሄድ ነው።
ይህን በመርዝ የተለወሰ ትርክት ገና ከጅምሩ የተዋጉ ነበሩ። ፕሮፌሰር መሐመድ ሀሰንን እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስን “የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች” እንደሆኑ በማስረጃ እያስደገፉ ሲጽፉ የነበሩ አገር ወዳድ ምሁራን፣ ፕሮፌሰሩን “የኦነግን ርዕዮተ-ዓለም የሚቀርጹና የኤርትራ ቅጥረኛ” ይሏቸው ነበር።
በተቃራኒው የኤርትራ ድምፅ (Eri-TV) እና ሌሎች የውጭ አገር ድረ-ገጾች፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስን እንደ “የአፍሪካ ቀንድ ብቸኛ ራዕይ ያለው መሪ”፣ ፕሮፌሰር መሐመድን ደግሞ እንደ “ታላቅ የአፍሪካ ምሁር” አድርገው በማቅረብ “ኢትዮጵያን ማዳን” ለሚለው አውሬ ትርክታቸው ማስፈጸሚያ ትርክት ይገነቡላቸዋል።
“ኢትዮጵያዊ ነን” የሚሉ ሚዲያዎች እኚህኑ ሰው በማስተዋወቅ፣ በየጊዜው ተደጋጋሚ የአየር ሰዓት በመስጠት ተጠምደዋል። አሁን ላይ “ኢትዮጵያን ማዳን” በሚለው በመርዝ የተለወሰ ትርክት፣ ተሸሽገው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከየአቅጣጫው የተነሱትን ኃይሎችን የሚረዳውን፣ የሚደግፈውን፣ የሚያደራጀውን፣ የሚያስለጥነውን የፕሬዚዳንት ኢሳያስን አገዛዝና የላኪዎቻቸውን ፍላጎት እያስተናገዱ ነው። ሲያስተናግዱም “ኢሳያስ ኢትዮጵያን ይወዳሉ፤ ኢትዮጵያን ወደ መልካም መንገድ ያሸጋግራሉ” በሚል ነው። ይህን ሰምተው ግራ የሚጋቡ “እንደ ኤርትራ” ሲሉ ይጠይቃሉ፤
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






