ከረሃብተኞች ዘርፈው የኮበለሉት ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ “ለሐገርና ለሕዝብ ላደረጉት አስተዋፅዖ” በሚል ተሸለሙ

Date:

በቅርቡ ካቀጣጠሉት የብሄር ግጭት ማፈግፈጋቸውን ያስታወቁት ሻለቃ ዳዊት ወለደ ጊዮርጊስ “ለሐገርና ለሕዝብ ላደረጉት አስተዋፅዖ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ሽልማትና ዕዉቅና ተሰጥቷቸዋል” ሲል የዘገበው በቅርቡ ከአዲስ አበባ መዘገብ እንዳይችል የታገደውና በጀርመን አገር በጀት ለጀርመን ብሄራዊ ፍላጎት ማስጠበቂያ የተቋቋመው የጀርመን ድምጽ የአማርኛ ፕሮግራም ነው። ጣቢያው የሸላሚዎቹን ስም እንጂ ሽልማት ሰጪው ድርጅት ማን እንደሆነ ይፋ አላደረገም። ሽልማቱን የሰሙ ” ከረሃብተኞች ጉሮሮ 300 ሺህ ዶላር ዘርፎ የኮበለለ ከሃዲ መሸለሙ የዘመኑ ድንቅ ወግ ነው” ሲሉ መከራከራኢያቸውን አክለው ፅብታቸውን ልከዋል።

የጀርመን ድምጽ “ሻለቃ ዳዊት፣በዓለሙ ማኀበረሰብ ዘንድም ዕውቅና የተሰጣቸው ዲፕሎማት እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ከሃገር ከተሰደዱ በኋላ፣በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ስር ያሉ የተለያዩ ተቋማትን በመምራትና በማማከር አገልግሎት ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል” ሲል ለዜናው መግቢያ ሰርቶላቸዋል። የተጠቅመው ምስል ሻለቃ ዳዊት የክብር ዘብ ሰላምታ ሲቀርብላቸው የሚያሳይ ሲሆን እሳቸውም ሰማኒያዎቹን የዕድሜ ክልል እይተሻገሩ በመሆናቸውና በቤት አዝማድና መሰል ወዳጆቻቸው ተከበው በደስታ ሲፈነጥዙ ያሳያል።

“ዳዊት በከዳት ኢትዮጵያ የክቡር ዘበኛ መለያና በሸጣት ባንዲራ ስር የክብር ሽልማት ሲሰጠው ማየት አሳዛኝ ነው” በማለት ስሜታቸውን የገለጹ የሻለቃውን ሌብነት የሚያሳየውን መረጃ ያለበትን ጠንካራ ጽሁፍ ልከዋል። በጽሁፍ ሻለቃ ዳዊት ሆን ብለው ትምህርታቸውን አቋርጠው ደርግን በሲአይኤ መልዕክተኛነት ወደ አገር ቤት እንደገቡ ራሳቸው መናገራቸውን ይጠቅሳል።

“በኤርትራ ክፍለ-ሐገር አስተዳዳሪነት፣ በምክትል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትርነትና በዕርዳታ ማስተባባሪያ ኮሚሽነርነት ያገለገሉት ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርስ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ተሸለሙ” በማለት የዓለም ሚዲያዎች በምስልና በማስረጃ አስደገፈው የዘገቡትን የዝርፊያ ታሪካቸውን የዘለለው የጀርመን ድምጽ፣ በስም የጠራቸውን ሸላሚ ስለ ሚከሰሱበት ሌብነታቸው ምንም አላነሳባቸውም። ይልቁኑም ለሻለቃ ዳዊት ዕዉቅናና ሽልማቱን የሰጠዉ ኮሚቴ አባል አቶ ኃይልገብርኤል አያሌዉ ጠቅሶ፣ “ሻለቃ ዳዊት ለሐገርና ለወገን ያደረጉት አስተዋፅኦ አብነታዊ ነዉ።ሻለቃ ዳዊት ባሁኑ ወቅት የአፍሪቃ ጉዳይ አጥኚ ናቸዉ” ሲል አሞግሷቸዋል።

በዓለም ዘንዳ የተከበሩ ዲፕሎማት መሆናቸው ያስታወቀው የጀርመን ድምጽ፣ ዳዊት “በአሁኑ ወቅት፣በአፍሪቃ ደህነትና ፀጥታ ስጋቶች  ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ፣የአፍሪቃ ስትራቴጂና የጸጥታ ጥናት ተቋምን መስርተው፣በዋና ስራ አስፈጻሚነት እያገለገሉ ይገኛሉ” ብሏል። ተቋሙ የስለላ ስራ የሚሰራና ግጭት ባለባቸው የአፍሪካ አገራት ዳራውን የተከለ አገልጋይ ተቋም እንደሆነ የስራቸውን ፍሬ የሚያውቁ ይናገራሉ።  

ስለሽልማቱ ተጠይቀው ኤርትራ አስተዳዳሪ በነበሩበት ወቅት የሰው ልጆች መብት እንዲከበር መስራታቸውን አመልክተዋል። አክለውም የዕርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን ሆኜ መጨረሻ ላይ የሰራነው ስራ፣ የብዙ ሚሊዮን ህዝብ ህይወት አትርፈናል፤ብዙ ሚሊዮን ህዝብ ህይወት አድነናል። ይሄ የተመዘገበ ነው፣እሱ እኮራበታለሁ።” የሚል መልስ የሰጡት ሻለቃ ዳዊት ከረሃብተኞች ጉሮሮ ዘርፈው መኮብለላቸው በአገርና በዓለም የሚታወቁበት ትልቁ የሕይወታቸው ሆኖ ሳለ “እኮራለሁ” ማለታቸው የህሊናቸውን መደደር የሚያሳይ እንደሆነ ቅር የተሰኙት አመልክተዋል።

“የጀርመን ድምጽንና ሻለቃውን በባህሪና በተፈጥሮ እንዲሁም የባዕዳን አገልጋዮች” በማለት የፈረጁዋቸው እነዚሁ ወገኖች እንዲከሽፍ ታስቦ በተዘጋጀው መፈንቅለ መንግስት የኢትዮጵያ ምርጥ ጄነራሎች እንዲፈጁ ሻለቃ ዳዊት ሱዳን ድረስ በመምጣት ከሻዕቢያና ወያኔ ጋር ይሰሩ እንደነበር በራሳቸው አንደበት ማመናቸውን ጠቅሰው መናገራቸውን በማስታወስ “ከሃጂ በክብር መሸለም ግፍ በተሰራባቸው ጄነራሎች አስም ላይ እንደመደነስ፣ በረሃብ ጠኔ በተጎዱትና ችጋር በጠበሳቸው ምስኪን ዜጎች ስቃይ ማላገጥና መሳለቅ ነው” ሲሉ ክፉኛ ወቅሰዋል።

“ዳዊት ከሃዲና ዘራፊ መሆኑን ለማሳየት ከረሃብ ሰለባዎች ጉሮሮ መንትፎ አገር ስለመክዳቱ መግለጻችን ከተራ የጥላቻ ስሜት የተቀዳ አይደለም። ዳዊት ዘራፊ መሆኑንን፣ የዘረፈውም ረሃብ ከሚጠብሳቸው ዜጎች ጉሮሮ ላይ ስለመሆኑ በወቅቱ የቀረበውን ማስረጃ የተደገፈ፣ ያስጨፈጨፋቸው ጄነራሎችም አገር እስከወዲያኛው የማይተኩ፣ በውጤቱም ኢትዮጵያን ባህር አልባ፣ የዘር ፖለቲካ መፈልፈያ ያደረገውን አገዛዝ የተከለው በዚሁ ዛሬ ድረስ በስለላ እየሰራ ነው” የተላከው ማስታወXአ ከስር እንዳለ ቀርቧል።

ለንዛቤ ቢሆን የተሸለመው ዳዊት ይህን ይመስላል

የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አገዛዝ በደርግ በተወገደ ጊዜ በትምህርት ውጭ አገር የነበረው ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በራሱ አንደበት ሲናገር እንደተሰማው (የፒኤችዲ) ትምህርቱን አቋርጦ ወደ አገር ቤት መጣ። እርሱ እንደሚለው ትግሉን ለመቀላቀል ቢሆንም ዋናው ዓላማ ግን በደርግ ውስጥ በመግባት ለምዕራባዊ ኃይሎች ለመሰለል እንደሆነ የበኋላ ሥራው ይናገራል። እርሱ እራሱም ቢሆን ይህንን የሁለት ቢላዋ ጨዋታ ሊያስተባብል አይችልም። እንዲያውም በአንዳንድ ቃለመጠይቆች ሞቅ ሲለው እየዘላበደ እምነቱን ሰጥቷል።

ደርግ ውስጥ በመግባት የስለላ ተግባሩን የቀጠለው ዳዊት፤ በወቅቱ ደርግን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል አመቺ ሁኔታ ባለመኖሩና ወቅቱ የጎላ አገር ወዳድነት የሚንጸባረቅበት፣ እንደ ዛሬ የጎጥ አስተሳሰብ የነገሰበት ባለመሆኑ ደርግን የተቀላቀለበትን ዋና የማፍረስ ተግባሩን አዘገየው። በቀጣይም ወታደርነቱን ሳይገፋበት የኤርትራ አስተዳዳሪ፣ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ወዘተ የተለያዩ ሥልጣን ላይ ከቆየ በኋላ ኢትዮጵያን ለምዕራባውያን በሯን ወለል አድርጋ እንድትከፍት የሚያደርጋት ሤራ ዋና ጠንሳሽ ሆነ። ይህንኑ እንዲያመቻች “ወታደሩ” ዳዊት የዕርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ዋና ኮሚሽነር ተደረገ።

ይህም በሰው ሰራሽ ምክንያት የደረሰብን ችጋር አጉልቶ በዓለምአቀፍ መድረክ እንዲሰማ በማስደረግ በዕርዳታ ሰበብ ለምዕራቡ ዓለም በሯን ጥርቅም አድርጋ የዘጋችው ኢትዮጵያ በግድ እንድትከፍት ጫና ተደረገባት። “እምቢ” ብትል በዓለም ዓቀፉ መድረክ ክስ እንዲቀርብባት የሚያስደርግ እንደሚሆን በተሠራው ሥራ ውስጥ የዳዊት ሚና የጎላ ነበር። ከውጭ የሚመጡትን “የዕርዳታ ሰዎች” የሚያነጋግር ወደ ውጭ አገራት በመሄድ የሚወያይ፣ የሚዋዋል … ተደርጎ የተሾመው ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ሆነ። ራሱ በተለያዩ መድረኮች እንደተናገረው አየርላንዳዊውን ቦልጊዶፍን እና “We are the World” የዘፋኞች ቡድን እንዲመጣ በማስደረግ ትልቅ ድርሻ አለው።

በዳዊት ወልደጊዮርጊስ አጼ ዮሃንሳዊ ምሪት ምዕራባውያን ሰተት ብለው አዲስ አበባ ገቡ። ኢትዮጵያ ተበረበረች፤ ትህነግ እስካፍንጫው ታጠቀ፤ የዕርዳታ እህል እየሸጠ ጦር መሣሪያ እንዲገዛ ዕድሉ ተከፈተለት፤ እነ ቦብ ጊልዶፍ “አናውቅም” ቢሉም በድራማው ዋና ተዋናይ ሆኑ፤ የድራማው ዳይሬክተር ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ነበር። ሁሉም ሲጠናቀቅ ዳዊት ከችጋር ሰላባዎች ጉሮሮ 300ሺ የአሜሪካ ዶላር ዘርፎ ወደ “እናት አገሩ” አሜሪካ ኮበለለ። እዚያም ሆኖ የኮ/ሎ መንግሥቱን ስም በሚያጠለሽ መልኩ እርሱ የሌለበት ይመስል “የደም ዕንባ” የሚል መጽሃፍ አሳተመ፤ በእንግሊዝኛ ተተርጉሞ ለምዕራባውያን የፖሮፓጋንዳ ፍጆታ እንዲውል ተደረገ። ዳዊት በዓላማና በትዕዛዝ ሁሉንም ይፈጽም ስለነበር ልክ እንደ ዛሬው ያኔም የትህነግ ህጻናትን በጦርነት የመማገድ ወንጀል ዝም ተባለ።

ኮ/ል ጎሹ ወልዴ ሳንቲም ሳያጎድሉ፤ የውሎ አበላቸውንና የመመለሻ ቲኬታቸውን ወደ አገርቤት በመመለስ አሜሪካ በስደት ለመኖር ሲወስኑ (በወቅቱ ቪኦኤ ላይ ቀርበው ተናግረዋል) ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ግን 300ሺህ ዶላሩን ከረሃብተኛ ሕዝብ ጉሮሮ ላይ ዘርፎ የተንደላቀቀ ኑሮውን በአሜሪካ ጀመረ። ለቀጣይ የሤራ ፖለቲካም ራሱን አዘጋጀ። 

በግንቦት ወር 1980ዓም ወታደራዊ መኮንኖች መፈንቅለ መንግሥት ሲያቅዱ የውጭውን ሤራ ሲመራ የነበረው ዳዊት ራሱ እንደነበር በተደጋጋሚ ሲናገር የነበረው ሃቅ ነው። እስከ ሱዳን ድረስ በመምጣት ከሻዕቢያ፣ ከትህነግና ከኦነግ መሰል ድርጅቶች ጋር ተደራድሮ፣ ሰነዶችን ፈርሞ የሄደው ራሱ እንደሆነ በአንደበቱ መስክሯል። ይህ መፈንቅለ መንግሥት እንዲከሽፍ ካስደረጉትና ኮ/ሎ መንግሥቱ በዕልህ ተነሳስተው ጄኔራሎቹን ገድለው የጦሩ ሞራል እንዲላሽቅ፤ በቀጣይም ትህነግ (ወያኔ) ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገው ጉዞ የጽጌረዳ ምንጣፍ የተነጠፈበት እንዲሆን በማስደረግ የዳዊት የውጪ ሚና እጅግ የጎላ ነው። መፈንቅለ መንግሥቱም ከሽፎ የቀረው ዓላማው መንግሥቱን ፈንቅሎ ነጻነት ለሕዝብ ለማምጣት ሳይሆን ኤርትራን ለማስገንጠልና ኢትዮጵያን ለምዕራባውያን አሻንጉሊትና ተላላኪ ለሆነው ትህነግ አሳልፎ ለመስጠት ነበር።

ትህነግ በኢትዮጵያ በየቦታው የቀበረውን ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ የብሔር (የዘውግ) ቦምብ ምን እንደሆነ እያወቀ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ የመሸጋገሪያ ዕቅድ ብሎ ያቀረበው አንዱ ሃሳብ “በብሔር ላይ የተመሠረቱ ድርጅቶችን በሙሉ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይሠሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዋጅ ማገድ አለባቸው” የሚል ነበር። ይህንን ረቂቅ በየዋህነት የተቀበሉ የዛሬ ሦስት ዓመት ጀምረው “የሽግግር ሮድማፕ (ፎኖተካርታ)” በሚል አገሪቱን የሚያፈራርስ ዕቅድ ይፋ አድርጎ ነበር።

ዳዊት ከሃዲና ዘራፊ መሆኑን ለማሳየት ከረሃብ ሰለባዎች ጉሮሮ መንትፎ አገር ስለመክዳቱ መናገራችን፣ የዘረፈውም ረሃብ ከሚጠብሳቸው ዜጎች ጉሮሮ ላይ ስለመሆኑ በወቅቱ የቀረበውን ማስረጃ ማተም አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። ለታሪክም ይቀመጥ ዘንድ፣ ሸላሚዎቹም ማንነታቸውን ይመረመሩበት ዘንድ ይረዳቸዋል።

የዛሬ 35 ዓመት ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ከነበረበት የዕርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሸን ስራው በመጠናቀቁ ለቅቆ አሜሪካን አገር የ”አስጠጉኝ” ጥያቄ አቅርቦ ነበር። በወቅቱ ከማይታወቀው ሌብነቱ በተጨማሪ በርሃብ ከተጠበሱ ዜጎች ጉሮሮ በቁጥር የተገለጸ የዕርዳታ ገንዘብ ዘርፎ ወደ አሜሪካ እንዳሸሸ በወቅቱ ተዘግቧል።

ዳዊት ዘረፈ ስለተባለውና ገንዘብ በወቅቱ በታተመው የአሶሺዬትድ ፕሬስ ዘገባ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። በወቅቱ ጥቂት ነገር ከመናገር ሌላ ስለ ገንዘቡም ሆነ በውጭ አገራት ስለገዛቸው የግል መኖሪያ ቤቶች በማስረጃ ወይም አሳማኝ በሆነ መልኩ ሲያስተባብል አልተሰማም። ሊያስተባልም አይችልም። አሶሺዬትድ ፕሬስ ያነጋገራቸው የዳዊት የቅርብ ሰው ዳዊት በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ጠቅላይ ግዛትና በእንግሊዝ አገር ሎንዶን የግል መኖሪያ ቤት እንዳለው መስክረውበታል። እንግዲህ ይህን ሰው ነው ኮተታቸውን ሰብስበው በቤተሰብ ጉባኤ ይዘት ባለው ድግስ የምስጋና ሽልማት የሰጡት። ይህን የምታነቡ ኢትዮጵያዊያን፣ ጉዳዩ ያገባናል ካችሁ የሸላሚዎቹንም ማንነትና ስብዕና ፈትሻችሁ የድርሻችሁን እንድትሉ ይሁን።

ዳዊት በተለያዩ ጊዜያት በራሱ አንደበት እንደተናገረው በ1980 የተደረገውን መፈንቅለ መንግሥት ካከሸፉት ተባባሪዎቹ አንዱ ቁምላቸው ደጀኔ በድብቅ ከአገር ወጥቶ አሜሪካ ጥገኝነት በጠየቀበት ጊዜ ዳዊት ቤት ተቀምጦ እንደነበርና እንደረዳው አስረድቷል። የዚህ ሁሉ ገድል ባለቤት ነው እንግዲህ ዛሬ “አገር ካልመራሁ” በሚል የዘረፈውን እየረጨ በሚዲያ በተለይም ባለሃብቶች ስም ሻዕቢያ ስፖንሰር በሚያደርገው የመረጃ ቴሌቪዥን፣ እንዲሁም በበርካታ አውዶች ጨምሮ የርስ በርስ እልቂት ክተተ ሲያውጅና ሲያሳውጅ የነበረው ዳዊት ነው የተሸለመው።

የዛሬ 40 ዓመት በዳዊት ወልደጊዮርጊስ ላይ የወጣው የዜና ዘገባ ከዚህ በታች ይገኛል።

Ethiopia Says Former Aid Chief Fled to United States with Money

JAMES R. PEIPERTMay 7, 1986

NAIROBI, Kenya (AP) _ Ethiopia said its top relief official during the 1984-85 famine has fled to the United States with at least $300,000 in famine aid money.

In Washington, the State Department on Wednesday confirmed that Dawit Wolde Giorgis was in the United States. Deputy spokesman Charles Redman had no comment on whether Dawit had sought political asylum.

A Voice of America official said Dawit was in New York where he told VOA by telephone there was no foundation to Ethiopian government charges that he had ″betrayed his country and exchanged his dignity for personal gain.″

The VOA official, Brian McClure, said the conversation with Dawit did not go beyond the denial and that Dawit declined an on-the-record interview.

The accusations against Dawit, who headed the Relief and Rehabilitation Commission, was made in a lengthy statement in the Amharic language late Tuesday by Ethiopia’s state-run radio. An English version of the statement was broadcast Wednesday and monitored in neighboring Kenya.

Asked about the allegations against Dawit, Redman said extensive U.S. government monitoring shows ″no indication any U.S. assistance has been diverted.″

The radio announcement was the first official acknowledgement that Dawit had defected. He was last heard of on Oct. 25, when he left Ethiopia for Europe and the United States to solicit famine relief funds.

Western diplomats and Ethiopian and foreign relief officials in Ethiopia generally assumed late last year that he had left for good and was in the United States. Last December, however, the State Department said no asylum request had been received.

The broadcast indicated Dawit was in the United States, referring to ″those like him who are living in luxury in the cities of America.″

An acquaintance of Dawit told The Associated Press last December in Addis Ababa, the Ethiopian capital, that Dawit had homes in California and London. Other sources said he settled in Santa Barbara, Calif.

Dawit’s defection was considered a severe embarrassment to the Ethiopian government. He had been an army major, a senior government figure and a close friend of the country’s military leader, Mengistu Haile Mariam.

The Ethiopian government statement said Dawit, a bachelor in his mid-40s, had ″engaged in personal profiteering at a time when every minute had to be used in the campaign to save lives.″

It said the embezzled funds included $300,000 from a Relief and Rehabilitation Commission bank account in New York, and that Dawit had distributed thousands of dollars to relatives in California and Maryland.

For two years Dawit was head of the commission, the main government agency coordinating the international famine relief operation. He was known internationally for his impassioned pleas for aid to his drought-stricken nation, where it was estimated that famine affected 8 million of its 42 million people.

″The money stolen by Dawit was stolen from the mouths of hungry infants, mothers and elderly citizens of Ethiopia,″ the government statement said.

″He misappropriated funds allotted to the work of saving the lives of our compatriot children and youth who were on the brink of death, thereby committing an act which will never be forgiven by history, and has fled from the country after betraying it.″

The government has never officially estimated the death toll in the famine. But relief officials have said privately they believe about a million Ethiopians died.

The statement called Dawit ″an urgently wanted criminal″ and an ″enemy of the people.″ It said that ″those who stand for justice and truth will cooperate with us in bringing him to punishment.″

When Dawit left Ethiopia last October, the itinerary for his fund-raising mission was not announced. But sources in Addis Ababa, including diplomats and relief officials, said he went to Britain, Belgium and the United States. They said his last contact with the Ethiopian government was from Brussels, the Belgian capital.

The sources said one of Dawit’s brothers defected to the United States last September.

The government statement said Dawit had arranged for commission bank accounts to be set up in foreign cities, including New York and London, for deposit of aid donations.

″The money deposited in the commission’s foreign bank accounts was then pocketed by the traitor,″ it said.

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኃይሌ ገብረስላሴ “አረቄን እጠቀም ነበር” በማለቱ ዕግድ ተጣለበት፤ እግዱ ለዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ማህበራት ተበትኗል

አዲስ ሪፖርተር - አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አረቄን ከዶፒንግ ጋር...

“የኢትዮጵያዊያ መከራ የሆነውን ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያና ትግራይ ምድር መንቀል ዋና ዓላማችን ነው”

አዲስ ሪፖርተር - እስካሁን በመላው ኢትዮጵያ ለተፈጠሩ ምስቅልቅሎች፣ በትግራይ...

የአማራ ክልል የወሲባዊ ጥቃት አሳስቧል፤ “በማንና እንዴት ይፈጸማል? ለሚለው በጥናት የተረጋገጠ መረጃ የለም” ጤና ቢሮ  

አዲስ ሪፖርተር - በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ጦርነትና...

በሻዕቢያና ህወሃት መካከል አለመተማመኑ ሰፍቷል፤ የሚታወቁ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ከእነ ሞንጆሪኖ ቡድን እየወጡ ነው

ስጋት ትልቁ ምክንያት ነው። ሻዕቢያ በተግባር የተፈተሸ ከሃጂ በመሆኑ...