ጃዋር “ከመምህራን ማሕበር ጋር በታህሳስ ወር አመጽ ለማስነሳት ተስማምተናል” ማለቱን ማሕበሩ ነቀፈ፤  

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ጃዋር መሐመድ በታህሳስ ወር ከኢትዮጵያ መመህራን ማህበር ጋር በመተባበር አመጽ ለማስነሳት በሚስጢር ስምምነት ላይ መደረሱን አስመልክቶ ያሰራጨው መረጃና ይህንኑ  ለማስፈጸም አስፈላጊ በጀት መዘጋጀቱን አስመልክቶ ማህበሩ ምንም ነገር እንደሌለ አስታወቀ።  ይልቁኑም ማህበሩ ከመንግስት ጋር በበርካታ ጉዳዮች እየሰራ መሆኑን ነው ያመለከተው። ጃዋር ይህን ያለው በስሩ ላሉት ተልዕኮ አስፈጻሚዎቹ በሚስጢር እንዳሰራጨ ሪፖርት ባቀረበበት መድረክ ላይ ነው።

“ከመምህራን ማህበር ጋር ስምምነት መደረሱ ሌሎች አደረጃጀቶችን በተለይ የሰራተኛ ማህበራት ተወካዮችን ስለሚያነቃቃ መረጃው በሕዝቡ ውስጥ በስፋት በወሬ ደረጃ እንዲሰራጭ በተላለፈውና በተላከው በጀት መሰረት ስራ እየተሰራ ነው” በማለት ጃዋር ማህበሩን በመጥቀስ በታህሳስ ወር አድማ ለማስነሳት ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ሪፖርት ባቅረበበት ስብሰባ ላይ የተገኙ ናቸው መረጃውን ለአዲስ ሪፖርተር የላኩት።

ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ ለአዲስ ሪፖርተር ፤ምላሻቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሐንስ በንቲ፣ “ጃዋር መሐመድ ስለተናገረው ንግግር ሆነ ዕቅድ የሰማነውም ፤ የምናውቀው ምንም ነገር  የለም፤ በሌለ ነገር ምላሽ መስጠት አይቻልም” ሲሉ ዜናው እንዳስፈገጋቸው አመልክተዋል።

ማኅበሩ ከየትኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ወገንተኝነት ነፃ የሙያ ማህበር መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ዮሐንስ፣ መረጃውን ከአዲስ ሪፖርተር መስማታቸውን በማመልከት የጃዋርን ምኞት አጣጥለዋል። አክለውም ማህበራቸው “ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና ልማት አጀንዳ ገለልተኛ ልንሆን አንችልም” ብለዋል።

የሀገር ሉዓላዊነትንና የቀይ ባሕር ጉዳይን እጀንዳቸው አድርገው እንደሚይዙ ያስታወቁት የኢትዮጵያ መመሕራን ማህበር ፕሬዚዳንት፣ ከመንግስት ጋር “በከፍተኛ ደረጃ” ባሉት አግባብ አብረው እየሰሩ መሆናቸውን አስታወቀዋል።

በደሞዝ፣ በጥቅማ ጥቅሞችና በመብት ዙሪያ ከመንግስት ጋር በትኩረት እየሰሩ እንደሆነ ያመለከቱት ዶ/ር ዮሐንስ፣ ልማትን የሚደግፉት እንደ ዜጋ የልማቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በአመክንዮ ስለሚረዱ እንደሆነ አመልክተዋል።

“ እኛ” አሉ ፕሬዚዳንቱ “ እኛ የሙያ ማህበር ነን፣ የማናስበውም እንደ ሙያ ማህበራችን በአመክንዮና በምክንያት ነው። በዚሁ አግባብ ሚናችንን ጠንቀቀን እናውቃለን”

ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም መመህራን ማሕበር የስራ አስፈጻሚ አባል በመሆን አፍሪካን ወክለው የተመረጡት ዶክተር ዮሐንስ፣ ጠብመንጃ ያነሱ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡ የሚመሩት ማሕበር እምነትና ፍላጎት ሲሆን በዚህ ረገድ አበክሮ እንደሚሰራም አመልክተዋል።

“በአገሪቱ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ድርድር እንዲመጡ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር በቅርበት እየሰራን እንገኛለን” ብለዋል። አክለውም በየትኛውም ሁኔታ ግጭት እንደ አገር የሚመረጥ ባለመሆኑ ማህበራቸው በዚህ አግባብ ሰላም እንዲሰፍን እንደሚሰራ አመልክተዋል።

ቀይ ባህርን አስመልክቶ “አጀንዳው የመንግሥት ሳይሆን የሕዝብና የአገር ነው”  ያሉት ዶክተር ዮሐንስ፣ “ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም አንፃር ገለልተኛ መሆን አንችልም” ሲሉ በድጋሚ የማህበራቸውን አቋም አስታውቀዋል። ማኅበሩ የተቋቋመበት ዓላማም ፣የሚመራበት መንገድ ፣በሳይንሳዊ እና ሙያውን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሆነም አስገንዝበዋል።

ጃዋር የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር በህዳር ወር በኢትዮጵያ አመጽ ለማቀጣጠል አስፈላጊውን ውይይት በማድረግ መስማማቱን፣ ለዚሁም በቂ በጀት መመደቡን አለኝ በሚለው መዋቅር ማስተላለፉን፣ ይህም በስፋት እንዲወራ፣ በተዋረድ ጊዜው ሲደርስ ሚዲያዎች እንዲቀባበሉት እንደሚደረግ ገልጾ አጀንዳ ማሰራጨቱን አዲስ ሪፖርተር የሰማችው ይህንኑ መመሪያ ሰምተናል ካሉ ምልምሎቹ ነው።

የሕክምና ባለሙያዎችን አመጽ እንደሚመራ ሲያስታውቅ የነበረው ጃዋር በዓመቱ መጀመሪያ ትምህርት ቤት ሲከፈት ዓመጽ እንደሚጀመር በክረምቱ መገባደጃ ላይ አስታውቆ እንደነበር አይዘነጋም።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related