የዓለም አቀፉ ቀይመስቀል ኮሚቴ በሰሜን ወሎ ያካሄደውን ቅኝቱን ሪፖርት አደረገ፤ ቡድን ለይቶ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም

Date:

Adisreporter – በወልደያ የተለያዩ በሮችን ጨምሮ በሰሜን ወሎ ዞን ባለፉት ሳምንታት ጦርነት መካሄዱ በተለያዩ መገናኛዎችና ማህበራዊ አውዶች ሲዘገብ ሰብቷል። ይህንኑ ጦርነት ከራስ የፖለቲካ ፍላጎት ጋር በማያያዝ በሰበር ዜና “ፋኖ ድል አደረገ” በሚል የዘገቡ ጥቂት አለነበሩም።

በሌላ በኩል ደግሞ ከፕሪቶሪያው የሰላም አማራጭ ስምምነት በሁዋላ ለማየት የሚከብድ የታጣቂዎች አስከሬን በቴሌግራም ገጾቻቸው በማሰራጨት ” የፋኖ፣ ትህነግና ሻዕቢያ የጥምረት ዘመቻ በዚህ መልኩ ከሽፏል” በሚል የመንግስት ደጋፊ መሆናቸው በሚታወቅ የማህበራዊ ሚዲያ አውዶች በስፋት ሲሰራጭ ተስተውሏል።

የፋኖ፣ ትህነግና የሻዕቢያ ልሳን ሚዲያዎች እንደሆኑ የሚታወቁ በርካታ ወታደሮች መማረከቸውን በመግለጽ የድል ዜና ማቅረበባቸውን እያሰሙ ሲሆን፣ አሁንም ከመንግስት ወገን የሆኑት፣ እንዲሁም የዞንና የወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤቶች መግለጫ በማውጣት ሌሎች ወገኖች የሚያወጡ መረጃ ሃሰት መሆኑን ሲያስታውቁ ከርመዋል።

በዚህ መካከል ነው የዓለም ዓቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ወደ ሰሜን ወሎ ዞን አቅንቶ ሪፖርት ያሰራጨው። በሪፖርቱ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በመንግሥትና በፋኖ ኃይሎች መካከል ውጊያ መባባሱን ያስታወቀው። ሪፖርቱን ተከትሎ መንግስት የዓለም ዓቀፍ ቀይ መስቀል ወደ ስፍራው እንዲገባ መፍቀዱ ከሽንፈት ወይስ የሚወራው ሁሉ በሶስተኛ ወገን ይፋ እንዲሆንለት ፈልጎ? የሚል መነጋገሪያ አስነስቷል።

ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች በሰሜን ወሎ አለ የሚባለው ውጊያ የሚነገርለትን ያህል አይደለም። የአካባቢው የመንግስት መዋቅሮችም ይህንኑ ይደግሙታል። የዓለም ዓቀፉ ቀይ መስቀልም ቢሆን አስራ ስድስት የመንግስት ቁስለኛ ወታደሮችን መረከቡን ከመግለጹ ውጪ ሲባል በነበረው ደረጃ የሚለካ ወይም የሚቀራረብ መረጃ አልሰጠም።

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና ከተማ የሆነችውን ወልዲያን ለመያዝ ለቀናት የዘለቀ ትንቅንቅ እንደነበር ነዋሪዎች ለቢቢሲ መናገራቸው ይታወሳል። ይህንኑ ዘመቻ ተከትሎ የመንግስት ደጋፊ አክቲቪስቶች ሙከራው እንዴት እንደከሸፈ በምስል አስደግፈው መረጃ አሰራጭተውም ነበር።

በሰሜን ወሎ ዞን ዋና ዋና ከተሞች ለአንድ ሳምንት ቅኝት ያደርገው የዓለም ዓቀፉ ቀይ መስቀል ቡድን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ፣ምርኮኞች መያዛቸውን እና ከባድ የሰብዓዊ ጉዳት መድረሱን በደፈናው ከማስታወቁ በዘለለ፣ በጠቀሰው ልክ ጉዳት ደረሰባቸው ያላቸውን ወገኖች ኮሚቴው አላብራራም። ስም ወይም የተኛው ወገን እንደተጎዳ ላይቶ አልገለጸም። በግጭቱ የተጎዱት ሰላማዊ ሰዎች ስለምሆናቸውም ያለው ነገር የለም።
ዓለም ዓቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ዓርብ መስከረም 30/3018 ዓ. ም. አመሻሽ ላይ ያወጣው መግለጫ በአካባቢው የተካሄደውን ግጭት የጠቀሰው በዚህ መልኩ ሲሆን፣ ከየትኛው ክፍል እንደሆኑ ሳያስታውቅ የቆሰሉ ለተሻለ ሕክምና እንዲላኩ መደረጉን ሲያስታውቅ አስራ ስድስት የመንግስት የጸጥታ አካላትን መቀበሉን ይፋ አድርጓል። እነዚህ ቁሰለኞችና በሪፖርቱ ተጎበኙ የተባሉት ቁጥራቸው ያልተገለጸ ምርኮዎች በአንድ ተነጥላ በተቀመጠች ምድብ ላይ በድንገት በተደረገ ጥቃት የተማረኩ መሆናቸው የተነገረላቸው ሊሆኑ እንደሚችል ግምት የሰጡ አሉ።

ሰሞኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተባበሩት መንግስታት ደርጅት ዋና ጸሃፊና አግባብ ላላቸው አካላት ባሰራጨው ደብዳቤ ወልዲያን ለመያዝ በተደረገው ጦረነት የፋኖ ተዋጊዎች ብቻ ሳይሆኑ የትህነግና የኤርትራ ኃይሎች መሳተፋቸውን ማስታወቁና ማስጠንቀቁ አይዘነጋም።

የድርጅቶቹ ደጋፊዎች ከየአቅውጣጫው ሶስቱ ኃይሎች በቅንጅት በውጊያው መሳተፋቸውን በይፋ ማስታወቃቸው፣ በድሮን በተደረገ ማጥቃት ሲያመልጡእ የተያዙ መኖራቸውን ጠቅሰው በምስል በማስደገፍ የዘገቡም እንደነበር አይዘነጋም።

“መንግስት በድሮን የሚያካሂደውን ጦርነት ያቁም” ከሚለው ዘመቻ ጀምሮ የተለያዩ ተቃውሞዎችን ማሰማት የጀመሩት የመንግስት ተቃዋሚ ሚዲያዎች፣ በሰሜን ወሎ ዞን ብቻ ሳይሆን በመላው አማራ ተደራራቢ ድል እያስመዘገቡ መሆኑን እየገለጹ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ክልሉ የዕለት ተለት ስራውን ያለምንም መስተጓጎል እየሰራ መሆኑን እየገለጸ ነው።

የዓለም ዓቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የላሊበላ ቡድን የሚመሩት ማርቲን ታልማን በግጭቱ “ክፉኛ” ከተጎዳው ኩልመስክ እና ሙጃ አካባቢ ሲመለሱ “ባለፉት ቀናት በሰሜን ወሎ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል አሊያም ቆስለዋል” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ በዝርዝር የተጎጂዎቹን ውገን ለይተው ያሉት ነገር የለም።

በላሊበላ፣ ወልዲያ እና በአካባቢው ለስድስት የጤና ተቋማት የድንገተኛ ሕክምና እርዳታ መስጫ ቁሳቁስ ማቅቡን የገለፀው ኮሚቴው፤ ከባድ ጉዳት ለደረሰባቸው 250 ሰዎች የቀዶ ጥገና እና የሕክምና እርዳታ መስጠት የሚችል ድጋፍ ማቅረቡን ተናግሯል። ጉዳት የደረሰባቸው 250 ያህሉ ሰዎች ማንነትና ከየትኛው ወገን እንደሆኑ አልተብራራም።

መስከረም 28፤ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አባላት በሰሜን ወሎ በፋኖ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ናቸው የተባሉ ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ እስረኞችን እንደገጎበኙ የኮሚቴው አባላት አስታውቀውቃል።

የፋኖ ልሳኖችም በርካታ ከማለት ውጭ በቁጥር አንድ ሁለት ብለው የጠቀሱት ቁጥ የለም። በተመሳሳይ የምርኮ ዜና የመንግስት ደጋፊ አክቲቪስቶች በምስል አስደግፈው የተገደሉ የፋኖ አመራሮ፣ የተማረኩ የሻዕቢያን የትህነግ ወታደሮችን ምስል አሳይተዋል።

የዓለም ዓቀፉ ቀይም መስቀል ኮሚቴ አባላት ምንም ይሁን ምን ለጦር ምርኮኞች አስፈላጊው ድጋፍ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው አሳስበዋል። የሰብአዊ መብታቸውም ሳይጣስ በወጉ እንዲያዙ ብለዋል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእናት ሀገር ጥሪ ተሳትፎና ኮሎኔል መንግሥቱ

የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ...

ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ፤ ኢትዮጵያን ወደ መፃኤ ዘመን የሚያሻግር የሎጂስቲክስ አብዮት

ኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ ሰማይ ስር የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ካርታዋን እንደገና ለመሳል...

“ጥርስ የሌለው ውሻ” የሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም መፃኢ እጣፈንታ

አዲስ ሪፖርተር - ፕሬዛዳንት ትራምፕ አሜሪካን ከተባበሩት መንግስታት ደርጅት...

በዘመነ ትራምፕ ጫና ውስጥ የወደቀችው ሶማሊያ እና ለሶማሌ ላንድ ተስፋን ያለመለመው አዋጅ

አዲስ ሪፓርተር - ከሶማሌላንድ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና ከእስራኤል እውቅና...