በትግራይ ለፓለቲካ ጥቅም ሲባል ተፈናቃዮች ላይ የሚደርሰው እንግልት እንዲቆም የሚጠይቁ ስልፎች ተካሂደዋል።
በትግራይ ክልል ትህነግ ከኤርትራ መንግስትና ፋኖ ጋር በመጣመር ለጦርነት ራሱን እያዘጋጀ መሆኑ በየአቅጣጫው እየተሰማ ባለበት፣ የትህነግ አመራሮች፣ የትህነግና የሻዕቢያ ልሳን ሚዲያዎችና አክቲቪስቶች ይህንኑ አይቀሬ የሚሉት ጦርነት እንደሚጀመር ምልክት እየሰጡ ባለበት ወቅት የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች ያደራጁትና የመሩት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ መካሄዱ እያነጋገረ ነው።
ትናንት የተጀመረውና ዛሬ የቀጠለው የሰላማዊ ሰልፍ፣ ከመኖሪያ መንደራቸው የተፈናቀሉና በመጠላይ ጣቢያዎች በከፋ ችግር እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖች ላይ የሚደርሰው እንግልት እንዲቆም፣ እነዚህን ወገኖች ለፖለቲካ ፍላጎት ማስፈጸሚያነት መጠቀም እንዲያበቃ በገሃድ መጠየቁን ሰልፉን የተከታተሉ የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪዎች አመልክተዋል። ትህነግ ተፈናቃዬች ተመልሰው ወደ መንደራቸው እንዲገቡ እንደማይፈቅድ በገሃድ መናገሩ አይዘነጋም። መጀመሪያ ትህነግ አካባቢውን ያስተዳድር የሚል አቋም ነው ያለው።
በትናንትናው ዕለት የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ውጤት ለህዝብ ሳይገለጽ፣ ዛሬ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከምስራቅ አቅጣጫ ወደ መቀለ ከተማ የሚያስገባው ዋና አውራ ጎዳና ከማለዳ ጀምሮ መዘጋቱ ታውቋል። ታጣቂ ኃይሎቹ ኣጉላዕና ጉርመዶ በሚባሉ ሁለት አቅጣጫዎች መንገዶቹን በመዝጋታቸው የተነሳ የትራፊክ መስተጓጎል መፈጠሩን ከስፍራው የወጡ ምስሎች አረጋግጠዋል። በስፍራው የሚገኙትን በማነጋጋር የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ አረጋግጧል። መንገዶቹ ስለመከፈታቸው ግን ማረጋገጫ አላገኘም።
ሰለፈኞቹ “በትግራይ ክልል ጦርነትና ግጭት መካሄዱን ተከትሎ ከቀዬቸው የተፈናቀሉ በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎች እየደረሰባቸው ያለውን በደልና መከራ በቂ ምላሽ እየተሰጠው አይደለም” ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል። ሰልፍ ለማድረግ ያነሳሳቸው ችግራቸውን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው አካላት በቂ ምላሽ ባለመሰጠቱ እንደሆነ አመልክተዋል።
የተቃውሞውን ሰልፍ ያካሄዱት በአመዛኙ የትግራይ ሰራዊት ኃይል በምህፃሩ TDF በሚል ራሳቸውን የሚጠሩና በቀደሙት ዓመታት በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ዋና ተሳታፊ የነበሩ ናቸው። በሰልፉ ላይ እንደታየው ትጥቅ አንግበውም ነበር።
ሰልፈኞቹ፣ ከፕሪቶርያ ስምምነት በኃላ ትጥቃቸውን ፈትተው በተዘጋጀላቸው ማቆያ እንዲሰፍሩ ከተደረገ በኃላ በርካታ ጥያቄዎች ሲያነሱ መቆየታቸውን የሚታወስ ሲኾን ችግሮቻቸውን ለቀድሞ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አቅርበው እንደነበር አይዘነጋም።
ይሁንና ቃል የተገቡላቸው የካሳና ጥቅማጥቅም ጉዳዮች እንዲኹም ተያያዥ ጥያቄዎች እልባት አልተሰጣቸውም በሚል በመቀለ ከተማ አጠር ላሉ ሰዓታት የተቃውሞ ድምፅ አሰምተዋል።
በከተማዋ የተሰማውና በሰልፉ ላይ ከቀረቡ አንገብጋቢ ናቸው ካሏቸው ርእሰ ጉዳዮች መካከል ተፈናቃዮች ተገቢውን መልስ እንዳልተሰጣቸው የሚገልፁና ለፓለቲካ ዓላማ ሲባል የሚከፈለውን አላስፈላጊ ዋጋ ከወዲኹ እንዲገታ የሚጠይቁ መሆናቸውን ታውቋል።
የሰልፉ አስተባባሪዎች እንደገለፁት ትህነግ፣ በኤርትራና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል እየሰፋ የሄደው መካረር ወደ ጦርነት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት አሳድሮባቸዋል። ትግራይ ዳግም የጦርነት ማዕከል እንዳትሆን የሚመለከታቸው ሁሉ ቆም ብለው እንዲያስቡ ጠይቀዋል።
ትህነግና ሻዕቢያ በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ሰበብ ወታደራዊ ጥምረት መፍጠራቸው፣ ሰሞኑን በተጠናቀቀው ኮንፍረንስ ላይ ኤርትራ መሳሪያ እንደሰጠቻቸው ራሳቸው የትህነግ መሪዎች መናገራቸው የሚታወስ ነው።
በመቀለ ከተማ የተካሄደው ይኸው ሰልፍ ሙሉ በሙሉ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ፍራቻ መኖሩን ከማስታወቁ በተጨማሪ፣ ትግራይን ወደ ሰላም እንድትመለስ ማሳሰቢያ የተላለፈበት ነው። ይህንኑ ፍላጎታቸውን “ሰላምን እንሻለን” በሚል ድምጽ ሰልፈኛቹ በተደጋጋሚ ሲያጸኑ ተሰምተዋል።
በተጨማሪም፣ በክልሉ በነበረው ጦርነት በትጥቅ ትግል የተሳተፉ እነዚሁ የትግራይ ታጣቂ ኃይል አባላት “የኛን ጥያቄ መመለስ የማይችል አመራር የሌላውን ህዝብ ጥያቄ ሊመልስ አይችልም” በማለት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ በሚመሩት ጊዜያዊ የክልሉ መስተዳድር ላይ ቅሬታ አሰምተዋል።
በሰልፉ ላይ የትግራይ ኃይል አባላት በመቀለ ከተማ ከጥዋቱ 2:30 ጀምሮ በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄዱ ሲኾን የተለያዩ የመብት ጥያቄዎች እንዲሁም ለተፈናቃዮች እየተሰጠ ያለውን ትኩረት በቂ አለመኾኑን የሚያወግዙ ሐሳቦች አንፀባርቀዋል።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ መፈክሮችን እያሰሙ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዝዳንት ፅህፈት በማምራት የክልሉን ጊዜያዊ መስተዳድር ፕሬዝዳንት ለማነጋገር ፈልገው ነበር። ይሁንና የጊዜያዊ መስተዳድሩ ፕሬዚዳንት ማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል።
በወቅቱ ጥያቄያቸው ስምቶ መልስ የሚሰጥ የጊዜያዊ መስተዳድሩ ሐላፊዎች በማጣታቸው የተቆጡት ሰልፈኛቹ ከቀኑ 7:00 እስከ 11:00 ባሉ ሰአታት የከተማው አውራ መንገድ ወደ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የሚወስደው ዋናው መንገድ በድንጋይ ዘግተውት መዋላቸውን ተገልጿል።
የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ዋናው መንገድ መዝጋታቸውን ከተሰማ በኃላ ከጊዚያዊ መስተዳድር ፅሕፈት ቤት የተወከሉ ከፍተኛ አመራሮች ሰልፈኞቹን ለማነጋገር ፍቃደኛ በመሆናቸው እንዲሁም ለውይይት መቀመጣቸውን ተከትሎ ተዘግቶ የነበረው መንገድ መከፈቱን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል ።
ዘግይቶ የተሰማው ዜና እንደሚያመለክተው ሌተና ጄኔራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ የትህነግና የሰራዊት አዛዦች ናቸው ከተባሉና በስም ካተዘረዘሩ ጋር ተነጋግረዋል። በውይይቱ ማጠናቀቂያ ምን አቋም እንደተያዘ በይፋ ባይነገርም፣ ለቀረበው የኢኮኖሚና የቁሳቁስ ጥያቄ “ አቅም ስለሌለን ነው፣ ወደፊት እናሟላለን” የሚል ምላሽ መሰትቱን አዲስ ሪፖርተር ሰምታለች።
ከሰብሰባው አዳራሽ ተቆርጦ የወጣው መሆኑ በተነገረለት አንድ ቪድዮ እንደተሰማው ከሆነ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የደመወዝ ፣ የድጎማ፣ የጥቅማጥቅምና የመኖሪያ ቤት የመስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
ከአቅሙ በላይ ሰፊ የወታደር ኃይል አሰባስቦ የክልሉን በጀት በአብዛኛው ለወታደር ደሞዝ የሚያውለው የትግራይ አስተዳደር አሁን ላይ የተነሳበት የደሞዝ ጭማሪ፣ የመለያ ልብስና ጫማ ጥያቄ ለመመለስ እንደማይችል አስቀድሞ ሲገለጽ እንደነበር ይታወሳል።
የትህነግ የንግድ ድርጅት የሆነውን ኤፈርትን ቦርዱን በማፍረስ በአዲስ የሰየመው ትህነግ፣ የንግድ ድርጅቱ በሚያስገባው ገቢው የታጣቂዎቹን ደሞዝ እንደሚጨምር ማስታወቁ አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰላማዊ ሰልፉ ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ላይ ማነጣጠሩን የሚጠቁሙ አዳዲስ መረጃዎች እየወጡ ነው። በሳቸው ምትክ ትህነግ ከሻዕቢያ ጋር የጀመረውን ጥምረት ከሚመሩት መካከል አንዱ የሆኑትን የትህነግ ምክትል ሊቀመንበር ኣማኑኤል አሰፋን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕፕሬዝዳት የማድረግ ዕቅድ እንዳለ ተሰምቷል።
በመቀለ ሃውልቲ አዳራሹ ከሌተናል ጀኔራል ታደሰ ጋር የተሰበሰቡት ሰልፈኞች ሌተናል ጀኔራል ታደሰ ወረደ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ስልጣናቸውን በአስቸኳይ እንዲለቁ መጠየቃቸው ተሰምቷል። ይሁን እንጂ ይህ ዜና ከድርጅቱ በይፋ አልተሰማም።
ስምንት መሰረታዊ ጉዳዮችን ለመፈጸም ቃል ገብተው በፌደራል መንግስቱ የተሾሙት ታደስ ወረደ፣ በዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመራውን አንጃ ጋር ቅንጅት በመፍጠራቸው ቢነቀፉም፣ ሻዕቢያ እንዳልወደዳቸው አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች እያስታወቁ ነው።
ሰሞኑን ከመንግስት ሚዲያ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን፣ በፕሪቶሪያው የሰላም አማራጭ ስምምነት መሰረት ተቋቁሞ የነበረውን ጊዜያዊ አስተዳደር በሴራና፣ ወታደራዊ ኃይል በመጠቀም ያፈረሱ መሆናቸውን ጠቅሰው ከሰዋቸው ነበር። በትግራይ ለውጥ ለማምጣት የጋራ ካውንስል ያቋቋሙት አራት ፓርቲዎችና ሶስት ተሰሚነት አላቸው የሚባል ወገኖች ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከስላጣን እንዲወርዱ ቀዳሚ ፍላጎታቸው እንደሆነም አክለው ገልጸው ነበር።
- “የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሚቀጥለው ሳምንት ኤርትራን ይወራል በውስጥ ያለው አመጽ ይፍጠን” የሻዕቢያ መረጃ ያስተላለፈው መመሪያ
“አስችኳይ ነው። ሩጫው ከጊዜ ጋር ነው” በማለት ደጋግመው ገለጹ። ይህን የሚናገሩት አቶ ነዓምን ዘለቀ ናቸው። አቶ ነዓምን ይህን የሚናገሩት ለአቶ ልደቱና በቅርባቸው ላሉ የአመጽ አመቻች የቴክኒክ ኮሚቴ የተመረጡ አባላት… Read more: “የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሚቀጥለው ሳምንት ኤርትራን ይወራል በውስጥ ያለው አመጽ ይፍጠን” የሻዕቢያ መረጃ ያስተላለፈው መመሪያ - ሻዕቢያ ያደራጀው የአመጽ ቀስቃሽ ኮሚቴ ዲያስፖራው ስለፈራ አገር ቤት አመጽ ማስነሳት ቅድሚያው አደረገ
ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ፤ ኢህአፓን ማገዝና ብረት ያንሱ ድርጅቶችን ስለመርዳት ምክክር ይደረጋል አዲስ ሪፖርተር – ራሱን አክስሞ ሻዕቢያ ባደራጀውና አቶ ነዓምን በሚመሩት የአመጽ አመቻች ቴክኒክ ኮሚቴ ውስጥ ተካቶ የነበረው… Read more: ሻዕቢያ ያደራጀው የአመጽ ቀስቃሽ ኮሚቴ ዲያስፖራው ስለፈራ አገር ቤት አመጽ ማስነሳት ቅድሚያው አደረገ - ፕሮፌሰር መሐመድ “ቀጣፊ ነው፤ የሚልኩብን እነሱ [ሻዕቢያዎቹ] ናቸው” ነዓምን
አዲስ ሪፖርተር – በኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ አነጋጋሪ ሰው ናቸው። በሁለት ጽንፍ ተፈርጀው ይተቻሉ። በአንድ በኩል “ለኦሮሞ ሕዝብ ማንነትና ታሪክ የታገሉ ምሁር” የሚሏቸው አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ… Read more: ፕሮፌሰር መሐመድ “ቀጣፊ ነው፤ የሚልኩብን እነሱ [ሻዕቢያዎቹ] ናቸው” ነዓምን - የአመጽ አደራጅ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላቱን አባረር፤ በግምገማ “የተጋበዙ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና ሚዲያዎች ሸሽተውናል” ተባለ
በዋሽንግቶን ዲሲ እና በሎንዶን ይካሄዳል የተባለው ‘ምድር አንቀጥቅጥ’ ሰላማዊ ሰልፍ በስጋት እንዲቀር አሳብ ቀረበ አዲስ ሪፖርተር ባለፈው ቅዳሜ ሚሊዮኖች እንደሚሳተፉበትና “አየር አንቀጥቅጥ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶት በተካሄደው የኢንተርኔት የተቃውሞ ሰልፍ… Read more: የአመጽ አደራጅ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላቱን አባረር፤ በግምገማ “የተጋበዙ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና ሚዲያዎች ሸሽተውናል” ተባለ - የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ
አዲስ ሪፖርተር – የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዶ/ር አኔት ዌበር Dr. Annette Weber ለኤርትራ መሪዎች ጣልቃ ገብነታቸውን እንዲያቆሙ አሳስበው መመለሳቸውን ተልትሎ በግል የኤክስ ገጻቸው በዲፕሎማት ቋንቋ ያሰፈሩት… Read more: የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ






