በአልጄርስ ስምምነት መሠረት የተቋቋመው የድምበር ኮሚሽን አመሠራረትና ኮሚሽኑ የሰጠው ውሳኔ ሲገመገም

Date:

ይህም ስለኢትዮጵያ የዕውቀት ማነስ በኮሚሽኑ ውሳኔ ላይ እንዴት እንደተንፀባረቀ ወደፊት እናየዋለን፡፡ በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ በህግ፣በታሪክና በሥነ መንግሥት እውቀታቸውና በሥራ ተሞክሮአቸው የታወቁ በትላልቅ ዩኒቨርስቲዎችና ልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የላቀ ሚና የሚጫወቱ ሌላው ዓለም ግልጋሎታቸውን የሚፈልገው ኢትዮጵያውያን በዚህ ትልቅ አገራዊ ጉዳይ እርዳታቸውን እንዲለግሱና ብሔራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ለምን እንዳልተጠየቁ ኢሕአደግ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያውያን እንደ ፈረንጆቹ ዘጠኝ ሚልዮን ዶላር ወጪ ሳያስወጡ አገራቸውን በዚህ ጉዳይ በነፃ ለማግለገል ፈቃደኛ ይሆኑ እንደነበረ መጠርጠር አይቻልም

በኤርትራና በኢትዮጵያ መሃከል የነበረው ቁጥራቸው እስከ

ዛሬም በሁለቱም ባላጋራዎች ያልተገለፀ በጣም ብዙ ኢትጵያውያንና ኤርትራውያን ወንድማማቾችና እህትማማቾች የተላለቁበት ጦርነት፣ ብዙ ዋጋ ብትከፍልም በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተደምድሞ የሁለቱም አገሮች መሪዎች በወቅቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሊቀ መንበር በነበሩት በአልጄሪያው ፕሬዝደንት በአብዱል አዚዝ ቡተፍሊካ አደራዳሪነት ሰላም ለማውረድ የድምበር ስምምነት ለመፈራረምና ለመካሰል ወደ አልጄሪያ ዋና ከተማ
አልጄርስ አቀኑ።

ድርድሩ በአጭር ቀናት ውስጥ ተጠናቅቆ በተኩስ አቁም

ስምምነት፣ የድምበር ኮሚሽንና የካሣ ኮሚሽኑ በሚያቋቁመው ሰነድ ላይ የሁለቱም አገሮች መሪዎች አቶ መለስ ዜናዊና አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ፈርመው ጥላቻና ቂም በሚያንፀባርቅ መልክ ተጨባብጠው በሌላ ወቅት እንደተለመደው ሳይተቃቀፉና አንዲት ቃል ሳይለዋወጡ ተለያዩ፡፡

በሁለቱ ወንድማማች “የሐበሽ መሪዎች (አቶ ኢሣያስ ቢክዱም)አንድ የአረብ አገር መሪ መሃል ገብቶ ሲያጨባብጣቸው ማየት ሕሊናን የሚሰብር ትዕይንት ነበር፡፡ እ.አ.አ. በዲሴምበር 12 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሁለቱ መሪዎች ድንበር ማካለሉ በቅኝ ግዛት ውሎችና በሌሎች ሕጐች መሠረት እንዲሆን ተስማምተው ሲጨባበጡ የተላለፈው መልእክት የኢትዮጵያ የባህር በር ተዘጋ፤“በቃ ተዘጋ” የሚል ለኢትዮጵያውያን አስደንጋጭ መልዕክት ነበር።

የአልጄርስ ስምምነትና ውሳኔ ከውጫሌው ውል ባልተናነሰ

ምናልባትም በከፋ መልኩ በአገር ላይ ጉዳት ያደረሰ ውል ስለሆነ ድርድሩ ቀጠና (Venue) አመራረጥ ጀምሮ የሊቀ መንበሩ አሰያየም ፤ ለድርድሩ መሠረት የሆኑ ሕጎችንና የዳኞቹ አመራረጥና ገለልተኛነት የድርድሩ አካሄድ መመርመር ያስፈልጋል።

እነዚህን የ1900ዓ.ም፣ 1902ዓ.ም እና የ1908ዓ.ም ስምምነቶችን በሥራ ላይ ለማዋል በአልጄርስ የተፈረሙው

ስምምነት በኢትዮጵያ ላይ ዘላቂ ጉዳት የሚያስከትል የኢትዮጵያን የባህር በር የሚዘጋና አሰብን ለኤርትራ የሰጠ ስምምነት ሲሆን፣ ይህ የአልጀርስ ስምምነት አጼ ምኒልክ እንደፈረሙአቸው “ውሎች” በኢትዮጵያ ላይ በግድ የተጫነ ሳይሆን የኢትዮጵያ መንግስት ሕወሓት/ኢሕአዴግ ፈቅዶ (ምናልባትም ለምኖ) ዳኛ መርጦ፣ሥልጣናቸውና የሚዳኙበት ሕግ ወስኖ የገባበት ስምምነት ነው፡፡

የዚህም ውል ዋናው ዓላማ የኢትዮጵያና የኤርትራ የጋራ

ድምበር የሚያካልል አምስት ዳኞች የያዘ ኮሚሽን አቋቁሞ ኮሚሽኑ የተባበሩት መንግሥታት የአውሮፖ ኀብረት፤ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአሜሪካ ተወካዮች በአስፈጻሚነት በተገኙበት የተቈረጠ ይግባኝ የሌለበት ውሳኔ መስጠትና ድምበር ማካለል ነበር፡፡

►የየአገራቱ ተወካዮች ማንነት

በኮሚሽኑ ፊት የኢትዮጵያን ቡደን የመሩ በውጭ ጉዳይ

ጉዳይ ሚኒስትርነት ክብረ ወሰን የያዙት በጊዜው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት የሕወሓት መሥራች አባል አቶ ሥዩም መስፍን ሲሆኑ በተባባሪነት ደግሞ የህግ ባለሙያ የሆኑት አምባሳደር ፍሰሐ ይመር ተመድበው ነበር፡፡ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አባል የሆኑ አንድ የሕግ ባለሙያ የመንግሥት ባለስልጣን በቡድኑ ተጨምረው፣ ሌሎች አስራ አንድ የውጭ አገር ዜጎችን ጨምሮ በጠቅላላው ኢትዮጵያ አስራ አራት አባላትን በሚያካትት ቡድን ተወክላ ነበር፡፡ ወሳኝ በሆነው በሕግ አማካሪነትና በጥብቅናው ዘርፍ ማንም ኢትዮጵያዊ አለመመደቡ ሊሠመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ናቸው ክርክሩን አዘጋጅተው በድምበር ኮሚሽኑ ፊት ቀርበው የሚሟገቱት ፡፡ ሌሎቹ የቡድኑ አባላት አማካሪዎች ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ የአንድ ኢትዮጵያዊ እንኳን በቡድኑ መካተት ወደ ፊት እንደሚታየው ግልጽ የሆኑ የኤርትራና የኢትዮጵያ ታሪካዊ ግንኙነቶችን በተመለከተ የተሠሩ ስህተቶችን ማረም ያስችል ነበር፡፡

የኤርትራው ቡድን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ሰይድ አብደላ ሲመራ ተባባሪአቸው ደግሞ ፕሮፌሰር ሲያ ብሪልሜየር ( Lea Brimayer) ነበሩ፡፡ የኤርትራ ቡድን በውስጡ ሦስት የመንግስት ባለስልጣናትና አንድ የኤርትራ ዩኒቬርሲቲ ፕሮፌሰር ያቀፈ ሲሆን፤ እንዲሁም አስር የውጭ ዜጎች አካትቶ በጠቅላላው ኤርትራ በአሥራ አራት ሰዎች ስትወከል በሕግ አማካሪነትና በጥብቅናው ዘርፍ ከውጭ አገር ዜጐች በተጨማሪ የአሥመራ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ ኘሮፌስር የማነ ምሾጊና ተመድበው ነበር፤

ሁለቱ ቡድኖች ሲነፃፀሩ ኢትዮጵያ በኮሚሽኑ ውስጥ አስራ

አራት ሰዎች ስታሠማራ ኤርትራም እንደዚሁ አስራ አራት
ሰዎችን መድባ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ በኩል ሁሉም የመንግሥትን አቋም የሚያቀነቅኑ ግለሰቦች ሲሆኑ የአልጄርስን ስምምነት የተቀበሉና የኢትዮጵያ የባህር በር እንዲዘጋ የተስማሙ ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያን የባህር በር መዘጋት የሚቃወሙ ቢሆኑ ኖሮ ጣልያን በኢትዮጵያ ላይ የጫነቻቸው የኢትዮጵያ የባህር በር በእርግጠኝነት የሚዘጉና የፈረሰ የቅኝ ግዛት ውሎችን
ተቀብለው ኢትዮጵያን ወክለው በድርድሩ ባልተገኘም ነበር፡፡

ሁለቱ ቡድኖች የሚለያቸው ነገር ቢኖር የኤርትራ ዜጎች

በኮሚሽኑ ውስጥ የነበራቸው ተሳትፎ የጎላ ሲሆን የኢትዮጵያውያን ተሳትፎ አነስተኛ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው ኤርትራ ከውጭ አገር ዜጎች ሌላ በሕግ አማካሪነትና በጥብቅናው ዘርፍ አንድ ኤርትራዊ ስትመድብ በዚህ እጅግ ወሳኝ በሆነ ዘርፍ ማንም ኢትዮጵያዊ ካለመመደቡም ሌላ ኢትዮጵያን የወከሉ የውጭ አገር ዜጎች አንዳቸውም በኢትዮጵያ ጥናት ማለት በሕግ፤በኢትዮጵያ ታሪክና ባሕል እውቀት የተካኑ ነበሩ ለማለት የሚያስደፍሩ አልነበሩም፡፡

ይህም ስለኢትዮጵያ የዕውቀት ማነስ በኮሚሽኑ ውሳኔ ላይ እንዴት እንደተንፀባረቀ ወደፊት እናየዋለን፡፡ በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ በህግ፣በታሪክና በሥነ መንግሥት እውቀታቸውና በሥራ ተሞክሮአቸው የታወቁ በትላልቅ ዩኒቨርስቲዎችና ልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የላቀ ሚና የሚጫወቱ ሌላው ዓለም ግልጋሎታቸውን የሚፈልገው ኢትዮጵያውያን በዚህ ትልቅ አገራዊ ጉዳይ እርዳታቸውን እንዲለግሱና ብሔራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ለምን እንዳልተጠየቁ ኢሕአደግ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያውያን እንደ ፈረንጆቹ ዘጠኝ ሚልዮን ዶላር ወጪ ሳያስወጡ አገራቸውን በዚህ ጉዳይ በነፃ ለማግለገል ፈቃደኛ ይሆኑ እንደነበረ መጠርጠር አይቻልም።

ምንጭ አሰብየማናት፤ያዕቆብኃይለማርያም፤107-10

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...

የፕሮፌሰሩ እይታ “ጠንቋይ የሰዉን እንጂ የራሱን አያዉቅም” አብይ አሕመድ ነጥብ አስጥለዋል

ሀገር የምትገነባው መንግስት ያድርግ በሚሉ ጥያቄዎች ሳይሆን እኔ ይሄን...